A. A. Airport Customs page

A. A. Airport Customs page በ2022 በአገራችን ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳደር ተገንብቶ ማየት ፡፡

ሁለንተናዊ አቅሙ የተገነባ የሰው ኃይል በማፍራት፤ ዘመናዊ የጉምሩክ አስተዳዳር ሥርዓት በመዘርጋት፤ ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት፤ የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴን ማሳለጥ፤ ንግድ ማጭበርበርና ኮንትሮባንድን መከላከልና መቆጣጠር፤ የማህበረሰቡን ደህንነት መጠበቅ እና ገቢን በብቃት መሰብሰብ፡፡ "ተለዕኮ"

14/08/2026

ነሐሴ 08 ቀን 2018 ዓ.ም
የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱና የተተው የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች ፣የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት ፣ጫማዎች ፣ የብር ጌጣጌጥ እና ሌሎች ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 10/2019 በቀን 4/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 11/2019 በቀን 7/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 12/2019 በቀን 11/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 13/2019 በቀን 14/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 14/2019 በቀን 18/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 15/2019 በቀን 21/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 16/2019 በቀን 25/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 17/2019 በቀን 28/12/2018 ዓ.ም መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ

1.በቅ/ጽ/ ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የዘመኑ ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2.ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00( አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
3.በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO)CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል፡፡
4.በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጸች መሠረት ለመረጡት የዕዋዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፤ የተጫራቾች ስም ፣ አድራሻ፣ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ( cpo ) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5.ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና መሻሸል አይችልም፡፡
6.ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል ፡፡
7.የጨረታ አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05 (አምስት) ቀናት ውሰጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባችው፡፡
8.ከላይ በተ/ቁ 7 በተገለጸው ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ(cpo) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
9.በተራ ቁጥር 01-08 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 10/2019 በቀን 4/12/2018 ዓ.ም ፣ ጨረታ ቁጥር 11/2019 በቀን 7/12/2018 ዓ.ም ፣ ጨረታ ቁጥር 12/2019 በቀን 11/12/2018 ዓ.ም ፣ ጨረታ ቁጥር 13/2019 በቀን 14/12/2018 ዓ.ም ፣ ጨረታ ቁጥር 14/2019 በቀን 18/12/2018 ዓ.ም ፣ ጨረታ ቁጥር 15/2019 በቀን 21/12/2018 ዓ.ም ፣ ጨረታ ቁጥር 16/2019 በቀን 25/12/2018 ዓ/ም ፣ ጨረታ ቁጥር 17/2019 በቀን 28/12/2018 ዓ/ም ከጥዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሄድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ አያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል፡፡
10.በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾ ች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100‚000.00/መቶ ሺህ/ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
11.ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ካቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃለን፡፡
12.ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታው ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳዉቃልን፡፡
13.ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0116684537 እና 0116684193 ደዉለው ይጠይቁ፡፡

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when A. A. Airport Customs page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share