03/09/2026
የአሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በባስኬቶ ዞን በመገኘት የበጎ ተግባር መርሐ-ግብር አካሄደ
ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም
በጎነት ለእህትማማችነት ለሴቶች ተሳትፎ ተጠቃሚነት በሚል መሪ ቃል ድንበር ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት መርሐ-ግብር ነው የአሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ያካሄደው።
በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክንፉ ሻቦ ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር ሰውን ታሳቢ ያደረገ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አቅመ ደካሞችን ፈልጎ በመድረስ በልዩ ትኩረት እውነትን መሰረት ያደረገ በጎ ተግባር ላለፋት ሰባት አመታት እየተሰራ ቆይቷል ስሉም አቶ ክንፉ አክለዋል።
ይህ የበጎነት ተግባር በአንድ አካባቢ ተወስኖ እንዳይቀር መስፋት አለበት በማለት የወንድም አሪ ህዝብ ላደረገው ድንበር ተሻጋሪ በጎ አድራጎት አመስግነዋል።
የአሪ ዞን ህዝብ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬ ብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ያሉ ስሆን ይህን መርህ በማድረግ በጎነት ድንበር ብሔር ሀይማኖት የለውምና ይህን ታሳቢ በማድረግ ወደ ባስኬቶ ዞን መጥተናል ብለዋል።
በበጎ ስራ ከዚህ ቀደም በርካታ አቅመ ደካሞች ተገልግለዋል ስሉም አክለዋል።
መደጋገፍና በጎ ተግባር አብሮነትን ከማጠናከር አንጻር ፋይዳው የጎላ መሆኑን የገለፁት የላስካ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ሀይሌ ከበጎነቱ ባሻገር አሪ ዞን ለወንድም ባስኬቶ ሁለተኛዋ ከተማ ናት ብለዋል።
የአሪ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ወ/ሮ ይመኙሻል ተፈሪ በበኩላቸው እንደገጹት በጎ ተግባር ዘር፣ ሀረግ፣ ብሄርንና ኃይማኖትን ባለመለየት ሰው ለሆነው ሁሉ በልግስና የሚከወን መልካም ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
የባስኬቶ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ መብተ ግሮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሴቶች ክንፍ በርካታ የበጎነት ስራዎች ተሰርተዋል ስሉ ገልጸዋል።
በጎነት የህዝብ ለህዝብ ያለውን መስተጋብር ከማጠናከር አኳያ ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ያሉ ስሆን ይህ በሁሉም ማሕበረሰብ ተጠናክሮ የኢትዮጵያን የቀደመ አንድነት መስተጋብር ማጠናከር ይገባል ስሉም ወ/ሮ መብተ አክለዋል።
የበጎ ተግባር ስራው በባስኬቶ ዞን ላስካ ከተማ አስተዳደር የአንድት አቅመ ደካማ ቤት ስራ ያስጀመረ ስሆን በላስካ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመገኘት ለወላድ እናቶች እንዲሁም ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አድርጓል።
ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም
#ላስካ