Addis Ababa Tourism Commission

Addis Ababa Tourism Commission Addis Ababa Tourism Commission

"የማንሠራራት ቀን" በአራዳ ፓርክ በደመቀ ሁኔታ ተከበረጳጉሜ 2/2018ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን)"የማንሠራራት ቀን" በዛሬው ዕለት በርካታ ወጣቶችና የብስክሌት ስፖርት አፍቃሪዎች በተገኙበት በ...
07/09/2026

"የማንሠራራት ቀን" በአራዳ ፓርክ በደመቀ ሁኔታ ተከበረ

ጳጉሜ 2/2018ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን)

"የማንሠራራት ቀን" በዛሬው ዕለት በርካታ ወጣቶችና የብስክሌት ስፖርት አፍቃሪዎች በተገኙበት በአራዳ ፓርክ በተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶች በደመቀ ሁኔታ ተከበረ።

ስፖርታዊ ኩነቱን ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ፤ በአዲስ አበባ በተከናወኑት ስር ነቀል የቱሪዝም የልማት ስራዎች ዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ ከማንሰራራት ባሻገር የከተማዋን ኢኮኖሚ በመደገፍ መሠረታዊ እመርታ እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል::

በተለይም በከተማዋ በተሰሩት በርካታ የስፖርት መሠረተ ልማቶች የህብረተሰቡን አኗኗር ከማሻሻል አልፈው አዲስ አበባ የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል እንድትሆን ጉልህ ሚና እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል::

Calaqqee Aadaa Ummata Oromoo kan ta'e agarsiifni Goobeefi Shinooyyee haala ho'aa ta'een Magaalaa Finfinneetti gaggeeffam...
06/09/2026

Calaqqee Aadaa Ummata Oromoo kan ta'e agarsiifni Goobeefi Shinooyyee haala ho'aa ta'een Magaalaa Finfinneetti gaggeeffamuu eegalee jira!

የኦሮሞ ባህል መገለጫ የሆነው የጎቤ እና ሺኖዬ ክብረ በዓል በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን )የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞ...
05/09/2026

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች እና የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጎበኙ፡፡

ነሀሴ 30/2018 ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን )

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከአንጦጦ መቀጠያ እስከ ፒኮክ ፓርክ ድረስ የተሰሩትን የወንዝ ዳርቻ ልማትን ጉብኝተዋል:: ሰራተኞቹ የመዲናዋን አዲስ ገጽታና የቱሪዝም ሳቢነት የሚያጎሉ የመሰረተ ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ተመልከተዋል።

በጉብኝታቸውም በመዲናዋ የተከናወኑት የልማት ስራዎች እጅግ የሚደነቁ መሆናቸውን ጠቁመው፣ አዲስ አበባን የአፍሪካ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የልማት ስራ እንደሚደግፉ እና የድርሻቸውን ለመወጣት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ሰራተኞች በመዲናዋ የለሙትን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲጎበኙ በርካታ የማስተዋወቅ ስራን እያከናወነ ይገኛል::

03/09/2026
01/09/2026
2ኛው የአዲስ አበባ ሆስፒታሊቲ እና የቱሪዝም እውቅና መስጠት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል ።ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን)የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ያዘ...
29/08/2026

2ኛው የአዲስ አበባ ሆስፒታሊቲ እና የቱሪዝም እውቅና መስጠት መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል ።

ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን)

የአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማህበር ያዘጋጀው ሁለተኛ ዙር ሆስፒታሊቲ እና የቱሪዝም ዕውቅና መርሃ-ግብር እና ፓናል ውይይት እየተካሄደ ይገኛል ።

ማህበሩ በአዲስ አበባ ላይ የሚገኙ የሆቴልና ቱሪዝም ባለሙያዎች እንዲሁም በዘርፉ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ ተቋማትና ግለሰቦች ዕውቅና ይሰጣል።

በመድረኩ የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር እንደገና አበበ እንዲሁም የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሁንዴ ከበደ ተገኝተው መልክት አስተላልፈዋል::

የቱሪዝም ዘርፍ አገልግሎት ለማሳደግ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት የባለሙያዎች ድርሻ ወሳኝ መሆኑን በመግለጽ ዕውቅና መስጠት ዘርፉን ይበልጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

የ76ኛው የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ ጉባኤ (RC76) ልዑካን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን)በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገ...
28/08/2026

የ76ኛው የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ ጉባኤ (RC76) ልዑካን በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎበኙ

ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም (ቱሪዝም ኮሚሽን)

በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ኮሚቴ ጉባኤ (RC76) ላይ የአህጉሪቱን የጤና ሴክተር የሚመሩ ከየአፍሪካ አባል ሀገራት የተውጣጡ የጤና ሚኒስትሮች ፣ ከፍተኛ የዓለም ጤና ድርጅት አመራሮች፣ ከተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች የመጡ ተወካዮች፣ የልማት አጋሮች እና በርካታ አለም አቀፍ ታዳሚዎች የከተማችንን የቱሪዝም መዳረሻዎች እንዲሁም የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ይህ ጉብኝት፤ እንግዶቹ አህጉራዊ የጤና አጀንዳዎችን ከመምከር ባለፈ፣ ከተማችን በቱሪዝምና በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን ለውጥ በቅርበት እንዲያዩት ልዩ አጋጣሚ ፈጥሮላቸዋል።

በርካታ ሀገራት እንዲሁም ዓለም-አቀፍ ተቋማትን ያሰባሰበው ይህ ጉባኤ፤ ከተማችን አለም አቀፍ መድረኮችን በብቃት የማስተናገድ አቅሟን ከማረጋገጡም በላይ፣ የቱሪዝም ፀጋዎቿን እና የልማት ስራዎቿን ለአለም ለማስተዋወቅ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።

27/08/2026
ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ዕውቀት ለመቅሰም ዕድሉ እነሆ!በነጻ በሚሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የማስተርክላስ መርሃ ግብርን ይቀላቀሉ፤ ከኦክስፎርድ MBA ተወካዮችና ባለሙያዎች ስለ ቱሪዝም፣ አ...
27/08/2026

ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ዕውቀት ለመቅሰም ዕድሉ እነሆ!

በነጻ በሚሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የማስተርክላስ መርሃ ግብርን ይቀላቀሉ፤ ከኦክስፎርድ MBA ተወካዮችና ባለሙያዎች ስለ ቱሪዝም፣ አመራርነት፣ ዘላቂ ዕድገትና ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጠራ ላይ ጠቃሚ ግንዛቤዎችን ያግኙ።

📅 ነሐሴ 25– 26

መሳተፍ ይፈልጋሉ?

🔗 አሁኑኑ ይመዝገቡ፦
https://regenerativeafrica.com/masterclasses/

ይህ ዕድል እንዳያመልጥዎ!

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ! ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና)   መርቀን ...
26/08/2026

የዘመነ መሰረተ ልማት፤ የዘመነ አገልግሎት ለዘመናዊ ከተማ!

ዛሬ በከተማችን አራት ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ ተርሚናሎችና ገበያ ማዕከላት (በጎተራ፥ ቦሌ፣ የካ እና ቀበና) መርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

እነዚህ መሰረተ ልማቶች የትራፊክ መጨናነቅን የሚያቃልሉ፣ የትራንስፖርት ሥርዓትን የሚያሻሽሉ፣ ህዝባችንን ከዝናብና ፀሐይ እንግልት የሚከላከሉ፣ በርካታ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ ምቹ ፣ ንፁህ እና የሰውን ክብር የሚመጥኑ የዘመነ አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።

መሰረተ ልማቶቹ በአንድ ጊዜ በርካታ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የታክሲ እና የአውቶቡስ ተርሚናሎች፣ የአየር ብክለትን የሚከላከሉ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች፣ ሰፊ የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የንግድ ሱቆች፣ ካፍቴሪያና ሬስቶራንቶች፣ የልጆች መጫወቻና ማረፊያ ስፍራዎች፣ ምቹ የተሳፋሪ መጠበቂያ ስፍራዎች፣ የአስተዳደር እና የትኬት መቁረጫ ቴክኖሎጂዎች፣ አሳንሰሮች እና ንፁህ መፀዳጃ ቤቶች እንዲሁም የደህንነትና የአደጋ ቅድመ መከላከል ሥርዓቶች የተሟሉላቸው የኢኮኖሚና የማህበራዊ አገልግሎትን ለማሳለጥ ትልቅ አስተዋጽዖ የሚያበረክቱ ናቸው።

ከለውጡ በፊት 3 ሺህ ብቻ የነበረውን የአንድ ጊዜ የተሽከርካሪ ማቆሚያ አቅም እና ምንም ያልነበረንን ተርሚናል በአሁኑ ጊዜ በጥራትና በፍጥነት የተገነቡ፣ ዘመናዊ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችን እና ተርሚናሎችን ከ170 ሺህ በላይ ማድረስ ችለናል ።
ለከተማችን ነዋሪዎች ተጠቃሚነት በተጨባጭ ቃላችንን በተግባር ስራዎችን እየፈጸምን በቅንነትና በታማኝነት እየሰራን እንገኛለን። አዲስ አበባ ከዚህ በላይ ይገባታል ቀጣይም ከሰራነው በላይ እንተጋለን!

የዛሬዎቹ ፕሮጀክቶች እውን እንዲሆኑ ለተጋችሁ፣ ላስተባበራችሁ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች፣ የትራንስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ ኮንትራክተሮች፣ አማካሪዎች በዚህ ስራ የተሳተፋችሁትን ሁሉ ከልብ አመሰግናለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

Address

Arat Kilo
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Tourism Commission posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share