25/08/2026
የመጨረሻ ምዕራፍ
የጋዝ አንቸ የንፁህ መጠጥ ውሃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ተጠናቋል። በዉሃ የተቸገሩ እናቶች ፣አዛውንቶች ፣ ህፃናቶች ዉሃ ሲጠጡ ማየት ያስደስታል።እኔ ከዚህ በላይ እርካታና ደስታ የለኝም።
ውሃው አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ሙሉ በሙሉ በሶላር እንዲሰራ የተደረገ ሲሆን ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ ተገንብቷል፡፡
ሀፃናቶችም ለመጀመመሪያ ጊዜ ከውሃው ተጎንጭተዋል። የህብረተሰባችንን የውሃ ጥማት ለማርካት ያብቃን።
ለመመረቅ ተቃርበናል።ውሃው ከትምህርት ቤቱ ዉጭ ለማህበረሰብም ተጠቃሚ እንዲያደርግ ተደርጓል።
የትምህርት ቤቱም ግንባታ እየተፉጠነ ነው ።
ስለሁሉም አምላክ ይመስገን!!!