የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን, Government Organization, Tewodros Square, Churchill Avenue, Addis Ababa.

To become competent and effective institution that has been able to create a vibrant civil society sector and a civilized culture that ensures the full benefit of the society by 2030.

24/08/2026
የንብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
17/08/2026

የንብረት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዬች ዙሪያ የመግባብያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡****************************...
13/08/2026

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር በጋራ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዬች ዙሪያ የመግባብያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
**********************************************************************
የስምምነት ማዕቀፉ የመረጃ ልውውጥ፣የጋራ ቁጥጥር፣የአቅም ግንባታ እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡

በፕሮግራ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ እንደገለጹት ከዚህ ቀደም ከባለስልጣኑ ጋር የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን ገልጸው በተለይም በዝርዝር የትብብር መስኮች መካከል በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ስም ተመዝግበው ህገ-ወጥ የንግድ ሚዲያ ስራ የሚሰሩ ድርጅቶችን መቆጣጠር ላይ በጋራ መስራት ይጠይቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ እንደተናገሩት በባለስልጣኑ በርካታ የሙያ ማህበራት መመዝገባቸውን ገልጸው ዜጎች የመደራጀት መብት እንዳላቸው ሁሉ ህግን እና አሰራርን አክብረው መፈጸም ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ በስምምነት ሰነዱም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ጋር ያስቀመጥናቸውን ጉዳዬች ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣንን ጨምሮ አስራ አንድ የሚመለከታቸው ባለድርሻ የመንግስት ተቋማት ጋር ውጤታማ ሬጉላቶሪ ስርዓት ለማጠናከር የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈራርሟል፡፡

የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ።የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ...
11/08/2026

የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ።

የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት በሴቶችና ህጻናት ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት 15 ዓመታት በላይ አገልግሎት እየሰጠ ያለ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን በዋናነት የሚሰራቸው ስራዎች በጎዳና ላይ ተጥለው የሚገኘ ህጻናት የማሳደግ እንዲሁም የህጻናትን ቤተሰቦች የመታደግና የማቋቋም ስራዎችን ይሰራል፡፡ በተጨማሪም ህጻናቱ ቤተሰቦቻቸው እጅ እያሉ የምግብ፣ የአልባሳት፣ የህክምና እና የትምህርት ወጪያቸውን በመሸፈን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው የጠፉ ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘት ስራዎችን ይሰራል፡፡

የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር አቶ ያሬድ አብዱ አጠቃላይ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ በሚያስጎበኙበት ወቅት እንዳሉት ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት በጎዳና ላይ ተጥለው የሚገኘ ህጻናት የማሳደግ እና የህጻናትን ቤተሰቦች የማቋቋም ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ህጻናቱ ቤተሰቦቻቸው እጅ እያሉ የምግብ፣ የአልባሳት፣ የህክምና እና የትምህርት ወጪያቸውን በመሸፈን እንዲሁም በተለያዩ ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው የጠፉ ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር የማገናኘት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት በአዲስ አበባና በሻሸመኔ በተለያዩ አማራጭ የድጋፍ አይነቶች ከ1700 በላይ ሴቶችና ህጻናት ልዩ ፍላጎት ያላቸውንም ጨምሮ አገልግሎ እየሰጠ ያለ ድርጅት እንደሆነ አንስተው በበጎ ፈቃድ ላይም በመሰማራት በከተማ ደረጃ ለአቅመ ደካማ እናቶች የቤት እድሳት በማድረግ ለማስረከብ መቻሉን አንስተዋል፡፡

የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ የተመለከቱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ድርጅቱ እያከናወነ ያለውን ስራ በመጎብኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ በተለይም በሴቶች እና ህጻናት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ይበልጥ ውጤታማና ስራዎችን መስራታቸው ለአገርም ለህብረተሰቡም የላቀ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸው በማንሳት ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት እያከናወኑ ያሉ ስራዎችን ለመደገፍ እና ለማገዝ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ።የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶ...
07/08/2026

የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ የባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት የስራ እንቅስቃሴን ተመለከቱ።

የሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት በምገባ እና በአቅም ግንባታ እንዲሁም በመልሶ ማቋቋም ላይ እየሰራቸው የሚገኙ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ባቡል ኸይር የበጎ አድድራጎት ድርጅት በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ላለፉት ስድስት ዓመታት ለአቅመ ደካማ እና ረዳት ለሌላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የዕለት ጉርስ ከማቅረብ ባለፈ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች፣ እንዲሁም ለበርካታ በችግር ላይ ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በመድረስ ራሳቸውን እንዲችሉና ከችግር እንዲላቀቁ እየሰራ የሚገኝ ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ነው።

የድርጅቱ መስራችና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሀናን መሀመድ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋወረው ባስመለከቱበት ወቅት እንደጠቆሙት ድርጅቱ በተለይም በርካታ ለችግር ተጋላጭ የሆኑና ልዩ ድጋፍ የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን በመመገብ፣ ሴቶችንና ወጣቶችን በማሰልጠንና አቅማቸውን በማጎልበት ከችግር እንዲላቀቁ አድርጓል።

በተጨማሪም ቤተል አካባቢ እያሰገነባ በሚገኘው የምገባና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል የጉድጓድ ውሀ በማውጣት ለአካባቢው ማህበረሰብ እያቀረበም ይገኛል።

ለበርካታ ሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር፣ ከስደት ተመላሽ ዜጎችን በማቋቋምም ወደር የለሽ ስራዎችን ማከናወኑንም ገልጸዋል።

ይህንኑ የድርጅቱን የስራ እንቅስቃሴ የተመለከቱት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ድርጅቱ ይበልጥ ውጤታማና አሁን እየሰራ ካለው ስራ በተሻለ መንገድ የህብረተሰቡን የላቀ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሃላፊዎች ደም ለገሱ።ባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞቹን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተ...
06/08/2026

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ሃላፊዎች ደም ለገሱ።

ባለስልጣን መስሪያቤቱ ሰራተኞቹን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን በማስተባበር በጦር ሃይሎች ሆስፒታል ከፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ደም የመለገስ ስራ ሰርቷል።

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በክረምት የበጎ ፍቃድ ስራ ከደም ልገሳ መርሃ ግብሩ በተጨማሪ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣የተማሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አና የአቅመ ደካማ የቤት ግንባታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

"ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የራሷን ሪከርድ የሰበረችበት እና ማድረግ መቻሏን ለዓለም ደጋግማ ያሳየችበት ታላቅ ዕለት ነው"ይህ ታሪካዊ ክንውን የኢትዮጵያውያንን...
04/08/2026

"ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኝ በመትከል የራሷን ሪከርድ የሰበረችበት እና ማድረግ መቻሏን ለዓለም ደጋግማ ያሳየችበት ታላቅ ዕለት ነው"

ይህ ታሪካዊ ክንውን የኢትዮጵያውያንን አንድነት፣ ቆራጥነት እና ለሀገራቸው ያላቸውን ተቆርቋሪነት በግልጽ ያሳየ እጅግ አስደናቂ ድል ሲሆን በዚህ አስደናቂ ተግባር የተሳተፋችሁ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችን በሙሉ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ምስጋና ያቀርባል፡፡

ማስታወቂያ
04/08/2026

ማስታወቂያ

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በጂማ ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር  ላይ ተሳትፍዋል ።ባለስልጣን መስሪያቤቱም በሂደቱ ላደረገ...
03/08/2026

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ በጂማ ከተማ የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፍዋል ።

ባለስልጣን መስሪያቤቱም በሂደቱ ላደረገው አስተዋጽኦ የምስጋና ሰርተፍኬት ከዞኑ ተበርክቷል።

የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከበርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካሂዷል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስ...
03/08/2026

የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከበርካታ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አካሂዷል፡፡

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከPHE Ethiopia Consortium እና ከወረዳው ጋር በመተባበር የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃግብር በሸገር ከተማ አስተዳደር ጣፎ ክፍለ ከተማ ጋራ ጋቲራ በሚባል አካባቢ 4500 ሃገር በቀል ችግኞች ተክለዋል።

‹‹ተስፋን እንትከል›› በሚለው በዚህ መርሃ ግብር ላይ የባለስልጣን መስሪያቤቱ አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች፣በርካታ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የቀበሌው አስተዳደሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Address

Tewodros Square, Churchill Avenue
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን:

Shortcuts

Share