06/08/2026
አዲስ መሶብ የአዲስ ከተማ ማዕከል ለህብረተሰቡ ፈጣን አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡
Addis MESOB: ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም.
በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት የአዲስ ከተማ ማዕከል አገልግሎቶችን ለማህበረሰቡ በዲጂታል ቴክኖሎጂ በአንድ ጣራ ስር በማቅረብ ተገልጋዬችን ከአሰልቺ ቢሮክራሲና እንግልት ሙሉ ለሙሉ በማላቀቅ አገልግሎቶችን በቀላሉ እያገኙ ነው፡፡
ከዚህ ቀደም ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም በመመላለስ አላስፈላጊ እንግልት ይደርስባቸው የነበሩ ተገልጋዬች አዲስ መሶብ ወደ ተግባር ከገባ ጊዜ ጀምሮ ፈጣን አገልግሎት፣ የጊዜና የወጪ ቁጠባን፣ ተደራሽነት እንዲሁም የተገልጋይ እርካታን በማሳደግ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ተገልጋዬችም የተቋሙን አመራሮች እና ሠራተኞች በማመስገን የአገልግሎት ጥራቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
Addis MESOB
The New Horizon of Service!
ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:
Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ
Website: addis.mesobcenter.et
Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!