Push Page

Push Page Welcome to Push Page! This page is dedicated to sharing insights and discussions on technology, innovation, social interaction, and occasionally, politics.

Our goal is to foster meaningful conversations, stay updated with the latest trends

ጠባሴ ቅዱስ ገብርኤል
21/08/2025

ጠባሴ ቅዱስ ገብርኤል

The African Development Bank (AfDB) has teamed up with Ethiopian Airlines 🇪🇹 to raise $8 Billion for the new Bishoftu In...
12/08/2025

The African Development Bank (AfDB) has teamed up with Ethiopian Airlines 🇪🇹 to raise $8 Billion for the new Bishoftu International Airport, planned to be Africa’s largest.

Ethiopian Airlines will fund 20% of the cost.

Located 40 km from Addis Ababa, the airport will be built in two stages, handling up to 110M passengers by 2029, with a goal to make Ethiopia a leading global aviation hub by 2035.

የእትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!________________________________1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና...
12/08/2025

የእትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!
________________________________

1ኛ ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡

4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-

፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡

፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-

= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-

፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)

፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ

፫= የጡረታ መለያ ቁጥር

፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ

፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ

፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ

፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡

ጉግል ምድርን በጥራት ማየት የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አስተዋወቀ*******ጉግል የዓለምን እያንዳንዱ ስፍራ የአየር ላይ ምስል ግልፅ በሆነ መንገድ የሚያሳይ “አልፋ ኧርዝ ፋው...
12/08/2025

ጉግል ምድርን በጥራት ማየት የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አስተዋወቀ
*******

ጉግል የዓለምን እያንዳንዱ ስፍራ የአየር ላይ ምስል ግልፅ በሆነ መንገድ የሚያሳይ “አልፋ ኧርዝ ፋውንዴሸን” የተባለ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አስተዋውቋል።

አዲሱ ቴክኖሎጂ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ከዋሉት የአየር ላይ ምስል አቅራቢዎች የተሻለ ጥራት እንዳለውም ተገልጿል።

አዲሱ ሞዴል ምድርን በሚዞሩ ሳተላይቶች ላይ ብቻ ከመመርኮዝ ይልቅ መረጃዎችን ከሶስት ዲያሜንሽን (3D) ካርታዎች፣ ከሳተላይት ምስሎች እና ከራዳር ጋር በማጣመር ዝርዝር እና ወቅታዊ ካርታዎች ለመፍጠር ይጠቅማል ተብሏል።

ይህም በትሪሊዮን የሚቆጠሩ ምስሎችን አጣምሮ ዝርዝር መረጃዎችን በመፍጠር ሳይንቲስቶች የምድርን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በንቃት እንዲከታተሉ ይረዳል ሲል ኢሮ ኒውስ ዘግቧል።

እ.አ.አ. ከ2017 እስከ 2024 ያለውን መረጃ በመጠቀም በተደረገው የመጀመሪያ ሙከራ፣ አልፋ ኧርዝ ፋውንዴሸን ሌሎች የዲጂታል ካርታ ሞዴሎችን የሚሰሩትን ስህተት 24 በመቶ መቀነስ መቻሉን ጎግል አስታውቋል።

እንዲሁም "ከአልፋ ኧርዝ ፋውንዴሽን" የተገኘው መረጃ ከተመሳሳይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓቶች በጣም ያነሰ የማከማቻ ቦታን የሚጠይቅ ሲሆን ይህም መጠነ ሰፊ ትንታኔን የበለጠ ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳል ብሏል ኩባንያው።

ጎግል አዲስ ያስተዋወቀው ሞዴል ተመራማሪዎች የምግብ ዋስትና ሥራዎችን፣ የደን ጭፍጨፋን፣ የከተማ መስፋፋትን እና የውሃ ሀብት ለውጦችን እንዲያጠኑ ይረዳቸው ሲል ዘገባው አመላክቷል።

ይህ ብር ከማን ኪስ ውስጥ የወጣ ይመስላችኋል
12/08/2025

ይህ ብር ከማን ኪስ ውስጥ የወጣ ይመስላችኋል

እንድታውቁት
12/08/2025

እንድታውቁት

11/08/2025

(ዘ-ሐበሻ ዜና) "በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ክስ ተመስርቶበት ከሀገር እንዳይወጣ እግድ ተጥሎበታል" ተብሎ ሲነገር የነበረው ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል፣ ወደ አሜሪካ መመለሱን ወዳጆቹ ገለጸዋል። ይህ ክስተት፣ "ፖሊስ ፈልጌ አጣሁት" ያለው ግለሰብ እንዴት ከሀገር ሊወጣ ቻለ? የሚል ጥያቄን በማስነሳት፣ የህግ የበላይነትን ጉዳይ በድጋሚ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም.፣ ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ "ለኢየሱስ" የተሰኘ ታላቅ የመዝሙር ድግስ ካዘጋጀበት ዕለት ሁለት ቀን ቀደም ብሎ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የህግ ክፍል ኃላፊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

በመግለጫውም፣ ቤተክርስቲያኗ በፓስተሩ ላይ ክስ እንደመሰረተችና በዚህም መሰረት የፍርድ ቤት የማሰር ትዕዛዝና ከሀገር የመውጣት እግድ እንደተላለፈበት አስታውቀው ነበር። የሚገርመው ግን፣ የፌደራል ፖሊስ፣ በሺዎች ፊት መድረክ ላይ የነበረውን ፓስተር "ፈልጌ አጣሁት" ማለቱ፣ በወቅቱ ከፍተኛ መነጋገሪያን ፈጥሮ ነበር።

ከዚህ ሁሉ ውዝግብ ከአንድ ሳምንት በኋላ፣ ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል አሜሪካ ተመልሷል መባሉ፣ የብዙዎችን ግምት ወደ ሌላ አቅጣጫ ቀይሮታል።

አንድ ግለሰብ ላይ የፖሊስ የጉዞ እግድ አለ እየተባለ፣ እንዴት የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያን የኢሚግሬሽን ቁጥጥር አልፎ ሊወጣ ቻለ? የሚለው ጥያቄ በስፋት እየተነሳ ነው።

የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ይህ ክስተት በኢሚግሬሽንና በጸጥታ አካላት በኩል ከባድ የሆነ የኃላፊነት ጉድለት ወይም ሆን ተብሎ የተደረገ ማላላጥ መኖሩን ያሳያል።

"የፓስተሩ ከሀገር መውጣት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጀመረችው የህግ ሂደት ላይ ትልቅ እንቅፋት ከመፍጠሩም በላይ፣ በሀገሪቱ የፍትህ ስርዓት ተአማኒነት ላይ ጥቁር ጥላን አጥልቷል" ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

በጉዳዩ ላይ ከሚመለከታቸው የመንግስት የጸጥታ አካላት በኩል የተሰጠ ምንም አይነት ይፋዊ ማብራሪያ የለም።

አዲስ አበባ | ዋሽንግተን ዲሲ

የእስራኤል ኤምባሲ ፓስተሩ ላይ መግለጫ አወጣ!!ከእስራኤል ኤምባሲ በኢትዮጵያ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡2/12/2017 ዓ.ምሰሞኑን በማሕበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው የፓስተር ቸርነት በ...
09/08/2025

የእስራኤል ኤምባሲ ፓስተሩ ላይ መግለጫ አወጣ!!

ከእስራኤል ኤምባሲ በኢትዮጵያ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡
2/12/2017 ዓ.ም

ሰሞኑን በማሕበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የሚገኘው የፓስተር ቸርነት በላይ (ፓስተር ቸሬ) ፀረ-ሴማዊ ንግግር በአይሁድ ህዝብ ላይ ለዘመናት ከትውልድ ትውልድ እየተላለፈ የመጣውን የሀሰት ትርክት እንዲሁም ስም የማጥፋት ዘመቻ እና የውሸት ውንጀላ አካል ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ልጆችን መግደል የሚለው የሀሰት ንግግር እና የእስራኤላዊያንን እውነተኛ ማንነት መካድ ከጥላቻ የመነጨ ነው፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ አብዛኛውን ጊዜ በተፅኖ ፈጣሪዎች እና በሀይማኖት አባቶች የሚሰነዘር እንደዚህ አይነት የጥላቻ ንግግሮች ከንግግር አልፈው አመጽ መቀስቀስ እንደሚችሉም አይተናል ፡፡ የእስራኤል ህዝብ ጥንታዊ ማንነቱና ባህሉ እንዲሁም ርስቱ እና ታሪኩ የሚመነጨው ፓስተር ቸርነት እወክለዋለሁ ብለው ከሚጠቅሱት ከመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡

ሀገረ እስራኤል እና መንግስቷ ዘርን ለማጥፋት ሽብርተኝነትን ከሚያውጁ በመካከለኛው ምስራቅ እና አለምን ለማተራመስ ከሚንቀሳቀሱ የሁከት ሃይሎች የመኖር ህልውናዋን የማረጋገጥ እና ዜጎቿን ከክፉ ነገር ሁሉ የመጠበቅ ብሎም የመከላከል ግዴታዋን እየተወጣች ትቀጥላለች።

እስራኤል የአይሁድ ህዝብ እና ዲሞክራሲ የሰፈነባት አገር ስትሆን የሁሉንም ማሕበረሰብ የማምለክ ነጻነት የምታከብር እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ የክርስቲያን ማሕበረሰብ እያደገ የመጣባት ብቸኛ አገር ናት፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤምባሲ የተናጋሪው ማንነት ማንም ይሁን ማን ፀረ-ሴማዊ የጥላቻ ንግግርን እስካስተላለፈ ድረስ መቃወሙን ይቀጥላል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ለሽብርተኝነት እጃችንን እንድንሰጥ ለማስገደድ በእስራኤል ላይ እየተነዛ ያለውን መሰረት የሌለው የውሸት ዘመቻን መቃወማችንን እንቀጥላለን፡፡

እስካሁን ድረስ ጋዛ ውስጥ በሃማስ ታግተው ለሚገኙት 50 የሚሆኑ ዜጎቻችን በሰላም እንዲመለሱ እና መጪው ዘመን ለህዝባችን ሰላምን እና ደህንነትን የሚያረጋገጥ እንዲሆን መስራታችንንና መጸለያችንን እንቀጥላለን፡፡

© Israel in Ethiopia

Ethiopia🇪🇹 southwest region Dawro zone capital city  Tercha!
09/08/2025

Ethiopia🇪🇹 southwest region Dawro zone capital city Tercha!

አሳዛኝ ዜና ❗️                             የደብረ ብርሃን ከተማ ምክር ቤት ኢኮኖሚና በጀት ቋሚ ኮሜቴ ሰብሳቢ  አቶ የኔአንተ አለኸኝ   በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ በትናን...
08/08/2025

አሳዛኝ ዜና ❗️

የደብረ ብርሃን ከተማ ምክር ቤት ኢኮኖሚና በጀት ቋሚ ኮሜቴ ሰብሳቢ አቶ የኔአንተ አለኸኝ በመኖሪያ ቤታቸው በር ላይ በትናንትናው እለት በቀን (30 ) 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 12:30 አካባቢ በጥይት ተመተው እንደተገደሉ ምንጮቻችን ገልፀዋል።

የምክር ቤት አባሉ አቶ የኔአንተ አለኸኝ ጠንካራና ሞጋች ከሚባሉ የከተማዋ የምክርቤት ሰዎች መካከል አንደኛው እንደሆኑም የሚያውቋቸው የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ።

ነፍስ ይማር!

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Push Page posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category