About Ethiopia

About Ethiopia ስለ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ፡ባህል ፡ትውፊት ፡ቅርስ ፡መልከአምድር እያወቅን የምንማማርበት ገፅ ነዉ ስለ ኢትዮጵያውያን ታሪክ ፡ባህል ፡ትውፊት ፡ቅርስ ፡መልከአምድር የምንማማርበት እና የምናዉቅበት ገፅ ነዉ

እንኳን ለ130ኛው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው ለአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!ዛሬ አድዋን ስናከብር ታሪኩን በማውሳት ብቻ መሆን የለበትም። ዛሬ በሀገራችን ያለው ሞት፣ መፈናቀልና የ...
02/03/2026

እንኳን ለ130ኛው የጥቁር ህዝቦች ኩራት ለሆነው ለአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ዛሬ አድዋን ስናከብር ታሪኩን በማውሳት ብቻ መሆን የለበትም። ዛሬ በሀገራችን ያለው ሞት፣ መፈናቀልና የእርስ በእርስ ግጭት የአባቶቻችንን መስዋዕትነት የሚፈታተን እውነታ ነው። አድዋ ያስተማረን ጠላትን በጦር ማሸነፍን ብቻ ሳይሆን፣ ከውስጥ የሚበላን መከፋፈልን አሸንፎ ለአንድ ዓላማ መቆምን ነው።

ዛሬም እንደ ትላንቱ፦

የጥላቻ ግንብ ፈርሶ የፍቅር ድልድይ የሚገነባበት፣

የዜጎች መፈናቀል አብቅቶ ሁሉም በሀገሩ በሰላም የሚኖርበት፣

ጦርነት በውይይት ተተክቶ የሰው ሕይወት ክብር የሚሰጠው አድዋን ልንደግመው ይገባል።

የዘንድሮው አድዋ የቁጭት ሳይሆን የይቅርታ፣ የጦርነት ሳይሆን የሰላም፣ የመፈናቀል ሳይሆን የመተቃቀፍ ድል ይሁንልን።

ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን! ሰላም ለኢትዮጵያ

#ዓድዋ
#130
!

አድዋን ማክበር ማለት የሰው ልጅን ክብር ማክበር ነው። የሰው ሕይወት የሚቀጠፍባት ሳይሆን የሚከበርባት፣ ዜጎች የሚፈናቀሉባት ሳይሆን የሚጠለሉባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል የምንገባበት ቀን ...
02/03/2026

አድዋን ማክበር ማለት የሰው ልጅን ክብር ማክበር ነው። የሰው ሕይወት የሚቀጠፍባት ሳይሆን የሚከበርባት፣ ዜጎች የሚፈናቀሉባት ሳይሆን የሚጠለሉባት ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል የምንገባበት ቀን ይሁን።

ለሞቱት ወገኖቻችን እረፍትን፣ ለተፈናቀሉት መጽናናትን፣ ለሀገራችን ደግሞ ዘላቂ ሰላምን ፈጣሪ ያድለን🙏

#130

አገር ስትሰራ አባት ላዋጣችሁ የጀግና ልጆች ክብር ይሁን!!እንኳን ለ47ኛው ዓመት የካራማራ ድል በዓል አደረሳችሁ!!  Yared ShumeteYared Shumete - ያሬድ ሹመቴያሬድ ሹመቴ
05/03/2025

አገር ስትሰራ አባት ላዋጣችሁ የጀግና ልጆች
ክብር ይሁን!!

እንኳን ለ47ኛው ዓመት የካራማራ ድል በዓል አደረሳችሁ!!



Yared ShumeteYared Shumete - ያሬድ ሹመቴያሬድ ሹመቴ

01/03/2025

በቀደምት ጀግኖች አያቶቻችን ታላቅ ተጋድሎ እና መስዋዕትነት እንዲሁም በታላቁ ታሪክ የማይረሳው ንጉሳችን ዳግማዊ አጤ ምንሊክ እና በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ብልህ አመራር እና አስተባባሪነት ለተቀዳጀነው አንፀባራቂው የ፻፳ ወ፱ኛው የአድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን ሳስተላልፍ በታላቅ ብሔራዊ ኩራት ነው::

ይህ በታሪክ ተመዝግቦ በየአመቱ የምንዘክረው አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የኢትዮጵያን ነፃነት ያስከበረ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ቀንበር ተጭኗቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ አፍሪካዊያን ወንድም እና እህቶቻችን እንዲሁም በመላው አለም በጭቆና ውስጥ የነበሩትን ጥቁር ህዝቦች ቀና ብለው እንዲሄዱ እና ነፃ እንዲወጡ በወቅቱ ታላቅ መነቃቃትን የፈጠረ ገናና የጥቁር ህዝቦች ድል ነው።

የዘንድሮውን የ፻፳ ወ፱ ኛው የአድዋ ድል በአል ስናከብር ሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ቀላል ለማይባሉ አመታት አንድነቷን አስጠብቃ ወደ ፊት እንዳትራመድ ሰቅዞ የያዛትን ተከታታይ የብሔር ፖለቲካ አዙሪት እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ያስከፈለንን እና እያስከፈለን ያለውን ዋጋ ግምት ውስጥ በማስገባት ካለንበት ውስብስብ እና እጅግ ኋላቀር የዘር ፖለቲካ ለመውጣት ከመቼውም ጊዜ በላቀ አንድነታችንን አስተባብረን የህልውናችን መሰረት የሆነችው እናት ሀገራችንን ለማዳን በንቃት መቆም ይጠበቅብናል።



ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

ለመላው የጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው ለታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዐል እንኳን አደረሳችሁ🙏«በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ። እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ሰዎች ...
01/03/2025

ለመላው የጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው ለታላቁ የአድዋ ድል መታሰቢያ በዐል እንኳን አደረሳችሁ🙏

«በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ። እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ሰዎች ደም በከንቱ መስፈሱን እያየሁ ድል አደረግሁ ብዬ ደስ አላለኝም» ዳግማዊ ምኒልክ ለአውሮፓዊው ዲፕሎማት ሙሴ ሸፍኔ በመጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤያቸው ከገለጹት

#ዓድዋ
#129

💚💛❤️ወንዲ ማክ -ካራማራ💚💛❤ብስራት ገድልሽ ተሰማ የድልሽ ዜናፈጣሪ ትቶ ማይተውሽ ሀገር ሆንሽናእንደ አሊ በርኬታንክ ማርኬለሀገሬ መሰዋት ነው ልኬበምስራቅ ሊከበው ገፎ ቀለሙንየአንድነትሽን ...
05/03/2024

💚💛❤️ወንዲ ማክ -ካራማራ💚💛❤

ብስራት ገድልሽ ተሰማ የድልሽ ዜና
ፈጣሪ ትቶ ማይተውሽ ሀገር ሆንሽና
እንደ አሊ በርኬ
ታንክ ማርኬ
ለሀገሬ መሰዋት ነው ልኬ

በምስራቅ ሊከበው ገፎ ቀለሙን
የአንድነትሽን ምስጢር ባያውቀው ውሉን
የሳሳሽ ቢመስለው የጎደልሽ ሀገሬ
ጦሩን ሰበቀብሽ በእብሪት ዚያድባሬ

ያ ዚያድ ባሬ ምን አለ
ካርታ እስከ አዋሽ ላይ የሳለ
እሱማ ቆርጦ ከመጣ
ሀገር ጠርታለች ና ውጣ

ካራማራ ካራማራ
ካራማራ ካራማራ

አብሮ መኖር በፍቅር አንጂ ጥቃት የማይለምደው
ዳርሽን ሲነኩት መሀሉ ሚነደው
ሀገር ተወረረች ብሎ እንቅልፍ ባይወስደው
ጀግናው ልጅሽ ወጣ ልክሽን ሊያስለካው

ታጠቅ ከተመ ታጠቅ ከተመ
ሚኒሻው ገባ ለሀገር ተመመ
ታጠቅ ከተመ ታጠቅ ከተመ
ገበሬው ገባ ለሀገር ተመመ

በሰኔ 18 ሸገር ተማምሎ
ወጥቶአደርሽ ወጣ ሰልፉን አስተካክሎ
የእናት የእህት ስንቁን በአገልግል ሸክፎ
በምስራቅ ተገኘ ወኔውን ታቅፎ

በገስጥ መድፈኛው ፋፈምና ቆሬ
መንግስቱ ሀይለማርያም ዘመተ ለሀገሬ
ከቀየው ቢርቅም የሰራውን ሰርቶ
ሀገር በማዳኑ አይረሳም ከቶ

ያ ዚያድ ባሬ ምን አለ
ካርታ እስከ አዋሽ ላይ የሳለ
እሱማ ቆርጦ ከመጣ
ሀገር ጠርታለች ና ውጣ

ካራማራ ካራማራ
ካራማራ ካራማራ

በሰማይ ተናንቆ የአየርሀይሉ ጀግና
ጀቱን አዘነበው በረዶ አረገና
ሐረር ብትከበብ ድሬንም ቢጨንቃት
ለገሠ ተፈራ አርነት አወጣት

በብረቱ ፍጭት በሳንጃው መቃደድ
በታንኩ ጉምጉምታ ቢዘጋበት መንገድ
ማለፊያ ቢያሳጣ ለወገን ቸግሮ
ላንቃውን አዘጋው የመድፉን ጉሮሮ

ያ ዚያድ ባሬ ምን አለ
ካርታ እስከ አዋሽ ላይ የሳለ
እሱማ ቆርጦ ከመጣ
ሀገር ጠርታለች ና ውጣ

ካራማራን ቋጥሮ ጠላት ቢያስጨንቃት
ኢትዮጵያዊው ወድቆ ኦጋዴንን ፈታት
ያ ፊደል ካስትሮ ያገር ባለውለታ
ወጥቶአደሩን ልኮ ግቡም ድሉን መታ

ሁሉን ፈጥኖ ደራሽ ያ ድንበር ጠባቂ
ለነፍሱ ሳይሳሳ ለሀገር ወዳቂ
ከፍታው ጨምሯል ተራራውን ለኩት
ግርማው ካራ ማራ በሰው ልጆች አጥንት





!

እንኳን ለ46ኛው የካራማራ ድል በዐል በሰላም አደረሳችሁ💚💛❤️  “ታላቋ ሶማሊያን” እውን በማድረግ ቅዠት የተለከፉት የሶማሊያ መሪ ዚያድ ባሬ በ1969ዓ.ም በምሥራቅ ኢትዮጵያ 700 ኪሎ ሜት...
05/03/2024

እንኳን ለ46ኛው የካራማራ ድል በዐል በሰላም አደረሳችሁ💚💛❤️




“ታላቋ ሶማሊያን” እውን በማድረግ ቅዠት የተለከፉት የሶማሊያ መሪ ዚያድ ባሬ በ1969ዓ.ም በምሥራቅ ኢትዮጵያ 700 ኪሎ ሜትር ድረስ ዘልቀው በመግባት ኢትዮጵያን ወራ ነበር።ኢትዮጵያውያን ካራማራ ተራራ አካበቢ በእልህ አስጨራሽ ውጊያ፣ ድል ያደረጉበት መታሰቢያ ቀን በነገው እለት በኢትዮ_ኩባ ፓርክ በድምቀት ይከበራል፡፡

ጄኔራል ዚያድ ባሬ በ1969 ኢትዮጵያን ለመውረር ሲወስን አንዱ ገፊ ምክንያት፣ ኢትዮጵያውያን በወቅቱ በውስጣዊ ፖለቲካ ተከፋፍለው መገኘታቸው ነበር፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያን ሲያስተዳድር የነበረው የደርግ መንግስትም ሀገሪቱን ከተቆጣጠረ የሦስት ዓመት ዕድሜ የነበረውና በውስጣዊ የፖለቲካ ክፍፍልም በከፍተኛ ደረጃ ተወጥሮ የነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ዚያድ ባሬ በአሜሪካን ታግዞ በወቅቱ መፍጠር ከቻለው የጦር አቅም አንጻር ድል እንደሚያደርግ ተማምኖ ነበር የመጣው፡፡

የወቅቱ የኢትዮጵያ ሶሻሊስት መሪዎች ተጨማሪ ለሦስት ወራት 300 ሺህ ሚሊሺያ በወቅቱ አጠራር (ሕዝባዊ ሠራዊት) በማሰልጠን ከመደበኛው ጦር ጋር በአብዮት አደባባይ ታላቅ ሠልፍ በማዘጋጀት ካስተዋወቁ በኋላ ከጠላት ጋር ተፋለሙ፡፡ የሶማሊያ ጦር የቆሬን የመከላከያ ቀጣና በጎን በማለፍ በጃርሶና ኮምቦልቻ በኩል አድርጎ ድሬዳዋን፣ በፌዲስና ሐኪም ጋራ በኩል ሐረርን ለመያዝ ታኅሣስ 15 ቀን 1970 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍተኛ ማጥቃት ቢያደርግም ጀግኖቹ ኢትዮጵያውያን ወደ ሐረር በመገስገስ ላይ የነበረውን ፌዲስ ላይ፣ ድሬዳዋን ለመያዝ በመገስገስ ላይ የነበረውን ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካው አካባቢ ሁለት ከፍተኛ የመልሶ ማጥቃት ዘመቻዎችን በማካሄድ ጠላትን አይቀጡ ቅጣት ቀጡ፡፡

ኢትዮጵያ በታሪክ እጅ እንድትሰጥ እና ታሪኳ እንዲበላሽ ሲያሴሩ የኖሩት የኔቶ አባል ሀገራት እና ግብጽ ለሶማሊያው ዚያድባሬ እገዛ በማድረግ ሉዓላዊት
ኢትዮጵያን ለማስደፈር እና በእጃቸው መዳፍ ለማድረግ ያልቆፈሩት ጉድጓድ አልነበረም፤ ሳይሳካ ተሸንፈው ማቅ ለበሱ እንጅ፡፡በመጨረሻም የአባቶቻቸውን ታሪክ በማደስ ጀግንነታቸውን ያደሱት ኢትዮጵያውያን አብዛኛውን ምሥራቃዊ ደጋ ክፍል ነፃ በማውጣት የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም እጅግ ‹‹ስትራቴጂካዊ››
የሆነውን የካራማራን ኮረብታና አካባቢ ከወራሪው ጠላት በከፍተኛ መስዋትነት አስለቀቁ፡፡ የካቲት 27 ቀን 1970 ዓ.ም የጅግጅጋ ከተማና አካባቢዋን በቁጥጥር ስር አውለው ሰንደቅ ዓላማቸውን በነፃነት እና በኩራት ዳግም እንድትውለበለብ አደረጉ፡፡

በዚህ ጦርነት ከ60,000 በላይ ኢትዮጵያውያን የተሰው ሲሆን በዓሉ ብሔራዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር የተለያዩ ወገኖች እስካሁን ጥያቄ እያቀረቡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

ዓለምን የለወጡ 3 (ሦስት) ክስተቶች!========================በአንድ ወቅት የታሪክ ፕሮፌሰሩ ዶ/ር አልማው ክፍሌ ጽሑፍ ያቀረቡበትን መድረክ የመታደም ዕድል አግኝቼ ነበር። እና...
02/03/2024

ዓለምን የለወጡ 3 (ሦስት) ክስተቶች!
========================
በአንድ ወቅት የታሪክ ፕሮፌሰሩ ዶ/ር አልማው ክፍሌ ጽሑፍ ያቀረቡበትን መድረክ የመታደም ዕድል አግኝቼ ነበር። እናም አንድ የተናገሩትን ነገር እስካሁን አስታውሳለሁ። ዶ/ር አልማው እንዳሉት በደቡብ አፍሪካ የሚገኝን አንድ ትልቅ ሙዚየም ሲጎበኙ በሙዚየሙ ውስጥ ትኩረታቸውን የሳበው ''ዓለምን የቀየሩ ሦስት ክስተቶች'' በሚል በጉልህ የተፃፈው ነገር ነበር።

1ኛ. እሳት (Fire)
2ኛ. የኢንደስትሪ አብዮት (Industrial Revolution)
3ኛ. የአድዋ ድል (The Victory of Adwa) 😍❤️

ይህ ቅደም ተከተል የጊዜ እንጂ የደረጃ አይደለም። እሳት (400 ሺህ ዓመት ገደማ)፣ ኢንደስትሪ አብዮት (260 ዓመታት ገደማ) እንዲሁም የአድዋ ድል (128 ዓመት)

ተ.ቁ. 3 ባለቤት አለው። ባለቤቱም ባለድሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። መሪ ንጉሡም ዳግማዊ አፄ ምኒልክ (እምዬ) ይባላሉ። ለዛሬ ነፃነት ላበቁን ሰማዕት ለሆኑም፣ በጦርነቱ ለተሳተፉም፣ ለመሪውም ዘላለማዊ ክብር! 🙏

መልካም የአድዋ ድል በዓል!

(በድጋሚ የተፖሰተ)
©️Hawlet Ahmed

  ድል!!‹‹የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈ...
02/03/2024

ድል!!

‹‹የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ!››
ዳግማዊ አፄ ምኒልክ
እምዬ ምኒልክ
..ምኒልክ ምንጊዜም ከማይረሱት ልማዳቸው አንዱ፣ ሠራዊታቸው ምግብ ሳይበላ እሳቸው አይበሉም ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ከደጃች ውቤ ቤት ተጋብዘው ሄዱ፡፡ ደጃች ውቤም አማታቸውን ምኒልክን ከተቀበሉ በኋላ ወደቤት እንዲገቡ ቢጠይቋቸው፣“በፊት አሽከሮቼን አስገባና አብላልኝ” ብለው እምቢ አሉ፡፡አሽከሮቹ ለግብር ሲገቡ የምኒልክንና የየመኳንንቱን በቅሎዎች የያዙ አሽከሮች ቀሩ፡፡ ይህን ያዩት ምኒልክ በቅሎአቸውን “ወዲህ አምጣት” ሲሉ፣ አሽከሮች እየሮጡ በቅሎአቸውን አቀረቡላቸው፡፡አብረዋቸው ያሉት መኳንንት፣ “ወዴት ሊሄዱ ነው?” እያሉ ሲጠይቁ ምኒልክ የበቅሎዋን መሳቢያ ለኮ ከአሽከራቸው ተቀብለው፣ “ሂድ ግባና ምሳህን ብላ” አሉት፡፡ ሁሉም ደነገጡ፡፡ ምኒልክም አሽከሮቻቸውን ተቈጥተው ወደ ግብር እንዲገቡ ሲያደርጉ፣ እፊታቸው የነበሩት ጸሓፌ ትእዛዝ ገብረሥላሴ ከምኒልክ እጅ በቅሎዋን ለመቀበል፣ “ይስጡኝ እኔ ልያዛት” አሏቸው፡፡ ምኒልክም፣ “የኔን ተውልኝና ያንተን ካንተ አሽከር ተቀበል” አሏቸው፡፡ ከዚህ በኋላ መኳንንቱ ሁሉ ከአሽከሩ በቅሎውን እየተቀበለ ሲይዝ አሽከር ምሳውን ሊበላ ወደ ግብር ገባ፡፡ ምኒልክ ከአንዲት የኮክ ዛፍ ሥር በቅሎአቸውን ይዘው ቆመው አሽከሮቻቸው በልተው እስቲወጡ ድረስ ጠጅ እየጠጡ ይጠብቁ ጀመር፡፡

“እምዬ ምኒልክ” የሚለውን ስም እንደ ኖሩት ይህ አንድ ማረጋገጫ መሆን ይችላል፡፡
----
ጳውሎስ ኞኞ፤አጤ ምኒልክ፣ ገጽ 434



#128ኛ

ለመላው የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ቀንዲል ለሆነው  128ኛው   መታሰቢያ በዐል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!💚💛❤️ #የምንሊክን  አዋጅ ሰምተው   እምቢኝ ብለው ለአደን እንኳን የማይበቃ ጥንታ...
02/03/2024

ለመላው የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ቀንዲል ለሆነው 128ኛው መታሰቢያ በዐል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!
💚💛❤️
#የምንሊክን አዋጅ ሰምተው እምቢኝ ብለው ለአደን እንኳን የማይበቃ ጥንታዊ መሳሪያቸውን አንግበው ወደ አድዋ የዘመቱ፣ለሀገራቸው ነፃነት ሲሉ ሰይፈውና ተሰይፈው ወድቀው ያቆሙንን ብዙ ሺ የአድዋ ዘማቾች እናመሰግናለን እንዘክራለን፡፡
እናንተ የሀገሬ አንገታችሁን ሰጥታችሁ እንድናቀና አርጋችሁናልና እናመሰግናለን፤ እናንተ እኛን በነፃነት እናከብራቹሀለን እንዘክራቹሀለን🙏

ዘላለማዊ ክብር እቺን ነፃ ሀገር ላስረከቡን የአድዋ ዘማች ሰማዕታት!!!!!
"ነፃነቴን...... ስጡኝ ወይም.................... ሞቴን"
አ..................ድ..............................ዋ
#ዓድዋ

#1888
#128ኛ


#ነፃነት
#ኩራት

📷ምስሎቹ ከ2 አመት በፊት በሚኒሊክ አደባባይ እና አድዋ ድልድይ አካባቢ የተነሱ ናቸው።

ዋ! አድዋ!(ሎሬት ፀጋዬ ገ /መድኅን)ዋ!…አድዋ ሩቅዋየዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥጉዋሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋአድዋ …በአንቺ ብቻ ህልዉናበትዝታሽ ብፅዕናበመስዋዕት ክንድሽ ዜናአበው ታደሙ እንደገ...
01/03/2024

ዋ! አድዋ!
(ሎሬት ፀጋዬ ገ /መድኅን)
ዋ!…
አድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ የአድማስ ጥጉዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
አድዋ …
በአንቺ ብቻ ህልዉና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና …
ዋ !
አድዋ የዘር አፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነቱዋ
በሞት ከባርነት ስርየት
በደም ለነፃነት ስለት
አበው የተሰውብሽ እለት
አድዋ …
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
አድዋ ..
የኩሩ ደም ባንቺ ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
አፅምሽ በትንሳዔ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ህዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሳኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘዉ መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው በለው በለው በለው
ዋ …አድዋ !…
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጎራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ በለው በለው
ዋ …አድዋ …
አድዋ የትናንትናዋ
ይኸው ባንቺ ህልውና
በትዝታሽ ብፅዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና::
(ከሎሬት ፀጋዬ ገ /መድኅን፣ የእሳት ወይ አበባ መድብል የተወሰደ፡፡)

#ዓድዋ
#128ኛ


#ነፃነት
#ኩራት

ለሀገሩ መሞት ለሀበሻ ጌጡ ነው!! 💚💛❤️"እኔ ሴት ነኝ ሰላም እንጂ ጦርነትን አልወድም። ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን/እመርጣለሁ። ሂድ መንገዱን ...
01/03/2024

ለሀገሩ መሞት ለሀበሻ ጌጡ ነው!!
💚💛❤️

"እኔ ሴት ነኝ ሰላም እንጂ ጦርነትን አልወድም። ነገር ግን ሀገሬ እንደዚህ ያለ ክብር የሚነካ ዘለፋ ከምትሸከም ጦርነትን/እመርጣለሁ። ሂድ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ፡፡

እግሩን ለጠጠር፣ ደረቱን ለጦር አስጥቶ፣ ደሙን ለሀገሩ ፍቅር አፍስሶ፣ለአፈሩ፤ ክብር ለብሶ፣ ወድቆ ሀገሩን የማያቆም እዚህ ያለ እንዳይመስልህ፡፡ ሂድ! የኢትዮጵያን ሰው ባታውቀው ነው፡፡ ለሀገሩ መሞት ማለት ለሀበሻ ጌጡ ነው። ሂድ! ባሻህ ጊዜ ተመለስ፤ ተሰናድተን እንጠብቅሀለን። ያንተን ወንድነት፣የጣይቱንም ሴትነት ያን ጊዜ እናየዋለን፡፡ ሂድ! መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ"

#ዓድዋ
#128ኛ


#ነፃነት
#ኩራት

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when About Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to About Ethiopia:

Share