21/01/2026
ለማህበራዊ ፈተናዎች፣ ዘላቂ የፈጠራ መፍትሄዎች!
የጠብታ አምቡላንስ መስራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ክብረት አበበ እና መላው የጥቢታ አምቡላንስ አመራርና ሠራተኞች፤ የ2026 የሽዋብ ፋውንዴሽን የማህበራዊ ሥራ ፈጠራ (Schwab Foundation Award for Social Entrepreneurship) ተሸላሚ በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ!
ይህ ዓለም አቀፍ እውቅና፤ ማህበራዊ ችግሮችን በሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ለሚፈቱ ውጤታማ የተቋማት መሪዎች የሽዋብ ፋውንዴሽን ከዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ጋር በመተባበር የሚሰጥ ትልቅ ዓለም አቀፍ ሽልማት ነው። ክቡር አቶ ክብረት አበበ በዚህ ዓመት ከተመረጡት 21 ዓለም አቀፍ መሪዎች መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ በመድረኩም ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተሸላሚ በመሆን የአገራችንን የፈጠራ አቅም በዓለም አደባባይ አስመስክረዋል።
ይህ ስኬት፤ የኢትዮጵያ የሥራና ፈጠራ ሥነ-ምህዳር ፈተናዎችን ወደ ኢኮኖሚያዊ ዕድል በመቀየር ረገድ ያለውን አቅም በተግባር ያሳየ ነው። ይህም ለዜጎች ምቹ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው፣ አገር በቀል መፍትሄዎች አገራዊ ፍላጎትን ከመሸፈን አልፈው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ መሆን እንደሚችሉ ተጨባጭ ማሳያ ነው።
በድጋሚ ክቡር አቶ ክብረት አበበ እና መላው የሥራ ባልደረቦቻቸውን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህ ስኬት ለሌሎች ሥራ ፈጣሪዎች የብርታት ምንጭ እንደሚሆን እምነቴ የፀና ነው።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!