MoA Cooperative/ግብርና ሚኒስቴር ሸማቾች ማህበር

MoA Cooperative/ግብርና ሚኒስቴር ሸማቾች ማህበር This is used for help ministies employees

04/09/2026
ግብርና ሚ/ር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበር MOA COOPERATIVE ከኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽኑ እና ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር በመሆን በሸገር ሲቲ የችግኝ ...
24/08/2026

ግብርና ሚ/ር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበር MOA COOPERATIVE ከኢትዮጵያ ኅብረት ሥራ ኮሚሽኑ እና ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ጋር በመሆን በሸገር ሲቲ የችግኝ ተከላ መርሐግብር አካሄደ
****
ህብረት ሥራ ማህበሩ ዘንድሮ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በሃገር አቀፍ ደረጀ በተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ከኅብረት ሥራ ማኅበራት እና ከኮሚሽኑ አመራሮች እና ፈፃሚዎች ጋር በመሆን በሸገር ሲቲ ቡራዩ ክፍለ ከተማ ላይ ዛሬ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂዷል።
በመርሐግብሩም የኮሚሽኑ አመራሮች እና ፈፃሚዎች ፣ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች ፣ እንዲሁም 20 የቁጠባ እና ብድር እና 15 የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተሳትፈዋል።
በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብሩ ኮሚሽነር ጌትነት ታደሰ ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል። በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይም መልዕክት ያስተላለፉት ኮሚሽነር ጌትነት፣ ባለፉት 7 ዓመታት ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸውን የጠቆሙ ሲሆን ዘንድሮም ከ8 ቢሊዮን በላይ ችግኞች በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተተከሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑም ኅብረት ሥራ ማህበራትን በማስተባበር፣ ዘንድሮን ጨምሮ ለተከታታይ 7 ዓመታት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ላይ በመሳተፍ ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ የሆነች ሃገር ለማስረከብ በሚደረገው ታላቅ ሃገራዊ ተልዕኮ የበኩሉን ሚና ሲወጣ መቆየቱን ተናግረዋል።
አክለውም፣ የአረንጓዴ ልማት ጉዳይ ለኅብረት ሥራ ማህበራት ከሌሎች የልማት አጀንዳዎች ተለይቶ የሚታይ ጉዳይ አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል ያሉት ሲሆን ይህ የችግኝ ተከላ መርሐግብር የኅብረት ሥራ ባህል ሆኖ ሊቀጥል እንደሚገባ ጥሪ አስተላልፈዋል

መልካም እሁድ ግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች መልካም እርፍት ቀን  ቀን ይሁንልዎ! ህብረት ስራ ማህበር አድራሻችን📍ግብርና ሚኒስቴር ግብ ውስጥ 7 ወለል ማህበራዊ ገፃቻ...
26/07/2026

መልካም እሁድ
ግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች መልካም እርፍት ቀን ቀን ይሁንልዎ!
ህብረት ስራ ማህበር

አድራሻችን

📍ግብርና ሚኒስቴር ግብ ውስጥ 7 ወለል

ማህበራዊ ገፃቻችንን ይጎብኙ !

💻Website,Telegram, facebook,instagram, youtube, Tiktok

ለበለጠ መረጃ : +251999828384 +251999848586 ይደዉሉ!

22/07/2026
09/07/2026

wase:
የኅብረት ሥራ ማኅበር አመሰራረት እና የአባላት ተጠቃሚነት

(በኢትዮጵያ ሕግ ማእቀፍ)

መግቢያ
በዚህ ጹሁፍ የኢፊድሪ ህገመንግስት አንቀጽ 31መሠረት በማድረግ የህብረት ስራ ማህበር አዋጅ ቁጥር 985/2009 የወጣውን አላማ፣አመሰራረት እና ክርክር በተነሳ ጊዜ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ያለው አካል ማን እንደሆነ ለግንዛቤ ይረዳ ዘንድ በዚህ ጽሁፍ እናመላክታለን።

1. ህብረት ስራ ማህበር ምንድነው?

በአዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 2/1/ መሠረት ህበረት ስራ ማህበር ማለት ሰወች በተናጥል ሊያደርጓቸው ወይም ጥቅም ሊያገኙባቸው የማይችሏቸውን ጥቅም የሚገኝባቸውን ስራዎች በራሳቸው ፍላጎት ዲሞክርሲያዊ በሆነ መንገድ ገንዘበ፣እውቀት፣ሙያ፣ንብረታቸውን በማዋጣት የሚመሠርቱት ሀረጋዊ ሰውነት ያለው ማህበር ነው።

2. ስለ ህብረት ስራ ማህበር አመሠራረት

በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ሰባት መሠረት መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ቁጥራቸው ከሀምሳ የማያንስ ሆኖ በአንድ ክልል ላይ የተመሠረቱ ከሆነ በዚያው ክልል የሚመለከተው የማህበራት ማደራጃ የሚመዘገብ ሲሆን ከተለያየ ክልል የተወጣጡ አባላት ከሆኑ በፌደራል ደረጃ የሚመዘገቡ ናቸው። የሚመለከተው ባለስልጣን ክፍል የኢኮኖሚ ደረጃቸውንና አዋጪነታቸውን በመመልከት ቁጥራቸውን በተመለከተ ሊወስን የሚችል ሲሆን ነገር ግን ከአስር ሊያንስ አይችልም።

3. ከአላማቸው አንጻር ህብረት ስራ ማህበር አይነቶች

በዚህ አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 8 መሠረት ሶስት አይነት የህበረት ስራ ማህበሮች አሉ።
3.1 የመጀመሪያው ምርት የሚያመርት የህብረት ስራ ማህበር ሲሆን በዚህ ማህበር ምርት እያመረቱ የሚጠቀሙበት ነው።

3.2 ሁለተኛው አገልገሎት የሚሰጥ የማህበር አይነት ነው

ይህ የህብረት ስራ ማህበር አይነት አገልግሎት በመሰጠት ማህበሩና አባላቱ የሚጠቀምበት ነው።
3.3 ሶስተኛው ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበር ነው
ይህ ማህበር አገልግሎቶ በመስጠትም ሆነ ምርት በማምረት ጥቅም የሚያገኝ ማህበር ነው። ከዚህ የተነሳ አባላቱ በመተዳደሪያ ደንባቸው መሠረት ጥቅም የሚያገኝበት ነው።

ከእነዚህ ሶስቱ በአንዱ አይነት ማህበር ሲመሠረት በአከባቢው ላይ ሀብት የሚገኝበት የምስረታ አይነት የቱ እንደሆነ በጥናት መለየቱ እጅግ አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ አባላቱ የሚያቋቁሙት ማህበር የማህበረሰቡን ሞራል ወይም ህግ ሊቃረን አይገባም።

4. የህብረት ስራ ማህበር ምዝገባ

የህበረት ስራ ማህበር ሲመዘገብ ማመልከቻውን ከመተዳደሪያ ደንብ፣ የመስራቾች ቀላ ጉባኤ፣ የህብረት ስራ አመራር ኮምቴ፣ቁጥጥር ኮሚቴ ስምና አድራሻ፣ፊርማ የህብረት ስራ ማህበር አባላቱ ብቁነት መግለጫ፣ ማህበሩ ከመሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር በላይ ሲሆን የአባላቱን ስም አድራሻ ፊርማ ከሶስት እስከ አምስት ድረስ የስራ እቅድ ፥የመነሻ ካፒታሉ የገንዘብ መጠን በባንክ ወይም ባንክ በሌለበት ቦታ ከሆነ የፋይናንስ ተቋም በማስቀመጥ ለዚህ ሰነድ ማረጋገጫ፣ የህብረት ስራ ማህበሩ የሚሰራበት ቦታ መግለጫ እንዲሁም በዚህ አወጅ የሚወጡ ደንብ ወይም መመርያ የሚወሰኑ መግለጫዎች ጨምሮ ተያይዞ ስልጣን ባለው አካል የሚቀርብ ሲሆን ይህ አካል አረጋግጦ ትክክለኝነቱን ካረጋገጠ በኋላ በአምስት ቀናት ውስጥ የምስክር ወረቀቱን ይሰጣል።

5. ከአባላት ቁጥር፣ እና ውህደት አንጻር የሚመሰረት የህብረት ስራ ማህበር አይነት

5.1 መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበር
ይህ ቢያንስ አነስተኛውን አባላት የያዘ የህብረት ስራ ማህበር የያዘ ነው።

5.2 የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን

ይህ ሁለት ተመሳሳይ አላማ ያላቸው ህብረት ስራ ማህበር በመዋሀድ የሚፈጠር ማህበር ነው። አንቀጽ 2/2/

5.3 የህብረት ስራ ማህበራት ፌድሬሽን

ሁለት ተመሳሳይ የህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ሲዋሀዱ የሚመሰረት ነው

6. ሌላው መታወቅ ያለበት አነስተኛው የህብረት ስራ ማህበራት አባል ቁጥር ነው

ይህ አነስተኛው ቁጥር መሠረታዊው/በዋናነት የሚታወቀው/ 50 ሲሆን አባላቱ አቅማቸውን በማየት የሚመለከተው ክፍል በመመሪያ የሚወስን ሲሆን ከአስር ግን አይወርድም።

ስለዚህ አነስተኛው በህግ 50 ሲሆን የሚመለከተው ክፍል በመመሪያ የሚወስን ሲሆን እንደ አባላቱ አቅም ታይቶ ከአስር ዝቅ አይልም።

7.1 አለመግባባት ሲፈጠር እርቅ/62/ ወይም በግልግል ዳኝነት/64/ የሚታይበት ሁኔታ....

አለመግባባት በተፈጠረ ጊዜ በመጀመሪያ ጉዳዩን በእርቅ ለመፍታት ጥረት ተደርጎ እርቁ ቀጥታ ተፈጻሚሲሆን ይግባኝ አይጠየቅበትም። በእርቁ ስነስረአት ሁለቱ አንድ አንድ ወገን ተመርጦ ሶስተኛ የመሀል ዳኛ ሁለቱም ወገን በስምምነት ይመርጣሉ። ሶስተኛውን የመሀሉን ለመምረጥ ካልተስማሙ በሚመለከተው ክፍል እንዲመረጥ ይደረገል።

በዚህ በእርቁ ለመስተናገድ ካልተስማሙ ግን በግልግል ዳኝነት እያንዳንዱ ወገን አንድ አንድ መርጦ የመሀል ዳኛ በስምምነት ወይም በፍርድ ቤት እንዲመረጥ ተደርጎ በፍ/ስ/ስ/ህግ መሠረት ክስ መልስ ክርክር ተደርጎ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ይህ በፍርድ ቤት በአፈጻጸም የሚፈጸም ይሆናል። በዚህ በግልግል ዳኝነት ውሳኔ ቅር የተሰኘ ወገን በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ የሚጠይቅበት ነው።

7.2 በግልግል ዳኝነት/በሽምግልና/ በአንቀጽ 64 መሠረት አለመግባባት ሲፈጠር ሊታዩ የሚችሉ ጉዳዮች...

አለመግባባቱ በአባላት መካከል፣በቀድሞ አባለትና በአሁን አባላት መካከል፣ በአባላትና በአመራር መካከል፣በአባላትና፣ በአባላት በወራሾች መካከል፣በቀድሞ አባላትና በአባላት ወራሾች መካከል፣ በአባላት/በቀድሞ አባላት ወራሾች/በአመራር እና በአባላት/በቀድሞ አባላት ወራሾች/በአመራር መካከል ሲሆን እንዲሁም አንድ ህብረት ስራ ማህበር ከሌላ ማናቸውም ህበረት ስራ ማህበር ጋር አለመግባባት ሲፈጠር በግልግል ዳኝነት/በሽምግልና/ በአንቀጽ 64 መሠረት የሚታይ ይሆናል።

8. ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን ጉዳይ ለማየት ስልጣን የሌለው ስለመሆኑ

በፍ/ስ/ስ/ህግ ቀጥር 9 እና 244/2/ሀ/ መሠረት ጉዳዩን ተቀበሎ ለማየት ስልጣን የሌለው ሲሆን ጉዳዩን ተቀብሎ ለማየት ስልጣን ያለው በእርቅ ለማየት በተመረጡ ሶስት ሰወች በዚህ ሳይሆን ሲቀር በግልግል ዳኝነት ጉባኤ ነው። ይሁን እንጂ በአንቀጽ 67 መሠረት በእርቅም ሆነ በሽምግግልና/ግልግል ዳኝነት/ እንዲታይ ያልተስማሙ ከሆነ የመደበኛው ፍርድ ቤት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አለው።

9.. የህብረት ስራ ማህበሩ ክርክሩ በተራ ቁጥር 7 ላይ ከተጠቀሱት ውጭ ሲሆንስ

የህብረት ስራ ማህበሩ ከሌላ ራሱን ከቻለ ህጋዊ ሰውነት ካለው አካል ጋር የዳኝነት ክርክር ሲኖረው በእርቅ ወይም በግልግል ዳኝነት ሳይሆን በመደበኛ ፍርድ ቤት የሚታይ ይሆናል።

10. የህብረት ስራ ማህበር የዳኝነት ታሪፍ
የህብረት ስራ ማህበር በሶስቱም አይነቶች በፍርድቤት ለሚያደርገው ክርክር ለመንግስት ከሚከፈል የታሪፍ ክፍያ ነጻ ነው።

10. የሕግ ምክር

የህብረት ስራ ማህበር ሰወች በተናጠል ችግራቸውን ለመፈታት አቅም ባነሳቸው ጊዜ በአንድነት በመሆን ቁጥራቸው ቢያንስ 50 በሚመለከተው ባለለስልጣን የአባላቱ ቁጥር ከአቅማቸው አንጻር በመመሪያ ከአስር የማይወርድ ሆኖ አባለቱ እውቀት፣ገንዘብ፣ሀብት ፣፣ሙያቸውን በማዋጣት አቅም ፈጥረው በተሰማሩበት የህበረት ስራ ማህበር አይነት የሚጠቀሙበት ነው።
https://t.me/Fantahunlawyer
https://www.facebook.com/share/18HGFcU3G6/

የሕግ ማጣቀሻዎች

1. የኢፊድሪ ህገመንግስት አዋጅ ቁጥር 1/1987
2.የህብረት ስራ አዋጅ ቁጥር 985/2009
3. የህብረት ስራ ማህበራት አደረጃጀትና አሰራር ደንብ ቁጥር 170/2016
4. የህብረት ስራ ማህበራት አደረጃጀት መመሪያ ቁጥር 896/2014
5. የህብረት ስራ ማህበራት ኦዲት አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 978/2016
Fantahun Delelew 09291010371

የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት! (አዲስ አበባ፣  መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር) ግብርና ሚኒስቴር ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ጋ...
14/03/2026

የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት!

(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)

ግብርና ሚኒስቴር ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ጋር በመተባበር ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ባለሙዎች እና ለግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

ስልጠናው በንድፈ-ሃሳብና በተግባር የታገዘ ሲሆን የኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ አተገባበር፣ ስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርናን መሰረት ያደረገ የምግብ አዘገጃጀት እንዲሁም የምግብ ደህንነትና ጥራት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

አንድ ሰው በቀን ውስጥ ስድስቱን የምግብ ምድቦች ማለትም ብዕርና አገዳ/መደበኛ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋፅዖ እና ቅባት/ዘይት እንዲሁም በአንድ ገበታ ደግሞ አራት የምግብ ምድቦችን አካቶ መመገብ እንዳለበት በስልጠናው ተገልጿል፡፡

የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለማፍራት ሚናው የጎላ መሆኑንም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡

የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር ስምንተኛ(8ኛ) ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡(አዲስ አበባ፣ ጥር 30/2018 ዓ/ም ፣ግብርና ሚኒስ...
07/02/2026

የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር ስምንተኛ(8ኛ) ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡
(አዲስ አበባ፣ ጥር 30/2018 ዓ/ም ፣ግብርና ሚኒስቴር ሸማቾች ማኅበር)
የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር በዛሬዉ ቀን በግብርና ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አደራሽ የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ፣ንዑሳን ኮሚቴ አባላት፣ተጋባዥ እንግዶች(የፌደራል ህብረት ሥራ ኮሚሽን አደራጅ ክፍል ፣ኦዲት ክፍል ባለሙያ) እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት 8ኛ ዙር ጠቅላላ ጉበኤ ተደረገ፡፡
በጠቅላላ ጉባዔዉ በኢትዮጵ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የ2018 ዓ/ም ኦዲት ሪፖርት ከኢት/ህ/ሥ/ኮሚሽን ኦዲተር ባለሙያዎች ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምዕ የፀደቀ ሲሆን በቀጣይ በጀት ዓመት ለማህበሩ ዉጤታማነት የሚረዳ ግብዓቶች ከቤቱ እና ከ ኦዲት ሪፖርት ማግኘት ተችሏል፡፡
አዲሱ የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር አመራሮች እና ንዑሳን ኮሚቴዎች በተለያዩ ምክንያት የለቀቁ ሲሆን የስራ አመራሩ አጠቃላይ ሪፖርት በማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ የ2018 እቅድ በማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ልደቱ ሞላ ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ የ2017 ዓ.ም ሪፖርት በአቶ ተመስገን ደሳለኝ አማካኝነት እና እቅድ በወ\ሮ አዲሳለም በየነ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ እና ዉስጣ ደንብ ለ አባላት ቀርቧል በዚህም ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን ፡፡ በዚህ መሠረት የቀረቡ ሪፖርቶችን ቤቱ በመልካምነት በመቀበል በቀጣይ መስተካከል ያለባቸዉን ነገሮች ዝርዝር በማቅረብ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም በ2017 ዓ/ም ከ9 ሚልዮን ባለይ ትርፍ የተረፋ ሲሆን የትርፍ ክፍፍል አወሳሰን በተመለከተ ለአባላቱ ዉሳኔ እንዲያስተላልፉ ቀርቦ በአባሉ ምርጫ ወደ ዕጣ ማዞር የሚፈልግ እንዲዞረለት፣ትርፍ ክፍፍሉን መዉሰድ የሚፈልግ በለው እጣ መጠን ትርፍ ክፍፍል አስከ የካቲት 30/2018 ዓ፣ም ድረስ ብቻ እንዲቀበል የተወሰነ ሲሆን በዚህ ጊዜ ተገኝቶ ትርፉን መዉሰድ ያልቻለ አባል ያገኘዉ ትርፍ ወደ ዕጣ የሚዞር መሆኑን የሥራ አመራር ልቀመንበር እና የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሰቢ ለተነሱት ጥያቄዎች እና እቀድ እና ደንቦች በማጻደቅ ማብራሪያ በመስጠት ጉባዔዉ ተጠናቅቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ልደቱ ሞላ
ፎቶ፡ ጌታቸው ምትኩ

Address

Addis Ababa Bole Sub City Woreda 06
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when MoA Cooperative/ግብርና ሚኒስቴር ሸማቾች ማህበር posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share