KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council

KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council, Public Service, kirkos Woreda 07, Addis Ababa.

28/08/2026

የፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ ግንባታ አሁናዊ ገፅታ

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ​አዲስ አበባ — ነሐሴ 11/2018 ዓ.ል​የአዲስ አበባ ከተማ እስ...
17/08/2026

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

​አዲስ አበባ — ነሐሴ 11/2018 ዓ.ል

​የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ማካሄድ መጀመሩን አስታወቀ።

​በጉባዔው መክፈቻ ላይ የጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ የፌደራል መጅሊስ አመራሮች፣ የክብር ጥሪ የተደረገላቸው ዑለሞች፣ ዱዓቶች፣ የአዲስ አበባና የክፍለ ከተማ ወጣቶች ካውንስል አመራሮች እንዲሁም ሌሎች የተከበሩ እንግዶች ተገኝተዋል።

​የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ "ጠቅላላ ጉባኤያችን መለኮታዊ ድንጋጌን መሠረት አድርገን በአደራዎቻችን ላይ የምንመክርበት ይሆናል" ብለዋል።

​በጉባዔው አጠቃላይ አፈጻጸሞች ላይ ከተመከረ በኋላ፣ ምክር ቤቱ ለቀጣዩ የሥራ ዘመን የሚከተሉትን አራት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ አድርጓል፦

​ተቋማዊ አሠራርን እስከ ታችኛው መዋቅር ማድረስ፦ የጀመረውን ተቋማዊ ሪፎርም፣ ህጎችና መመሪያዎች እስከ ወረዳ፣ መስጂድና መድረሳ ድረስ በተግባር ማውረድ።

​የተቋሙን የፋይናንስ አቅም ማሳደግና ዘላቂ ሀብት መፍጠር፦ ነባር ሀብቶችን በአግባቡ ከመጠቀም ባሻገር አዳዲስ የገቢ ምንጮችን በመፍጠርና የወቅፍ ልማቶችን በማስፋፋት ዘላቂ የሀብት መሠረት መገንባት።

​የ«ኒዛም» ሶፍትዌርን አጠናቆ ወደ ሥራ ማስገባት፦ ዲጂታል አሰራርን በሁሉም መምሪያዎች ላይ በመተግበር ግልጽነትና ፍጥነትን ማረጋገጥ።

​የሰው ኃይልና የሰላም ግንባታን ማጠናከር፦ የወረዳና የመስጂድ አመራሮች በተቋማዊ አሠራር፣ በአመራር ብቃት፣ በግጭት አፈታትና በማኅበረሰብ ትስስር ዙሪያ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ማድረግ።

​በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው፥ የአዲስ አበባ መጅሊስ በከተማዋ የተለያዩ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጸዋል። በተሠራው ስራም የተለያዩ ባሕሪይ ባለው የአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የነበሩ ችግሮች እየተቀረፉ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

​አያይዘውም፥ "ኢማሞቻችን እና ሌላው የማሕበረሰብ ክፍል የሚቸገርባቸውን ጉዳዮች ለማቃለል ተቋማችንን በልዩ ልዩ አቅም ማጠናከር ይገባል። በውይይት አጀንዳዎቻችን ሀገራዊ ለውጥን እያጠናከርን በቀጣይ በጋራና በትብብር እንሠራለን" ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

⚽️ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች የወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ! ⚽️​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ​ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች መካከ...
15/08/2026

⚽️ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች የወጣቶች የእግር ኳስ ውድድር ፍጻሜ! ⚽️
​አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካትሁ
​ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወጣቶች መካከል ሲካሄድ የቆየው አጓጊው የእግር ኳስ ውድድር ወደ ፍጻሜ ደርሷል!

​ይህ ውድድር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አዘጋጅነት የተከናወነ ሲሆን፣ ወጣቶችን በአንድነት ለማስተሳሰርና የስፖርት ተሰጥኦአቸውን ለማሳደግ ታላቅ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል።
​🌟 የፍጻሜው ፕሮግራም ዝግጅት
​የፍጻሜው ጨዋታ ነገ እሁድ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው "አዲስ ስፖርት ፓርክ" ወረዳ 08 ከወረዳ 03 ጋር በደመቀ ሁነታ ይካሄዳል!
​ከዋናው የፍጻሜ ጨዋታ በፊትም ታዳሚውን የሚያዝናኑ የተለያዩ ስፖርታዊ እና መዝናኛ ዝግጅቶች የተዘጋጁ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።

​🎖️ የተከበሩ እንግዶቻችን
​በዚህ ደማቅ ሁነታ ላይ፦
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች አመራሮች፣
​የክፍለ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣
​የክፍለ ከተማው እና የወረዳው የእስልምና ጉዳዮች ኃላፊዎች፣
​ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ የስፖርት ተምሳሌቶች እንዲሁም የስፖርት አፍቃሪዎች የሚገኙ ይሆናል።

15/08/2026
⚽️ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ካውንስል የእግር ኳስ ውድድር ወቅታዊ መረጃ! ⚽️​ሐሙስ ዕለት በይፋ የተጀመረው የክፍለ ከተማው ወጣቶች ካውንስል የእግር ኳስ ውድድር መርሃ ግብር ቀጥሎ ዛሬም አ...
09/08/2026

⚽️ የክፍለ ከተማው ወጣቶች ካውንስል የእግር ኳስ ውድድር ወቅታዊ መረጃ! ⚽️

​ሐሙስ ዕለት በይፋ የተጀመረው የክፍለ ከተማው ወጣቶች ካውንስል የእግር ኳስ ውድድር መርሃ ግብር ቀጥሎ ዛሬም አጓጊ ጨዋታ ተካሂዷል!
​📊 የዛሬ ዕለት የጨዋታ ውጤት
​ወረዳ 07 5 - 1 ወረዳ 09 (ወረዳ 07 በሰፊ ውጤት አሸንፏል)

28/07/2026

የክፍለ ከተማው ወጣቶች ካውንስል የሚያዘጋጀው የወጣቶች የእግር ኳስ ወድድር ሃሙስ 23/11/2018 ይጀምራል።
ለውድድሩ የሚሆኑ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን የክፍለ ከተማው ወጣቶች ሰብሳቢ ወጣት ኑርአህመድ መንሱር ገልፀዋል።

የአረፋ ቀን ፆም መፆም እንዳንዘነጋ!ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦ ﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾ ...
25/05/2026

የአረፋ ቀን ፆም መፆም እንዳንዘነጋ!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ ማክሰኞ ግንቦት 18 ነው።

18/05/2026

ተጨማሪ ማብራሪያ በቀብር ክፍያ ማስተካከያ ላይ

ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር አንድ ሰው የቀብር አገልግሎት ለማግኘት 2000 ብር ለከፍተኛ ም/ቤቱ ይከፍልና ከዚህ በተጨማሪ ለብሎኬት ግዢ ከ2200 እስከ 2800 ብር ለግለሰቦች በመክፈል የማጓጓዣ ሳይጨምር በድምሩ ቢያንስ ከ4200 እስከ 4800 ብር በማውጣት አገልግሎት ያገኝ ነበረ።

አሁን በተደረገው የአሰራር ማሻሻያ አንድ ሰው ለም/ቤቱ በሚፈፅመዉ የ4000 ብር ክፍያ የብሎኬት አቅርቦትን የሚጨምር የቀብር አገልግሎት የሚያገኝ ከመሆኑም በተጨማሪ ተገልጋዮች ለአላስፈላጊ እንግልት እና ተጨማሪ አላስፈላጊ ወጪ እንዳይዳረጉ ይረዳል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የከፍተኛ ም/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሰጡትን ማብራሪያ ማክሰኞ ግንቦት 11/2018 ከረፋዱ 4:00 በፌስቡክ እና ዩቲዩብ ገፃችን የምናስተላልፍ መሆኑን እናሳውቃለን።

1447ኛው የዒድ አልአድሃ በዓል ረቡዕ ይውላል።​ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ ጨረቃ በመታየቷ የዙል-ሂጃ ወር መግባቱ ተገልጿል።​ይህን ተከትሎ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (የዓረፋ) በዓል ዕሮብ ረቡ...
17/05/2026

1447ኛው የዒድ አልአድሃ በዓል ረቡዕ ይውላል።

​ዛሬ በሳዑዲ አረቢያ ጨረቃ በመታየቷ የዙል-ሂጃ ወር መግባቱ ተገልጿል።

​ይህን ተከትሎ 1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (የዓረፋ) በዓል ዕሮብ ረቡዕ ግንቦት 19 ተከብሮ ይውላል።

Address

Kirkos Woreda 07
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when KSC Woreda 07 Islamic Affairs Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category