06/04/2026
ዛሬ ጠዋት እራስን ማሻሻል ላይ መሰረት ያደረገ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄዷል !!
መልካም ሳምንት ይሁንልን🙏
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው እለት የተደረገ ሲሆን ""ውጤታማ እና ስኬታማ"" ለመሆን የሚያስፈልጉዎት ዋና ዋና ነገሮች በሚል ርዕስ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በስራዎት ውጤታማ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያውስ እነዚህን የስነ-ልቦና መመሪያዎች አንብባችሁ ተግባራዊ አድርጓቸው፡፡
በስራችን ውጤታማ ለመሆን ከሚያስፈልጉን ነገሮች መካከል የስነልቦና ዝግጅት የመጀመሪያው የስራ መሳሪያችን ነው፡፡
ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ እንድንሆን ከሚረዱን ዋና ዋና ነገሮች መካከል ስንመለከት በጥቅቱ፡፡
1, ፍላጎት፡-
በስራችን ስኬታማ ለመሆን ከሚያስፈልጉን ነገሮች መካከል ፍላጎትየመጀመሪያው እና ዋናወ መሰረታዊ የስኬት ምስጢር ነው፡፡
2, እምነት፡-
እምነት አላማችን የሚገነባበት መሠረት ስለሆነ ሁላችንም የምንሰራውን ስራ አምነን መቀበል እና በመጨረሻም ውጤታማ እንደምንሆን ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡
3, እራስን ማሳመን፡-
ወደ ስራ ከመግባታችን በፊትም ሆነ ስራ ላይ ከተሰማራን በኋላ በስራችን ውጤታማ ለመሆን እራሳችንን አሳምነን መስራት ሌላኛው የውጤታማነት ቁልፍ ነው፡፡ስለዚህ እራሳችንን አሳምነን በስነ-ልቦና ዝግጁ መሆን እና ወደስራ መግባት ያሰፈልጋል፡፡
4, እቅድ ማውጣት-
እቅድ ማውጣት ጊዜን በአግባቡ እንድንጠቀም ያደርገናል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በየጊዜው የምንሰራውን ስራ ለመገምገምም እድል ይሰጠናል፡፡
5, ጽናት፡-
የምንሰራው ስራ ተሳክቶ ውጤታማ እስክንሆን ድረስ ያለመሰልቸት በፅናት መስራት ያስፈልጋል፡፡
ወርቅ በእሳት ይፈተናል እንደሚባለው ሁሉ በስራችን በርካታ ፈተናዎች እና ውጣ ውረዶች ሊደርሱብን ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ግን በፅናት መስራት አለብን፡፡
28/07/2018
Addis Ababa Education Bureau