13/03/2026
ጠንካራ ኢንስፔክሽን ፣ለጠንካራ ፓርቲ!!
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት በ8ንት ወረዳዎች የሚካሄደውን ፕሮፎርማንስ ኦዲት እቅድና ቼክ ሊስት ከኢንስፔክሽን ቡድኑን ጋር የጋራ ተደረገ።
ውይይቱን የመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተሾመ ወልደየስ እንደገለፁት የተሠጠዉን ኃላፊነትና አደራ በወል ተረድቶ በጥንቃቄ በጥብቅ ዲስፕሊንና በመመራት በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፅ/ቤቱ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ አዳነ ሙላው በበኩላቸው እየተሠሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን
ገልፀው በኢንስፔክሽኑ ለፓርቲያችን እሴት የሚጨምሩ እና የነበሩ ጥንካሬዎችን የማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም ተቋማትን የማጠናከር ስራ በትኩረት ሊያመላከቱ የሚችሉ መሆን ይገባቸዋል ብለዋል።