PP Star Youth Wing

PP Star Youth Wing PP Star youth wings

የኢትዮ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ አካሄደየኢትዮ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች...
04/09/2026

የኢትዮ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ የችግኝ ተከላ አካሄደ

የኢትዮ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሃሳብ በ8ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በአዳማ የክፍያ መንገድ ዳር የችግኝ ተከላ አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ከ120 በላይ የወረዳው ወጣቶች በንቃት ተሳትፈዋል። በዕለቱ የታየው የወጣቶች ተሳትፎና መነሳሳት መርሃ ግብሩ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ያመላከተ ነበር።

ለመርሃ ግብሩ በድምቀት መሳካት የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ላደረገው አስተዋጽኦ የኢትዮ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል።

የችግኝ ተከላው በአካባቢ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ ልማት እና በቀጣይ ትውልድ ላይ የሚኖረውን የጋራ ኃላፊነት ለማጠናከር ያለመ ሲሆን፣ ወጣቶች በአካባቢ ጥበቃ ተግባራት ላይ ያላቸውን ተሳትፎም የሚያጠናክር ነው።

03/09/2026


የተበረከተ ድንቅ ስጦታ✅🙏🇪🇹

02/09/2026

‎የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው

‎አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ ‎የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ።

ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል።

‎የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው።

በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል።

‎መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል።

‎የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል።

‎በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል።

‎በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል።

‎በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል።

‎ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።

Ethiopian News Agency #ኢዜአ

02/09/2026
01/09/2026

ያስፈልጋታል🇪🇹✅🙏

01/09/2026


🔊 🇪🇹✅

ኢትዮጵያ በረከተ ብዙ ናት። ተፈጥሮ የሰጣት ሀብት ከሰው ሰራሽ ጥሪቷ ጋር ተዳምረው ብልጽግናዋ አይቀሬ ለመሆኑ ምስክር ናቸው።

ቱሪዝም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉት ምሰሶዎች አንዱ ሆኖ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውስጥ ልዩ ስፍራ ተሰጥቶታል። ይህ የዕይታ አድማስን ማስፋትና ጸጋዎችን የመመልከት መንገድ ደግሞ ሀብታችን በተገቢው ለመጠቀም እንዲያስችል ታምኖበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው “ኢንዱስትሪው በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና አካባቢያዊ ሁኔታዎች ውስጥ ትልቅ አስተዋጽዖ እንዲኖረው እንፈልጋለን።” ሲሉ የመንግሥታቸው መሻት መጠን ምን ድረስ እንደሆነ ያስቀምጣሉ።

ባለፉት ዓመታት በከተማም ሆነ በገጠር የሚገኙ መዳረሻዎች ተለይተው፣ ነባሮቹ ተሻሽለው፣ አዳዲሶችም ተገንብተዋል። ይህ ጥረት የመጣውን መልካም ዕድል ወደ ተጨባጭ ጥቅም ለመቀየር የተደረገ ትልቅ እርምጃ ነው።

ሆኖም የቱሪዝም እድገት በመሠረተ ልማት ብቻ የሚገለጽ አይደለም። ዓለም እየተለወጠ ባለበት በዚህ ዘመን፤ ኢትዮጵያን ለዓለም የማስተዋወቅ ኃላፊነት ወደ አዲሱ ትውልድ እጅ እየተሸጋገረ ነው።

ወጣቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ በተለይም ማህበራዊ ሚዲያን፣ ክውን ጥበባትንና የአኒሜሽን ጥበብን ተጠቅመው የኢትዮጵያን መልክ ለዓለም እየገለጡ ይገኛሉ።

አዲሱ ትውልድ የሀገራችንን ማራኪ ውበቷን፣ የማይደበዝዘውን የታሪክ ትውፊቷንና ድንቅ ብዝሃነቷን ለዓለም በአዲስ መንገድ እያሳየ ይገኛል። ይህ ደግሞ ቱሪዝምን ከባህላዊው የማስተዋወቂያ ስልት አልፎ ዲጂታል ትውልድ ወደሚረዳው ቋንቋ የሚተረጉም አዲስ ድልድይ ፈጥሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ ለዚሁ ለአዲሱ ትውልድ አባላት የኢትዮጵያን ድንቅ የብዝሃነት ውበት እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተለይ ደግሞ በዓለም ዙሪያ የተበተኑ የሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ባህላቸውን፣ ታሪካቸውንና ቅርሳቸውን በአካል የሚያውቁበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። "Connect to your culture"፣ "Connect to your history" እና "Live your legacy" በሚል በተለያዩ ዙሮች የተካሄዱት ጥሪዎች፣ ወጣቶች ከመሠረታቸውና ከፈለቁበት ምድር ጋር እንደገና እንዲተሳሰሩ አድርጓቸዋል።

ወጣቶች ጥሪውን ተቀብለው ብቻቸውን አልመጡም። ኢትዮጵያን ዘመናዊ በሆነ የቴክኖሎጂ ቋንቋ ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ አምባሳደሮችም ሆነውላታል።

በአዲሱ ዓመት ብዙ ቁጥር ያላቸው የሁለተኛው ትውልድ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ይህ አጋጣሚ ሁለት ገጽታ አለው። አንደኛው፣ እነዚህ ወጣቶች ሀገራቸውን በዓይናቸው አይተው፣ ቅርሶቿን ዳስሰው፣ ከሥረ መሠረታቸው ጋር ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩበት ዕድል ማግኘታቸው ነው።

ሁለተኛው፣ ይህ ትውልድ ካለው የቴክኖሎጂ ብቃትና ዓለም አቀፍ ትስስር በመነሳት፣ የተመለከቱትን ውበትና ትውፊት ወደ ዲጂታል ይዘት በመቀየር ለዓለም ማህበረሰብ ማስተላለፍ መቻሉ ነው።

ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክና በባህል የበለጸገች ብትሆንም፣ ይህን ሀብት ለዓለም በሚስብ መልኩ የማድረስ ስራ ገና ብዙ ይቀረዋል።

የቱሪዝም መሠረተ ልማት መስፋፋትና የሁለተኛው ትውልድ መመለስ ብቻ በቂ አይደሉም፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ የታገዘ ተረክ ያስፈልጋል። አኒሜሽን፣ ዲጂታል ይዘቶች፣ ማህበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የሚቀርቡ ውብ ታሪኮች ኢትዮጵያን ከቀድሞው በተለየ ፍጥነትና ስፋት ለዓለም ማስተዋወቅ ይችላሉ።

በዚህ መልኩ ቅርስ፣ ትውልድና ቴክኖሎጂ ተዋህደው ኢትዮጵያ ለራሷ ልጆችም ሆነ ለዓለም ማህበረሰብ በአዲስ መንገድ የምትተዋወቅበት ዘመን ተጀምሯል። አዲሱ ዓመት ለዚህ ትስስር መጠናከር ትልቅ አጋጣሚ ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በአፈወርቅ እያዩ

01/09/2026

🇪🇹🙏✅

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when PP Star Youth Wing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share