29/08/2026
የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽን ቡድን በከተማዉ ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አደረገ!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኢንስፔክሽን ቡድን በወራቤ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ቀበሌዎች ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ላይ የመስክ ምልከታ አድርጓል።
ምልከታው በዋናነት ትኩረት ያደረገው ዜጎችን ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለማሸጋገርና የሰብዓዊ እርዳታ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰሩ ባሉ ስራዎች ላይ ነው።
በምልከታው ወቅት ቡድኑ በከተማው ከተረጂነት ወደ አምራችነት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮች ማሳን እና በራስ አቅም ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስራዎችን ተዘዋውሮ ምልከታ በማድረግ በሂደቱም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ምክክር አድርገዋል።
እነዚህ የልማት ስራዎች የነዋሪዎችን ኑሮ ከመደገፍ ባለፈ ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ረገድ እያሳዩት ባለው ለውጥ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የቡድኑ አባላት በሰጡት አስተያየት፡ በከተማዋ የተረጅነት አስተሳሰብን በመስበር ዜጎች በራሳቸው አቅም እንዲያመርቱ እየተደረገ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።
የሰብዓዊ እርዳታ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና በምግብ ራሳችንን ለመቻል የሚደረገው ጉዞ በተግባር እየታየ መሆኑም ተመላክቷል።
ረጂ ተቋማት እየቀነሱ መምጣታቸዉ የተገለጸ ሲሆን መስራት የማይችሉና የሚደገፉ አካላትን በመለየት ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ በማድረግ እኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ይገባል ተብሏል።
የተረጅነት ስነ-ልቦናን በማስወገድ ህዝቡን የልማቱ ባለቤትና አምራች ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸዉም ተጠቁሟል።
የኢንስፔክሽን ቡድኑ በከተማ አስተዳደሩ ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለመሸጋገር እየተደረጉ ባሉ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ ድጋፍና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ መዘገባችን የሚታወስ ነው።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ነሃሴ 22፣ 2018 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]