19/06/2026
የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤት ሰኔ 11/2018 ዓ/ም
በአዲስ ዘመን ከተማ ቀበሌ 01 የህዝብ የምክክር መድረክ ተካሄደ
የሊቦ ከምከም ወረዳ ፍርድ ቤትፕሬዚዳንትና የህዝብ ግንኙነት እና የኮምንኬሽን ባለሙያ በተገኙበት የህዝብ የምክክር መድረክ በስፋት ተካሂዷል፡፡በመጀመሪያም የፍርድ ቤቱን የ11ወራት የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የፍርድ ቤቱን ተደራሽነት በምክክር መድረኩ በስፋት ዉይይት የተደረገበት አጀንዳ ነዉ፡፡
እንዲሁም የባህል ፍርድ ቤቶችንም አስፈላጊነትና አላማ በድጋሜ በህዝብ የምክክር መድረኩ ዉይይት ተደርጓል፡፡የተመረጡ የባህል ፍርድ ቤቶችም የማህበረሰቡን ወግና ባህል መሰረት አድርገዉ በዳበረ የሽምግልና ስርዓት ሰላምን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም ባህላዊ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንደሚቻል ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡
ቀጣይ ወደ ስራ ለሚገቡ የባህል ፍርድ ቤት ሽማግሌዎች አጋር አካላት በማቶሪያል፤በቢሮ ማስቻያ፤እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠናም በመስጠት ከጎናችን መሆን እንደሚጠበቅባቸዉ ፕሬዚዳንቷ መልክት አስተላልፈዋል፡፡
ሰኔ 11/2018 ዓ/ም
አ/ዘመን