ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ

  • Home
  • Ethiopia
  • Adis
  • ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ

ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ Creating democrat, vibrant and front line youth that has accepted and ready to implement programs and objectives of prosperity party

ንቁ ወጣቶች ለሀገር ግንባታ!ወጣቶች የአንድ ሀገር ኃይል፣ የለውጥ አራማጆች እና የነገዋ ሀገር መሰረቶች ናቸው፣ንቁ ወጣትነት በሀገር ጉዳይ ላይ በባለቤትነት ስሜት በመሳተፍ፣ ማህበራዊና ኢኮኖ...
27/08/2026

ንቁ ወጣቶች ለሀገር ግንባታ!

ወጣቶች የአንድ ሀገር ኃይል፣ የለውጥ አራማጆች እና የነገዋ ሀገር መሰረቶች ናቸው፣ንቁ ወጣትነት በሀገር ጉዳይ ላይ በባለቤትነት ስሜት በመሳተፍ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፎካካሪነትን በማሳደግ ለአዎንታዊ ለውጥ ዝግጁ የሆነ ትውልድን ይፈጥራል። ወጣቱ ክፍል ባለው አዲስ ጉልበት፣ ያልተገደበ አቅም እና ተነሳሽነት ተጠቅሞ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ ከፊት መስመር ሲሰለፍ፣ የሀገራችን እድገት ፈጣን፣ ዘላቂ እና አስተማማኝ ይሆን።

​ፈጠራ እና አዳዲስ ሀሳቦችን ማፍለቅ ደግሞ የወጣቶች ትልቁ የኃይል ምንጭ ነው። በአሁኑ የቴክኖሎጂ እና የእውቀት ዘመን፣ ባህላዊ አሰራሮችን በአዳዲስ ዘዴዎች መተካት፣ የማህበረሰብ ችግሮችን በፈጠራ መፍታት እና በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ መሰማራት የሀገርን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል። ወጣቶች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በኪነ-ጥበብ እና በማህበራዊ ዘርፎች የሚያሳይዋቸው አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች ሀገርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ ቁልፍ መሳሪያዎች ናቸው።

​በተጨማሪም፣ ወጣቶች በማህበራዊ ሀላፊነት፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በማህበረሰብ ልማት ስራዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ የሰላም እና የአንድነት አምባሳደር በመሆን የሀገርን ዘላቂ ህልውና ያረጋግጣሉ። ዛሬ በምንገኝበት የዲጂታል ዘመን፣ ማህበራዊ ሚዲያ የወጣቱን አቅም፣ እውቀት እና አዎንታዊ አስተዋፅኦ ለትውልድ ግንባታ እና ለሰላም ማስፈን ለማዋል ትልቅ አስተማሪና አስተሳስሪ መሳሪያ እየሆነ መጥቷል።

​መንግስት፣ ማህበረሰቡ እና የሚመለከታቸው አካላት የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያበረታቱ እድሎችን ማመቻቸት ይኖርባቸዋል። ወጣቶች ሀገራዊ ራዕይን አንግበው፣ ሰላምን፣ አንድነትን እና ልማትን በማጠናከር በቁርጠኝነት ሲንቀሳቀሱ የበለፀገች እና ጠንካራ ሀገርን እውን ማድረግ ይቻላል።

የክረምት በጎ ፍቃድን ምክንያት በማድረግ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከጤና ሚኒስትር፣ከየካ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት እና ሚድያ ዘርፍ እና የወጣቶች ክንፍ ጋር በጋራ በመሆን ንቁ ወጣቶች ለሀገር ግንባታ በሚል ርእስ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ስልጠና ሰተዋል።

"ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት"በለሚ ኩራ  ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ   "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የ 2018 የማጠቃለያ ኮንፍረን...
18/08/2026

"ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት"

በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የ 2018 የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በድምቀት አካሂዷል።

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የተቋሙን ተግባራት የያዘ ሰነድ ቀርቦ ጥልቅ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በተለይም በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የፓርቲያችንን መንትያ ግቦች በማሳካት ረገድ የፓርቲውን አባላት በማንቀሳቀስ ረገድ ሰፊ ስራ መሰራቱ ተመላክቷል። ከፓርቲ መደበኛ ተግባራትም አንፃር ሰፊ ስራ መሰራቱ የተገለፀ ሲሆን የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል የነበሩ ውጤታማ ስራዎችን በማላቅ ለቀጣይ በጀት ዓመት ስኬታማነት በቂ ስንቅ መሰነቁ ከመድረኩ ተመላክቷል።

በኮንፍረንሱ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክ/ከተማው አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በልዩ አበበ የወጣት ክንፉ ተቋማዊ አቅሙ እያደገ የመጣ መሆኑን በመጠቆም የህንን አዳጊ አቅም የበለጠ በማላቅ ለፓርቲያችን ሁለንተናዊ ስኬት ማወል እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት “ደሜን ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የደም ልገሳ መርሐግብር በዛሬው ዕለት  ተካሂዷል።​...
13/08/2026

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪነት “ደሜን ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የደም ልገሳ መርሐግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

​በዚህ የበጎ አድራጎት መርሐግብር ላይ የክፍለ ከተማው የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊን ጨምሮ የሁሉም ወረዳ የዘርፉ አመራሮች፣ የክንፉ አባላት እና በርካታ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተው ህይወት አድን ደም በመለገስ አአርአያነታቸውን አሳይተዋል።

​ የደም ልገሳ መርሐግብሩ የብልፅግና ፓርቲ ዋና መመርያ የሆነውን ሰው ተኮርነትንና የመደመር እሳቤን በግልጽ በመሬት ላይ ያረጋገጠ ተግባር መሆኑም ተመላክቷል።

በመርሐግብሩ ላይ የተገኙት የወጣቶች ክንፍ አመራሮች እንደገለጹት፤ የወጣቱ ትውልድ ድርሻ ሀገርን በግንባታና በልማት መደገፍ ብቻ ሳይሆን የወገንን ሕይወት መታደግ እና ወንድማማችነትን በተግባር ማሳየት በመሆኑ፣ ደም መስጠት የፍቅር፣ የደግነት እና የሰው ልጅ ህይወት የማደስ ትልቅ ማህበራዊ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

​ወጣቱ አቅሙን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወት አድን ደሙን ለወገኑ በማካፈል ማህበራዊ አለኝታነቱን በማረጋገጥ ላይ እንደሚገኝ በዕለቱ የተጠቆመ ሲሆን፣ ይህ የደም ልገሳ የበጎ አድራጎት ስራ የአንድ ወቅት ዘመቻ ብቻ ሳይሆን የፓርቲውን እሴቶች መሠረት ያደረገ ተቋማዊና ባህላዊ አሰራር ሆኖ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

በአንድነትና በወንድማማችነት መንፈስ የሚከናወኑ እንዲህ ያሉ በጎ ተግባራት የህብረተሰቡን ህብረ-ብሔራዊ ትስስር አጠናክረው ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ብልፅግና መረጋገጥ የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸውም ተጠቁሟል።

«ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ » የወንዝ ዳርቻ ልማት የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ «ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ » የአካባቢ ጥበቃና የፅዳት ዘመቻ አካሄደ።...
12/08/2026

«ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ » የወንዝ ዳርቻ ልማት የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ «ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ » የአካባቢ ጥበቃና የፅዳት ዘመቻ አካሄደ።

በፅዳት ዘመቻው የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ አቶ ተገኝ ወዛ እንደተናገሩት የወንዝ ዳርቻዎችን ከቆሻሻ ነጻ ማድረግ የከተማ ውበትን ከማስጠበቅ ባለፈ የውሃ ምንጮችን ከብክለት ለመጠበቅ፣ የአካባቢ ጤናን ለማሻሻልና የኢኮሎጂ ሚዛንን ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ገልፀው፤የወንዝ ዳርቻን በአንድ ቀን ብቻ ማጽዳት በቂ እንዳልሆነ ባለመሆኑ ቆሻሻን ከምንጩ መቆጣጠር፣ በአግባቡ መሰብሰብና አካባቢን በየጊዜው መንከባከብ የሁሉም ዜጋ የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ተናግረዋል

የ«ፅዱ ኢትዮጵያለ ትውልድ» ዘመቻ ከጽዳት ሥራ ባለፈ ንጽህና ባህልን በማሳደግና ማኅበረሰቡ የአካባቢው ባለቤት እንዲሆን በማበረታታት ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ሥርዓት ለመገንባት ያለመ መሆኑን የተናገሩት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ በቀለ ሰርቤሳ በቀጣይም የወንዝ ዳርቻዎችን ከቆሻሻ ነጻ ለማድረግ የማኅበረሰብ ተሳትፎን በማጠናከር የጽዳትና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

በጽዳት ዘመቻው የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የወጣቶች ክንፍ አባላት፣ በጎ ፈቃደኞችና የተለያዩ የማኅበረሰብ አካላት በመሳተፍ በወንዝ ዳርቻው የተከማቹ የፕላስቲክ ቆሻሻዎችንና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን አስወግደዋል።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በክረምቱ መርሀ ግብር "prosperity Youth summer cup " በክፍለ ከተሞች መካከል የሚካሄድ የወንድማማችነት ስፖርታዊ ውድድ...
07/08/2026

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በክረምቱ መርሀ ግብር "prosperity Youth summer cup " በክፍለ ከተሞች መካከል የሚካሄድ የወንድማማችነት ስፖርታዊ ውድድር በዛሬዉ ዕለትም ቀጥለዋል፡

ስፖርታዊ ውድድሮች ለህብረ ብሔራዊ አብሮነት መጠናከር!የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በክረምቱ መርሀ ግብር በክፍለ ከተሞች መካከል የሚካሄድ የወንድማማችነት ስፖርታዊ ...
06/08/2026

ስፖርታዊ ውድድሮች ለህብረ ብሔራዊ አብሮነት መጠናከር!

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ በክረምቱ መርሀ ግብር በክፍለ ከተሞች መካከል የሚካሄድ የወንድማማችነት ስፖርታዊ ውድድር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በሚገኘው የእግር ኳስ ሜዳ አስጀምሯል።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በፕሮግራሙ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የወጣቶች ክንፍ ለወጣቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት እንዲሁም የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በማስተባበር ስኬታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስፖርት ማዘውተሪያዎችን በብዛትና በጥራት በመገንባት ለወጣቶች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የጠቀሱት አቶ ዘሪሁን ስፖርታዊ ውድድሮች ህብረ ብሔራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንደሚያግዙ አስረድተዋል።


የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ም/ ኃላፊ ወጣት በቀለ ታጀብ በበኩላቸው በክረምቱ መርሀ ግብር ተጠናክሮ ከቀጠለው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጎን ለጎን በክፍለ ከተሞች መካከል የሚደረጉ ወንድማማችነትን የሚያጠናክሩ ስፖርታዊ ውድድሮች መጀመራቸውን ገልፀዋል።

ስፖርታዊ ውድድር ወጣቶች እርስ በእርሳቸው የሚተዋወቁበት፣ ጤናቸውን የሚጠብቁበት መሆኑን ያስረዱት ወጣት በቀለ አስተዳደሩ ለወጣቶች የገነባቸውን የስፖርት ማዘውተሪያዎች በአግባቡ መጠቀም እና መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ለሴቶችና ወጣቶች ስልጠና ተሰጠ።​በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የወጣትና ሴት ክንፎች ከ...
05/08/2026

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ለሴቶችና ወጣቶች ስልጠና ተሰጠ።

​በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የወጣትና ሴት ክንፎች ከክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር ለአባላቶቻቸው በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ የስልጠና መድረክ አዘጋጁ።

​ስልጠናው በዋናነት ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ፣ የማህበረሰብ አብሮነትን በማጠናከር እና በችግሮች አፈታት ዙሪያ የወጣቶችና የሴቶችን ንቁ ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ያተኮረ ነው።
​በመድረኩ ላይ እንደተገለፀው፤ ሰላም የልማትና የእድገት መሰረት በመሆኑ፣ ሴቶችና ወጣቶች በየአካባቢያቸው የሰላም አምባሳደር በመሆን ዘላቂ እሴቶችን የመገንባትና የማስረጽ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ከሰው ተኮር ተግባራቶች መካከል አንዱ በበጎ ተግባራት የተቸገሩትን መጠየቅ ነው!የመረዳዳት የመደጋገፍና አብሮነትን ከፍ የሚያደርገው እሳቤ ሰው ተኮር ተግባራቶችን አልቆ በመፈፀም የበጎ አድራጎ...
04/08/2026

ከሰው ተኮር ተግባራቶች መካከል አንዱ በበጎ ተግባራት የተቸገሩትን መጠየቅ ነው!

የመረዳዳት የመደጋገፍና አብሮነትን ከፍ የሚያደርገው እሳቤ ሰው ተኮር ተግባራቶችን አልቆ በመፈፀም የበጎ አድራጎት ስራዎችን አበርክቶ በመስራት የእህትማማችነትና የወንድማማችነት እሳቤ በተግባር በመግለጥ መረዳዳትን ባህል ማድረግ መቻል ነው።

የአስተሳሰብና የአመለካከት አንድነት ማምጣት ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትን በማፅናት ሂደት ውስጥ የበጎ አድራጎት ተግባራት ፋዳቸው የጎላ ነው።

በዛሬ እለት ይህንን እሳቤ በሚገልፅ መልኩ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤ የወጣቶች ክንፍ በየካቲት 12 ሆስፒታል በመገኘት በጎነት በሆስፒታ መረሃ-ግብር አከናወነ።

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ቃሏን አክባሪዋ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ደማቅ ክብረ ወሰን አስመዘገበች።ኢትዮጵያ ዛ...
03/08/2026

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ቃሏን አክባሪዋ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ደማቅ ክብረ ወሰን አስመዘገበች።

ኢትዮጵያ ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ 805.3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ ዕቅድ በላቀ ስኬትና በታላቅ ድምቀት ማሳካቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አደረጉ።

ይህ ታሪካዊ ድል የዛሬው ዕለት ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያቀደችውን ግብ ያለምንም መጓደል በተግባር እያሳካች መሆኗን በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

 #ለወጣቶች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ስጋት እና መፍትሄዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!===========================ሐምሌ 24/2018የክረምት በጎ ፍቃድ አንድ አካል የሆነው ወጣቶች...
01/08/2026

#ለወጣቶች በሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ስጋት እና መፍትሄዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!
===========================
ሐምሌ 24/2018

የክረምት በጎ ፍቃድ አንድ አካል የሆነው ወጣቶችን በሁለንተናዊ የአመለካከት እና የስነልቦና ውቅር የመቅረጽ ተግባር የወጣቶች የስለጠና መድረክ የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ እና ወጣቶች ስፖርት ዛሬ በይዘቱ ጠለቅ ያለ ስልጠና በሕገ-ወጠ የስውዎች ዝውውር ስጋትና መፍትሄዎች ዙሪያ ተሰጥቷል፡፡

በውይይቱም የክ/ከተማው ወጣቶች እና የክንፍ አባላት ተጋባዥ እንግዶችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የችግሩን ክብደት ስፋት እና ጥልቀት በስልጠናው ተነስቶ ወጣቶቹ ተገቢዉን ግንዛቤ እንዲጨብጡ እና የመፍትሄው አካል እንዲሆኑ በውይይት ዳብሯል።

የቦ/ክ/ከተማ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ለሰልጣኞቹ ባቀረቡት ሰነድ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር በብዙ ወጣቶች ላይ የሕይወት፣ የደኅንነት እና የኢኮኖሚ ችግሮችን የሚያስከትል አደገኛ ወንጀል መሆኑን በመግለጽ በዚህ መሠረት ወጣቶች የማይታመኑ የሥራ ወይም የጉዞ ቃል ኪዳኖችን እንዳይቀበሉ፣ ከሕጋዊ መንገዶች ብቻ እንዲጠቀሙ እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ለሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት እንዲያሳውቁ ጠይቀዋል።እንዲሁም ወጣቶች ክንፍ እና ወጣት እና ስፖርት ጽ/ቤት በመተባበር ግንዛቤን በማሳደግ ወጣቶችን ከዚህ ዓይነት አደጋ ለመጠበቅ ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ጠቅሰዋል።

የቦሌ ክ/ከተማ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ሔለን ለገሰ እና የወጣት ስፖርት ኃላፊ አቶ ዳግም ጣሰው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የሰው ክብርንና ሕይወትን ለአደጋ የሚዳርግ ወንጀል መሆኑን በማንሳት ያልተረጋገጡ የሥራና የጉዞ ቃል ኪዳኖችን አለማመን፥ የመረጃ እውነተኝነትን ማጣራት እና አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ለሚመለከታቸው አካላት መጠቆም እንዳለባቸው ራሳችንን በመጠበቅ ማህበረሰባችንንም እንጠብቅ በሚል ለወጣቶች ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

Address

Adis

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ብልፅግና ወጣቶች ክንፍ - አዲስ አበባ ቅርንጫፍ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share