10/03/2026
አስደሳች ዜና ለአይሳኢታ እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ!!!
የዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል "Cure Blindness Project" ከተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከተለያዩ አካባቢዎች ለሚመጡ ወገኖች ነፃ የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ከመጭው መጋቢት 21 እስከ 25 ባሉ ተከታታይ ቀናት ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።
ስለሆነም የዓይን ሞራ ግርዶሽ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች ከመጋቢት 1/07/18 ጀምሮ በአይሳኢታ ፕራይመሪ ሆስፒታል የቅድመ ልዬታ እና የምርመራ ሥራ እየተሠራ ስለሆነ ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲትሆኑ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ይህ የህክምና ዘመቻ ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በመሆኑ ታካሚዎች የቀዶ ህክምና ከመደረጉ በፊት ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ካሉ ቀደም ብሎ በመምጣት ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቿል። ስለዚህም የልዬታ ሥራው በሆስፒታላችን ከዛሬ ጀምሮ የተጀመረ መሆኑን እየገለፅን በሆስፒታላችን በመገኘት የቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ወይም ወዳጅ ዘመድዎን እንዲያስመረምሩ ጥሪችንን እናቀርባለን።
በአይን ሞራ ግርዶሽ አማካኝነት የአይን ብርሀናቸውን ያጡ ወገኖቻችን በመረጃ እጥረት ምክንያት እቤታቸው እንዳይቀሩ መረጃውን በማዳረስ የበኩሎን ይወጡ።
Aysaita Primary Hospital!!!