Fanti-Rasuk Qadli Miracsenta

Fanti-Rasuk Qadli Miracsenta Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fanti-Rasuk Qadli Miracsenta, Government Official, Afar, Afar.

Rakaakayak Qadli xagortik  Taama selta makaado Tatre  12 Alsat Tekke  Qadli Taamoomih Abnissol walal gexsen  Ta walalat ...
02/07/2026

Rakaakayak Qadli xagortik Taama selta makaado Tatre 12 Alsat Tekke Qadli Taamoomih Abnissol walal gexsen

Ta walalat Rakaakay Poolisik Edde caba Amolladi miracsentaay Garkuraay Gaaroyseey Gittoyso Buxaay Rakaakayak Qadli xagortik Taama Selta makaado Edde Tengele

Taracal Geytimak Rakaakayak Sangerra cokmih buxah prezixantih Gifta muusa Qabdu Yabti fakenta Abek Lakalay Sanatat Namma Addat Rasittel Teknik makaado Aben Taama Gufnel suber visin Taamal Tumbulle Qakittee kee ciggiila Udduurul Tambulle Taqabitteh Yamcawwuwa cilli wagittaamal Baar walal Gexisen

Tamakaado sanatat 2 addat Raasittel teknik kumite caddol Rasitet takke taama gufnel aw subar visin taamal tumbulle kaqitte kee ciggila uddurul tumbulle taqbiteh yantacawwa calli wagittaamal baar le walal gexisak geytiman.

rakaakayak gittoyso xiinissoh Komishiini!!

26/06/2026

ሙስናን ለመከላከል አምስቱ “መ” ዎች

*********************

ሙስናን ለመከላከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ በ“አምስቱ መ ዎች” (ቁልፍ ፅንሰ-ሃሳቦች) ላይ መስራት የፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማነቱን ያጎለብተዋል። እነዚህም የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

1. መገንዘብ (ግንዛቤ ማስጨበጥ)፡- ሙስናን ለመከላከል በመጀመሪያ ማህበረሰቡን፣ በየደረጃው ያሉ የተቋማት አመራርና ሠራተኞችን በሙስና አስከፊነት፣ አይነቶችና መገለጫዎች በቂ እውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው።

በሥነ-ምግባር የታነጸ ትውልድ ለመፍጠር ቀጣይነት ያለው ግንዛቤ መፍጠሪያ ዘመቻዎችና ስልጠናዎች ወሳኝ ናቸው።

2. መከላከል (ቅድመ-መከላከል)፡- ሙስና ከተከሰተ በኋላ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ አስቀድሞ እንዳይከሰት መከላከል መቅደም አለበት። ይህም የሙስና ስጋት ግምገማ በማድረግ፣ የአሰራር ክፍተቶችን በመድፈንና ግልጽነት ያላቸውን አሠራሮችና መመሪያዎችን በመዘርጋት መተግበር ያስፈልጋል።
3. መተባበር (ቅንጅታዊ አሰራር)፡- ሙስናን በአንድ ተቋም ብቻ መዋጋት አይቻልም። የመንግስት ተቋማት፣ ልማት ድርጅቶች፣ ህዝባዊ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰባትና መላው ህዝብ እጅና ጓንት ሆነው በጋራ እንዲሰሩ መተባበር እና ጠንካራ ሥነ-ምህዳር መፍጠር የመጨረሻውና ወሳኙ ምሰሶ ነው።

4. መመርመር (ሙሰኞችን ማጋለጥ፣ ኦዲት ማድረግ)፡- ማንኛውንም የሙስና ጥርጣሬ ወይም ጥቆማ በጥልቀት መመርመር እና ማረጋገጥ ሌላኛው ሥራ ነው። ይህም ጠንካራ የውስጥና የውጭ ኦዲት አሰራርን መዘርጋት፣ የሙስና ጥቆማ መቀበያ ስልቶችን ማጠናከር እንዲሁም በተጨባጭ ማስረጃ ላይ የተመሰረተ የምርመራ ሂደት የተከተለ ሥራ ማከናዎን ያስፈልጋል።

5. መቅጣት (ተጠያቂነትን ማረጋገጥ)፡- በሙስና ድርጊት ላይ የተሰማሩ አካላትን ፍህታዊ በሆነ መልኩ በህግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። ተጠያቂነት በተግባር ሲረጋገጥ እና አስተማሪ እርምጃዎች ሲወሰዱ በሌሎች ላይ የመከላከልና የመገደብ ስሜት ይፈጥራል። ከዚህ ባሻገርም በሙሰኞች የተዘረፉ ንብረቶችን በማስመለስ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

በመሆኑም፣ እነዚህ አምስቱ “መ” ዎች በአንድ ላይ ሲተገበሩ ለሙስና ምንም አይነት ክፍተት የማይሰጥ፣ ጠንካራና ግልጽነት ያለው ተቋማዊ አሰራር ለመገንባት ያስችላሉ።

ትውልድን በሥነምግባር፤ ተቋምን በአሰራር!

የሙስና ወንጀል መጠቆሚያ አማራጮችን፣ ወቅታዊ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት👇🏾

ሞባይል መተግበሪያ

ስልክ ተጠቃሚዎች
https://play.google.com/store/apps/details...

or iPhone ስልክ ተጠቃሚዎች
https://apps.apple.com/us/app/ncrs/id659366231

ለሀብት ማሳወቅና ምዝገባ፦ https://feaccears.gov.et/

ዌብሳይት፦ https://www.feacc.gov.et

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/feaccOfficial/

ቴሌግራም፦ https://t.me/feacc

ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-corrupti149

ትዊተር፦ https://twitter.com/EthiopiaFeacc በመወዳጀት ይከታተሉን።

26/06/2026
የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤው የሚመከርባቸው 8ቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች  👇👇1.  የሀገር ግንባታ ጉዳይ2.  የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ3.  የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ...
24/06/2026

የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤው የሚመከርባቸው 8ቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች 👇👇

1. የሀገር ግንባታ ጉዳይ

2. የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ

3. የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ

4. የሐይማኖት ጉዳዮች

5. የተቋማት ግንባታ የህግ የበላይነት እና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ

6. ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች

7. ሙስና እና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች

8. የሰላም ግንባታ ጉዳዮች ናቸው ።

ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለሀገራችን 🇪🇹

20/06/2026
በአፋር ክልል ለባሕላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና ለመስጠት እና ለማቋቋም በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው***************************የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር...
18/06/2026

በአፋር ክልል ለባሕላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና ለመስጠት እና ለማቋቋም በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው
***************************
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር በመተባበር፣ በክልሉ የባሕላዊ ፍርድ ቤቶችን እውቅና ለመስጠት እና ለማቋቋም በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከክልሉ የአገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ለሁለት ቀናት የሚቆይ ውይይት በሰመራ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የባሕል ፍርድ ቤቶች መደበኛውን የፍርድ ሂደት በማገዝ ሰላምን ለማረጋገጥ የማይተካ ድርሻ እንዳላቸው በተጠቆመበት በዚህ የውይይት መድረክ፤ አዋጁ ሙሉ በሙሉ ጸድቆ ሥራ ላይ ሲውል የአካባቢውን ማኅበረሰብ ፈጣን እና ቀልጣፋ የፍትሕ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታመናል፡፡

የአዋጁ መጽደቅ ዋና ዓላማም ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች በቂ እውቅና አግኝተው የፍትሕ ሥርዓቱ አጋዥ እንዲሆኑ ማብቃት እንደሆነ በውይይቱ ላይ ተገልጿል፡፡ እስካሁን ዘጠኝ ክልሎች ባሕላዊ ፍርድ ቤቶችን አቋቁመው ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፣ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥትም የአዋጁን ረቂቅ በማዳበር አጽድቆ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ረቂቅ ሰነድ የቀረበ ሲሆን፤ በተጨማሪም ሕግ የማውጣት አስፈላጊነትና ሥልጣን፣ የፍትሕ ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን አዳዲስ አቅጣጫዎች፣ የባሕላዊ ፍርድ ቤቶች እውቅና አሰጣጥና አደረጃጀት፣ እንዲሁም ስለ ባሕላዊ ፍርድ ቤቶች ሥልጣንና አካሄድ አስመልክቶ የመነሻ ሐሳብ ቀርቦ ሰነዱን ለማዳበር የሚያስችሉ ግብዓቶችን ማግኘት ተችሏል፡፡

በውይይቱ ላይ የፍትሕ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳኞች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች እና ዑለማዎች ተሳትፈዋል፡፡

ምንጭ :- FDRE Ministry of Justice/ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር

ስርቆት የማህበረሰብ ትልቁ ነውርና የውድቀት ምልክት ነዉ። ስርቆት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የቁሳቁስ ማጣት ወይም የኢኮኖሚ ጉዳት ብቻ አይደለም፤ ከዚያ ባለፈ የሞራል፣ የባህል እና የማህበራዊ...
17/06/2026

ስርቆት የማህበረሰብ ትልቁ ነውርና የውድቀት ምልክት ነዉ።

ስርቆት በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የቁሳቁስ ማጣት ወይም የኢኮኖሚ ጉዳት ብቻ አይደለም፤ ከዚያ ባለፈ የሞራል፣ የባህል እና የማህበራዊ እሴቶች መደርመስ ትልቁ ማረጋገጫ ነው።

ስርቆት የማህበረሰብ ውድቀት ምልክት መህኑ መገለጫዎች፦

✍️. እምነትን ያጠፋል፦
አንድ ማህበረሰብ በሰላም አብሮ ለመኖር እርስ በርስ መተማመን ወሳኝ ነው። ስርቆት ሲነግስ ግን ያ እምነት ይጠፋል፤ ጎረቤት በጎረቤቱ፣ ዜጋው በዜጋው ላይ ጥርጣሬ ያሳድራል። እምነት በሌለበት ደግሞ ሰላምና አንድነት ሊኖር አይችልም።

✍️. የስራ ባህልን ያኮስሳል፦
"በጥላህ እረፍ፣ በላብህ እደር" የሚለው የቆየና የተከበረ ባህላችንን በመናቅ፣ ሰርቶ ከመለወጥ ይልቅ የሌላውን ጥረትና ድካም በአቋራጭ መውሰድን ያበረታታል። ይህም ወጣቱ ትውልድ በስራና በጥረቱ ከመቀየር ይልቅ በቀላሉ ለመበልጸግ ወደ ወንጀል እንዲያደላ ያደርጋል።

✍️. የደህንነት ስጋት ይፈጥራል፦
ስርቆት ባለበት ማህበረሰብ ውስጥ ሰዎች በገዛ ቤታቸውና በንብረታቸው ላይ ዋስትና ያጣሉ። ይህ ስጋት ደግሞ የሰዎችን የመኖርና የመስራት የስነ-ልቦና ነጻነት ይነጥቃል።

✍️. የኢኮኖሚ እድገትን ያደናቅፋል፦
ሌቦች በሰረቁት ልክ ሰሪውና አምራቹ አካል ተስፋ ይቆርጣል። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በስርቆትና በደህንነት እጥረት ምክንያት ይስተጓጎላሉ።

በአጠቃላይ ስርቆትን እንደ "ነውር" አለመቁጠር እና በቸልታ ማለፍ ማህበረሰቡን ወደ ከፋ የሞራል ውድቀት ይመራዋል። ስለዚህ ድርጊቱን በህግ ብቻ ሳይሆን፣ ከቤተሰብ ጀምሮ በማህበራዊ እሴቶችና በትምህርት ማውገዝ እንዲሁም የታማኝነትን ክብር ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል።

ሙስና የማህበረሰቡን ዘመቻ የሚጠይቅ አዳገኛ በሽታ ነዉሙስና በአንድ ማህበረሰብ ኢኮኖሚ፣ ፍትህ እና ሞራል ላይ የሚያደርሰው ውድመት በቀላሉ የሚገመት አይደለም፤ ልክ እንደ አደገኛ ወረርሽኝ በ...
16/06/2026

ሙስና የማህበረሰቡን ዘመቻ የሚጠይቅ አዳገኛ በሽታ ነዉ

ሙስና በአንድ ማህበረሰብ ኢኮኖሚ፣ ፍትህ እና ሞራል ላይ የሚያደርሰው ውድመት በቀላሉ የሚገመት አይደለም፤ ልክ እንደ አደገኛ ወረርሽኝ በሽታም የሀገርን እድገት ቀስ በቀስ ይበላል።

ይህን ታላቅ አደጋ ለመከላከልና ሙሉ በሙሉ ለማስወገድ የአንድ ተቋም ወይም የጥቂት አካላት ጥረት ብቻ በፊጹም በቂ አይሆንም።

ሙስና በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ውስጥ ራሱን ደብቆ የሚኖር በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ዜጋ በትኩረትና በነቃት ካልተከታተለው ለማስወገድ አስቸጋሪ ነው።

ግልጽነት እና ተጠያቂነት ሊሰፍን የሚችለው፣ ህብረተሰቡ የሙስና ድርጊቶችን በግልጽ ሲያጋልጥ፣ አድሎአዊ አሰራሮችን ሲቃወም እና ለአነስተኛም ሆነ ለከፍተኛ የሙስና ጥቆማዎች ተባባሪ ሲሆን ነው።

ሙስናን የመዋጋት ዘመቻው ትልቁ ምዕራፍ በየቤታችን፣ በየመስሪያ ቤታችን እና በየማህበረሰባችን ውስጥ ታማኝነትን፣ ሥነ-ምግባርን እና ግልጽነትን ባህል አድርጎ ማሳደግ ነው።

ሙስናን መዋጋት የሀገርን ህልውና እና የትውልድን እጣ ፈንታ የመታደግ ብሄራዊ ግዴታ ነው።

ይህንን አደገኛ በሽታ በጋራ በመመከት፣ ፍትሃዊ፣ ግልጽ እና በሥነ-ምግባሩ የታነጸ ማህበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጉዞ ላይ የማህበረሰቡ ሚና እና ቁርጠኝነት ሁልጊዜም ከፍተኛ ዋጋ አለው።

ጭዋነት ምንድን ነዉ?°°°°°°°°°°°°°°°%°°°°°°°°%%%°°°°°°°°°°°%%ጭዋነት ማለት መልካም ሥነ-ምግባር፣ ራስን መግዛት፣ ግብረገብነት እና ለሌሎች ሰዎች ያለን አክብሮት መግለጫ...
16/06/2026

ጭዋነት ምንድን ነዉ?
°°°°°°°°°°°°°°°%°°°°°°°°%%%°°°°°°°°°°°%%
ጭዋነት ማለት መልካም ሥነ-ምግባር፣ ራስን መግዛት፣ ግብረገብነት እና ለሌሎች ሰዎች ያለን አክብሮት መግለጫ ነው። አንድ ሰው በንግግሩ፣ በአካሄዱ፣ በሰዎች መካከል ባለው ግንኙነት እና በዕለት ተዕለት ሕይወቱ የሚያሳየው በጎና የተከበረ ማንነት ነው።

ጭዋ ሰው በንዴት፣ በደስታም ሆነ በጭንቀት ጊዜ ስሜቱ ለተለያዩ ነገሮች ተገዢ አይሆንም። ነገሮችን በምክንያት እና በትዕግሥት ይመዝናል። ሌላውን ሰው የማይጎዳ፣ የማይሰድብ እና የማይዘልፍ ንግግርን መጠቀም የጭዋነት ዋነኛ መገለጫ ነው።

የሰዎችን ሐሳብ ማክበር፣ ሳያቋርጡ በጥንቃቄ ማዳመጥ እና የተለያየ ሐሳብ ያላቸውን ወገኖች በነጻነት ማስተናገድን ይጨምራል። ራስን ከፍ ከፍ አድርጎ ሌላውን ዝቅ አድርጎ ማየት አይችልም። በዕድሜ፣ በእውቀትም ሆነ በኃላፊነት የሚበልጡትን ማክበር፣ እኩያዎችን ማፍቀር፣ እንዲሁም ከራስ በታች ያሉትን በርኅራኄ መመልከት ነዉ።

ጭዋነት በሰው ፊት ብቻ የሚለበስ ጭንብል ሳይሆን፣ ሰው በሌለበትም ጭምር የሚተገበር የውስጥ ማንነት ነው። የገቡትን ቃል መፈጸም እና በኃላፊነት ስሜት መንቀሳቀስ ማለት ነዉ።

ማኅበረሰቡ የሚጠላቸውን መጥፎ ድርጊቶች (እንደ ስርቆት፣ ውሸት፣ እና ሌሎችን ማግለል) ያሉትን ፈፅሞ ይጠላል።

በሀገራችን ባህል ጭዋነት ከሃይማኖታዊ እና ከማኅበራዊ የግብረገብነት ትምህርቶች ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው፤ ትውልድን የሚገነባ መሠረት ተደርጎም ይታያል።

በአጠቃላይ ጭዋነት የአንድ ሰው የውስጥ ስብዕና ውበት መገለጫ ሲሆን፣ በአንድ ማኅበረሰብ ውስጥ ሰላም፣ መተማመን እና አንድነት እንዲሰፍን የሚያደርግ ዋነኛ መሣሪያ ነው።
ቅን እንሁን✅👏

Address

Afar
Afar
AFAR.GOV.ET

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fanti-Rasuk Qadli Miracsenta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share