Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ

Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት Security Guard

ከመስጅድ ግቢ የአራት ሰዎችን ጫማና ልብሶችን ሰብስበው ይዛ ልወጣ የነበረ ተጠርጣሪ መየዙ ተገለፀ።ነሐሴ 26/2018 ዓም ሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ በሀላባ ዞን አቶቲ ወረዳ በጉባ ከተማ ከመስ...
01/09/2026

ከመስጅድ ግቢ የአራት ሰዎችን ጫማና ልብሶችን ሰብስበው ይዛ ልወጣ የነበረ ተጠርጣሪ መየዙ ተገለፀ።

ነሐሴ 26/2018 ዓም ሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ

በሀላባ ዞን አቶቲ ወረዳ በጉባ ከተማ ከመስጅድ ግቢ አቶ ጀማል ኡመር የተባለው ግለሰብ ሰዎች 7:00 ሰለት መቆማቸውን አረጋግጦ የአራት ሰዎችን ጫማና ልብስ ይዞ ልወጣ ስል እጅ ከፍንጅ መያዙ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪ ግለሰብ የቁፌ ቀበሌ አራዶ ንዓስ ነዋሪ ስሆን በተያዘበት እጅ ከፍንጅ ስርቆት ወንጀል በአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፖሊስ በጊዜያዊ ማቆያ በምርመራ ለይ እንደሚገኘው ተገልጿል።

ስለዚህ መሠል ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ወደ መስጅድ ስገቡ የያዛችሁትን ንብረት በጥንቃቄ እንድትይዙ እናሣስባለን።

ወንጀልን በጋራ እንከላከል !!

የቅጥር ማስታወቂያየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾታ ተ...
30/08/2026

የቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾታ ተዋፅዖን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ተመልምለው በተቋሙ ባሉት ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ተመድበው ማገልገል የሚፈልጉ ዕጩ ፖሊሶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

ዕጩ ተመልማዮቹ ምልመላው ተጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥልጠና ማዕከል ገብተው ሥልጠና ከመጀመራቸው በፊት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በሚያዘው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አማካይነት የሚሰጣቸውን ሥልጠና በሚገባ በመከታተል ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሥልጠና ቆይታ ጊዜያቶችም በማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ በኩል የምግብ፣ የመኝታ፣ የሕክምና እና ለሥልጠናው የሚያስፈልጉ የአልባሳት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የኪስ ገንዘብ ይሰጣል።

ሥልጠናው ሲጠናቀቅም እያንዳንዱ ተመራቂ በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሰረት ወርሃዊ ደመወዝና የቀለብ ሂሳብ የሚከፈለው ሆኖ በተቋሙ ልዩ ልዩ የስራ አልባሳት፣ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በካምፕ የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።

ተመርቀው ፖሊሳዊ የሙያ አገልግሎት በሚያበረክቱባቸው ጊዜያትም በተቋሙ ውስጥ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ደንብ እና የስልጠና መመሪያዎች መሠረት በሚወጡ መመዘኛዎች አማካኝነት በልዩ ልዩ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች በመወዳደር ተጠቃሚ የመሆን ሠፊ ዕድል የሚጠብቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በደስታ ይገለፃል።
የምልመላ መስፈርት (መመዘኛ)

1. ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች፣

2. ለሕገ-መንግስንቱና ለሀገሪቱ ሕጎች ተገዥና ታማኝ የሆነ/የሆነች፣

3. ከማናቸውም ደባል ሱሶች የፀዳ/የፀዳች እና መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ያላት፣

4. በሚመለመልበት አካባቢ ነዋሪ ስለመሆኑ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

5. ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር፣ ከአካባቢው ፖሊስ እና ከተማረበት ትምህርት ቤት የተዘጋጁ ቅፆችን በማስሞላት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

6. በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን/የምታምን፣

7. ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤናማ መሆኑን/መሆኗን በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

8. ዕድሜው/ዋ ከ18 እስከ 25 ዓመት ያላነሰና ያልበለጠ/ያልበለጠች፣

9. የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣

10. የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች እንዲሁም ትምህርት ያጠናቀቀበት ካርድ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

11. ብዝሃነትንና አካታችነትን ለማረጋገጥ ሲባል ያልተካተቱና አነስተኛ ቁጥር ባለባቸው ብሔሮች አካባቢ ለሚመለመሉ ወጣቶች ቢያንስ 6ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች፣

12. ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ የሆነ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ የሆነች፣

13. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በተደነገገው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በየትኛውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተቋም የሥራ አከባቢ ተመድቦ/ተመድባ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፣
14. ከአሁን በፊት በወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ/ያልተቀጣች ወይም የወንጀል ሪከርድ የሌለበት/የሌለባት የአሻራ ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኘ የሆነ/የሆነች

15. ከአሁን በፊት በማንኛውም የፖሊስ እና የመከላከያ ሰራዊት ተቋም ሥልጠና ያልተሳተፈ/ያልተሳተፈች ወይም በአባልነት ተቀጥሮ ያልሰራ/ያልሰራች፤

16. ያላገባ እና ያልወለደ ወይም ያላገባች እና ያልወለደች፣
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም ዕጩ ተመልማይ በምዝገባ ወቅት ከላይ ከተገለፁት መመዘኛዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ይዞ በመቅረብ መመዝገብ ይኖርበታል፡፡

1) የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና የማይመለስ 1 ፎቶ ኮፒ፣

2) ከ2 ዓመት በላይ ነዋሪነትን የሚያመለክት የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ ይዞ መቅረብና መመዝገብ ይጠበቅበታል፣

3) የተመልማዩን ማንነት አጠቃላይ ሁኔታ ለመገንዘብ እንዲያስችል ታስቦ በሥልጠና ማዕከሉ አማካይነት የተዘጋጀውን ፎርም ከምዝገባ ጣቢያው በመቀበል የመጨረሻ አመት ካጠናቀቀበት ወይም ካጠናቀቀችበት ትምህርት ቤት፣ ከመኖሪያ ቀበሌና ከአከባቢው የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጽ/ቤት ቀርቦ ወይም ቀርባ የማስሞላትና በተጠቀሰው የቀን ገደብ መሰረት ለምልመላ ጣቢያው አስቀድሞ ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4) ሴት ተወዳዳሪዎች ይበረታታሉ።
ማንኛውም ምልምል ከ500 ብር በላይ፣ ወርቅ፣ የተለያዩ ስለታማ ነገሮችን፣ ምግብ ነክ ነገሮች እና ከሁለት ቅያሪ ልብስ በላይ ይዞ ወደ ማሰልጠኛው ማዕከል መግባት የተከለከለ ነው፡፡

የምዝገባ ጊዜው ከጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፣ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በየክልሉ በሚገኙ ዞኖች፣ ወረዳዎች እና በምልመላ ጣቢያዎች በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።ሠ

🏆 እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉የዌራ ወረዳ ምክርቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በ2018 የዌራ ወረዳ  ሰላምና ፀጥታ አስተደደር ጽ/ቤት የላቀ አፈጻጸም በመስመዘገ...
30/08/2026

🏆 እንኳን ደስ አላችሁ! 🎉
የዌራ ወረዳ ምክርቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በ2018 የዌራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ አስተደደር ጽ/ቤት የላቀ አፈጻጸም በመስመዘገቡ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።
ነሐሴ 24/12/2018 ዓ.ም ====================================
የዌራ ወረዳ ምክርቤት 4ኛ ዙር 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በ2018 የዌራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ አስተደደር ጽ/ቤት የላቀ አፈጻጸም በመስመዘገቡ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።
🏆ይህ ውጤት በወረዳው የሚገኙ አመራሮችና በጽ/ቤቱ ሠራተኞች በትጋት፣ በተጠያቂነት፣ በቅንጅትና በተቀናጀ አሠራር የሰሩት የጋራ ጥረት ውጤት ስሆን የተገኘው ዕውቅና የመጨረሻ ግብ ሳይሆን ለበለጠ ስኬት መነሻ መሆኑን በመገንዘብ፣ በ2019 ዓ.ም የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በተሻለ ትጋትና ትብብር ለመሥራት ዝግጁ እንደሆነ የዌራ ወረደ ሰላምና ፀጥታ ኃለፍ አቶ በህረድን ኬዳ ገልጸዋል።

 #በትላንት ዕለት በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በሀቢቦ ፉራና ቀበሌ እና በሙደ ማያፋ ቀበሌ መሀል በብላቴ ወንዝ ሞታ የተገኛችሁ እናት ቤተሰብ ከሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ከማጃ ቀበሌ መጥተው የሟችን ...
29/08/2026

#በትላንት ዕለት በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በሀቢቦ ፉራና ቀበሌ እና በሙደ ማያፋ ቀበሌ መሀል በብላቴ ወንዝ ሞታ የተገኛችሁ እናት ቤተሰብ ከሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ከማጃ ቀበሌ መጥተው የሟችን አስክሬን መውሰዱን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ረ/ኢንስፔክተር ነስሩ አወል ገልጸዋል።

ኢንስፔክተሩ አያይዘው ሟች ከማጀ ቀበሌ ወደ ላይኛው በደኔ ከአራት ቀነት በፍት ለመውሊድ ብለ ከቤት እንደወጣች ከቤተሰቡ መረጀ እንደወሰደው ገልፀዋል።

በመጨረሻም ሰዎች የለመታወቂያ በመንቀሳቀስ እለት ተእለት ጉዟቸው በብዙ ጉደዮች ለይ የማንገላታትና መሠል አደጋዎች በሚደረሱበቸው ጊዜ እያታንገላተቱ ስለመሆኑን ጠቅሰው የሚመለከተው አከል የነዋሪነት መታወቂያ እንድሰጣቸው በማሳሰብ ይህንን የሟች አስክሬን ለቤተሰቡ እንድደርስ ለተባበሩት የፔጃችን ተከታዮች ምስጋና አቅርበዋል።

ነሐሴ 22/2018ዓም ሀላባ ቁሊቶ

የሀላባ ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም በ2018ዓም በጀት አመት የላቃ ውጤት በማስመዝገቡ የሜዳሊያና የሰርተፍኬት ምስክር ወረቀት ተበራክቷል።የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት...
07/08/2026

የሀላባ ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም በ2018ዓም በጀት አመት የላቃ ውጤት በማስመዝገቡ የሜዳሊያና የሰርተፍኬት ምስክር ወረቀት ተበራክቷል።

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በፓርቲ ሥራ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ አካላት እውቅና ሰጥቷል ።

በዚህም መሠረት በ2018 በጀት ዓመት በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አስተዳደር ህብረት ዘርፍ ካሉ ቤተሰቦች የሀላባ ዞን ማረሚያ ተቋም ብልጽግና ቤተሰብ #1ኛ ደረጀ በመዉጣት የሜዳሊያና የሰርቲፊኬት ተሸላሚ በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ ያለን።

የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ቤተሰብ በ2018 በፓርቲ ስራዎች ከአስተዳደር የብልጽግና ህብረት ቤተሰቦች ውስጥ በልማት ትሩፋት ፣ በግቢ ኮሪደር ልማት ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በማውጣት የሜዳሊያና የሰርቲፊኬት ተሸላሚ በመሆን በበጀት ዓመቱ በርካታ ውጤቶችን አስመዝግቦ አልፏል ።

የተመዘገበው አኩሪና አስደሳች ውጤት ለቀጣዩ ሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥር ትልቅ እገዛ ይሆነናል ።

የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ከጥልፍልፍ ችግር ወጥቶ ለዝህ ውጤት እንዲበቃ ትልቅ ድርሻ ለነበራቸው አካላት ምስጋና መቅረቡ ተገቢ በመሆኑ በመጀመሪያ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን፣ የሀላባ ዞን አስተዳደር የብልጽግና ህብረት አመራሮች፣ የሀላባ ዞን ምክር ቤት ፣የሀላባ ዞን ፍትህ መምሪያ ፣ የቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ማኔጅመንት አካላትና መላው ታታሪ ፖሊስ አባላት ሠራተኞች እንድሁም የሕግ ታራሚዎች፣ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።
!!
!!

የትራፍክ አደጋ የሚያበቃለት ስላልሆነ ደንብ የጣሱ ተሽከርካሪዎች ቁጥጥርን በአበረታች ሁኔታ መቀጠሉ ተገለፀ።።።።።።።01/12/2018 ዓ.ም ዌራ፤።።።።።  የትራፍክ አደጋን ለመከላከል ደንቡ...
07/08/2026

የትራፍክ አደጋ የሚያበቃለት ስላልሆነ ደንብ የጣሱ ተሽከርካሪዎች ቁጥጥርን በአበረታች ሁኔታ መቀጠሉ ተገለፀ።

።።።።።።01/12/2018 ዓ.ም ዌራ፤።።።።።

የትራፍክ አደጋን ለመከላከል ደንቡን የጣሱ ተሽከርካሪዎችን ትራፍክ ፖሊስ ተቆጣጥረዉ እርምጃ መዉሰዱን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የትራፍክ አደጋ መከላከል ማስተባበሪያ ኃላፊ ረ/ኢ/ር ፉዓድ ታጁ ገለፁ።

ከተፈቀደዉ በላይ ርቀት ስያሽከረክሩ የተገኙ የባለ ሦስት እግር ባጃጆችንና የባለሁለት እግር ሞተር ተሽከርካሪዎችን እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ጠቅሰው የትራፍክ አደጋን ለመከላከል ስባል እርምጃውም የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።

ኃላፊዉ አክለዉም ለማንኛውም አሽከርካሪ የትራፍክ ደንብን መተላለፊ ከጥቅሙ ይበልጥ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ የትራፍክ አደጋ ተጋላጭነቱን ለመቀነስ ከግንዛቤ መፍጠር ስራ ጀምሮ ጥሰቱን ለሚፈፅሙ አካላት የደንብ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊዉ መሆኑን ገልፀው ጥንቃቄ እንድያደርጉም አሳስበዋል።

።።።።የትራፍክ አደጋን በጋራ እንከላከል።።።።
የወረዳዉ ትራፍክ ማኔጅመንት

በሸምሰዲን ከድር
ረ/ኢ/ር

የሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆነው በሚቆይባቸው ወቅቶች ስለሚሰጠቸው አገልግሎቶች የተሰጠ መግለጫ። በፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1/2016 በአንቀፅ 59(2) እና የዳኝነ...
07/08/2026

የሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ የመጀ/ደረጃ ፍርድ ቤት ዝግ ሆነው በሚቆይባቸው ወቅቶች ስለሚሰጠቸው አገልግሎቶች የተሰጠ መግለጫ።

በፍርድ ቤቶች አዋጅ ቁጥር 1/2016 በአንቀፅ 59(2) እና የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 2/2016 በአንቀጽ 39(1) መሠረት ከነሐሴ 1 እስከ መስከረም 30 ድረስ ዝግ ሆነው እንደሚቆዩና የዳኞች የዓመት እረፍት ግዜያቸው እንደሚሆን በተደነገገው መሠረት ከነሐሴ 1/2018 እስከ መስከረም 30/2019 ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናቶች ዝግ ሆነው የሚቆዩ ይሆናል።

ሆኖም ፍርድ ቤታችን ዝግ ሆነው በሚቆዩባቸው ግዜያቶች ሁሉ እጅግ አንገብጋቢና አጣዳፊ የሆኑ ጉዳዮች ፤
1. በወንጀል ጉዳዮች
▪️የዋስትና ጥያቄዎች
▪️የብርበራ ፍቃድ
▪️የመያዣ ትዕዛዞች
▪️አመክሮ
▪️ቅጣት ይደመርልኝ ጥያቄ
▪️አካልን ነፃ ለማውጣት የሚቀርቡ አቤቱታዎች

2. በፍትሐብሔር ጉዳዮች
▪️የቀለብ ጉዳዮች
▪️በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የደመወዝ ክርክሮች
▪️በስምምነት ፍርድ እንዲሰጥ የሚቀርቡ አቤቱታዎች
▪️በስምምነት የተሰጡ ፍርዶች አፈጻጸም ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎች

3. አዲስ መዝገቦች
▪️አዲስ የወንጀልና የፍትሐብሔር መዝገቦችን መክፈት
▪️ቀጠሮ መቀበልና ማስያዝ
ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች በተረኛ ዳኛ አማካኝነት በመቀጠል እንደሚሰጡ የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ መሐመድሣኒ ኑርዬ ገልጸዋል።

መግላጫው፦ የዌራ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው

የሞተር ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተያዛ።ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም በሀለባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ አድሱ ከተማ አስተዳደር ጀርባ ሚሚ ምግብ ቤት...
06/08/2026

የሞተር ስርቆት የፈፀመው ግለሰብ በህብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ ተያዛ።

ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም በሀለባ ዞን ቁሊቶ ከተማ ውስጥ ልዩ ስሙ አድሱ ከተማ አስተዳደር ጀርባ ሚሚ ምግብ ቤት በር ከቀኑ 10:30 አከባቢ አቶ ትግስቱ ሌጋሞ የተባለው ተጠርጣሪ ማኢካላዊ እትዮጵያን ክልል ሀዲያ ዞን ምስራቅ በደዋቾ ወረዳ ነዋር ስሆን 100cc ኮክሰር ሞተር ሰይክል አንስቶ ወደ ሾኔ መስመር እያነዳ ሲሄድ በህብረተሰብ ጥቆማ በከምባታ ዞን አድሎ ወረዳ ተጠርጣሪው ከና ሞተሩ በፖሊስ እጅ ከፍንጅ መያዝ ተችሏል ።

ወንጀልን በጋራ እንከላከል !!
የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ህዝብ ግንኙነት ።

ዌረ ወረደ ፖሊስ የስተፊ ስረ አመረሮችና አበለቱ በተቋሙ ግብ ውስጥ የችግኝተከለ ዝግጀት  መደረጉን አስተወቀ::*********************************************ሀምሌ 3...
06/08/2026

ዌረ ወረደ ፖሊስ የስተፊ ስረ አመረሮችና አበለቱ በተቋሙ ግብ ውስጥ የችግኝተከለ ዝግጀት መደረጉን አስተወቀ::
*********************************************
ሀምሌ 30/2018ዓ/ም (ዌ.ወ.ፖ)

የጽ/ቤቱ አመረርና አበላቱ የተጣለባቸውን የስራ ኃላፊትነትን በቁርጠኝነት በተግባር ላይ ሆነው በማከናወን ጎን ለጎን በተቋሙ ግቢ ውስጥ የከዚህ ቀደሙን ችግኞችን በመንከባከብ እና እንዲሁም ተጨማሪ የችግኝ ተከላ ቦታዎችን በማዘጋጀት አሻራቸውን ለማኖር እየተጉ ይገኛሉ።

ወንጀልን በጋራ እንከላከል!!

ልጂት ከቤተሰቦቿ ጋር ተገናኘች!!በማህበራዋ ትስስር ገፃችን ላጋራችሁ ትብብራችሁ በተቋሙ ስም ምስጋናችን ከልብ ነው።
04/08/2026

ልጂት ከቤተሰቦቿ ጋር ተገናኘች!!
በማህበራዋ ትስስር ገፃችን ላጋራችሁ ትብብራችሁ በተቋሙ ስም ምስጋናችን ከልብ ነው።

Address

City
Alaba K'ulito
POLICE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Halaba Zone Wera Woreda Police Office pageበሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገፅ:

Shortcuts

Share