በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት, Political organisation, atoti ulo Guba, Alaba K'ulito.

ይህ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ይፋዊ የፌስቡክ የሚዲያ ገፅ ስሆን አጠቃላይ ወቅታዊና መደበኛ የፓርቲ ስራዎች ዘወትር ይተላለፋል።
👇ከታች ያለውን Follow በታን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
https://www.facebook.com/profile.php?id=100069137263054

21/08/2026
የመሶብ አንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊነትን በማረጋገጥ የህዝብን እንግልት በመቀነስ ረገድ እያሳየ ያለው አበረታች ጅምር ስራ አጠናክሮ ልቀጥል ይገባል፦ አቶ ሙህዲን ሁሴን***የሀላ...
21/08/2026

የመሶብ አንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊነትን በማረጋገጥ የህዝብን እንግልት በመቀነስ ረገድ እያሳየ ያለው አበረታች ጅምር ስራ አጠናክሮ ልቀጥል ይገባል፦ አቶ ሙህዲን ሁሴን
***
የሀላባ ዞን አስተዳደር ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር "የመሶብ" አንድ ማዕከል ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት በመገኘት ምልከታ አድርገዋል።

የማዕከሉ ሥራ አስኪያጅ ሙባረክ ለማ እንዳብራሩት ማዕከሉ መጀመሪያ ላይ 8 (ስምንት) ዘርፎች አገልግሎት ይሰጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ተጨማሪ ዘርፎችን በመጨመር አገልግሎቱን ወደ 13 (አስራ ሶስት) ማደጉን ገልጸዋል።

ይህ እድገት ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን የተለያዩ መሠረታዊ አገልግሎቶች በአንድ ጥላ ስር በፍጥነት እንዲያገኝ ትልቅ እገዛ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የዞኑ አስተዳደር ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደገለጹት ተቋሙ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት ይበልጥ በማቀላጠፍ የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋል።

ተቋሙ ህብረተሰቡን ከጽ/ቤት ወደ ጽ/ቤት ሳያመላልስ የተሟላና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ረገድ እየሰራ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

የዜጎችን እርካታ ማረጋገጥ የብልጽግናና የመልካም አስተዳደር ዋነኛ መለኪያ መሆኑ ታምኖበት ለዚህም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የሀገር አቀፍ ኢኒሼቲቭ የሆነውን "የመሶብ" ስራ ስኬታማና ውጤታማ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላትና ሰራተኞች በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ክቡር አቶ ሙህዲን አብራርተዋል።

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት ፈፃሚመዘጋጃ መድረክ ላይ ከዘርፉ ንዑሳን ኮሚቴዎች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረመ።=======...
21/08/2026

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት ፈፃሚመዘጋጃ መድረክ ላይ ከዘርፉ ንዑሳን ኮሚቴዎች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራረመ።
========
(ነሃሴ፣15/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ
በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመተግበር የሚያስችል የግብ ስምምነት ፈጽሟል። ስምምነቱ የተፈረመው ከሁሉም ማህበራዊ መሰረት አደረጃጀት ዘርፍ ንዑሳን ኮሚቴዎች ጋር ሲሆን:-

ይህን ስምምነት ለመድረስ፣ የዘርፉ አመራሮች የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ የታዩትን ጥንካሬዎችና ድክመቶች በጥልቀት ገምግመዋል። ግምገማውን ተከትሎም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አካል እንዲሆኑ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

ይህ መድረክ የፓርቲውን አደረጃጀት ዘርፍ ንዑሳን ኮሚቴዎችን በሙሉ ያሳተፈ ሲሆን፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችን በአንድነት ለመፈጸም የጋራ ቁርጠኝነት የተገለጸበት ነው። የግብ ስምምነቱ በወረዳው የፓርቲውን አደረጃጀት የማጠናከር እና በኢኮኖሚ በማህበራዊ በፖለቲካና በውጭ ግንኙነት የተቀመጡ የፓርቲውን ፕሮግራምና በወረዳው የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው ይጠበቃል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል !!

‎በሀላባ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብራ ሀይል ዙሪያ ለምክክር የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።‎‎በሀላባ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳ...
21/08/2026

‎በሀላባ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብራ ሀይል ዙሪያ ለምክክር የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ ።

‎በሀላባ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ የፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት አስወጋጅ ግብራ ሀይል ዙሪያ ለምክክር የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደዋል ።

‎በመድረኩ ለዉይይት የተዘጋጁ ሰነዶች በሀላባ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ በአቶ ገረሙ ሱንክቻ እና በሀላባ ዞን ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ በወ/ሮ እመቤት ጀማል በመቅረብ ሰፈ ያለ ዉይይት ተደርጎበታል ።

‎የዉይይት መድረኩም በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ሀላፊ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ በአቶ ራማቶ መሀመድ እና የሀላባ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊ በገራሙ ሱንክቻ እንድሁም በዞኑ ሴቶች እና ህጻናት መምሪያ ሀላፊ በወ/ሮ እመቤት ጀማል ተመርቷል ።

‎በመድረኩ በዞኑ የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን እና እንደ አስገድዶ መድፈር ፣ ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያሉ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ረገድ የተከናወኑ ተግባራትና የታዩ ክፍተቶች በስፋት ተገምግመዋል።

‎በዚህም -የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ሀላፊ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ በአቶ ራማቶ መሀመድ እንደገለጹት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስወገድ የባህሪ እና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስፈልግ በመጠቀስ፣ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራው እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል (ቀበሌ) ድረስ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል

‎፧ አቶ ራማቶ አክለዉም በሴቶች የምደርሰዉ ጾታዊ ጥቃት እና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ያሉ ድርጊቶች የማህበረሰቡን ደህንነትና የሴቶችን የወደፊት ተስፋ የሚያጨልሙ በመሆናቸው፣ በባህላዊና ሃይማኖታዊ መድረኮችም ጭምር በግልፅ ሊኮነኑና ሊወገዙ እንደሚገባ ተገልጿል።

‎የሀላባ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፍ አቶ ገራሙ ሱንክቻ እንደገለጹት የተቀናጀ የግብረ ኃይል እንቅስቃሴ ማድረግ የጉዳቱን ስፋት ለመቀነስና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑ ተመልክቷል። በተለይም ጥቃት አድራሾችን ለህግ በማቅረብ ረገድ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸው በአጽንኦት ተነግሯል ።

‎የሀላባ ዞን ሴቶች እና ህጻናት መምሪያ ሀላፊ በወ/ሮ እመቤት ጀማል እንደተናገሩት ፆታዊ ጥቃትና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ማስወገድ የሴቶችና ህፃናት መምሪያ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላው ህብረተሰብ እና የሁሉም ተቋማት ኃላፊነት ነው ያሉት ወ/ሮ እመቤት ጀማል ሁሉም የዚህ ቤት ባለድርሻ አካላት በየመዋቅራቸው የጀመሩትን የክትትልና የቁጥጥር ሥራ አጠናክረው በመቀጠል፣ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እና ለተጎጂዎች አስፈላጊውን ፍትህና ድጋፍ ለማስገኘት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸው በአጽንኦት አስገንዝበዋል ።

‎ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶችና ህፃናት ፈጣን ፍትህና ሁለንተናዊ የህክምና እንዲሁም የስነ-ልቦና ድጋፍ የሚያገኙበት አሰራር ይበልጥ ሊቀላጠፍ እንደሚገባ ተመልክቷል።

‎ጥቃት አድራሾች በህግ ጥላ ስር ውለው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ለማድረግ በፖሊስ፣ በፍትህ አካላትና በማህበረሰብ አደረጃጀቶች መካከል ያለው የመረጃ ልውውጥና የቅንጅት ስራ ከቀድሞው በበለጠ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል

‎በምክክር መድረኩ የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችም ድርጊቶቹን በማህበረሰቡ ዘንድ ለማስወገድ በባህላዊ መንገድ በመተቸት መስመር ለማስያዝ በትኩረት እንደሚሰሩ ተነግሯል ።

‎​በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በየተሰማሩበት ዘርፍና መዋቅር የጀመሩትን ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር፣ ለሴቶችና ህፃናት ምቹ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ከጥቃት ነፃ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተው መድረኩ በስኬት ተጠናቋል።

‎በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ የዞኑና የወረዳዎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፍትህና የፀጥታ አካላት (ፖሊስ፣ ዐቃቤ ህግና ፍርድ ቤት)፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀት ተወካዮች ተገኝተዋል።
‎ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል

ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው መከላከል አብይና ንኡስ ኮሚቴ የእስካሁን ስራዎችና ቀጣይ ተግባራዊ የሚደረገው ስራ በተመለከተ ውይይት ተካሄደ =====ነሀሴ 1...
21/08/2026

ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው መከላከል አብይና ንኡስ ኮሚቴ የእስካሁን ስራዎችና ቀጣይ ተግባራዊ የሚደረገው ስራ በተመለከተ ውይይት ተካሄደ
=====

ነሀሴ 15/2018 በሀላባ ዞን ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይና ንኡስ ኮሚቴ የእስካሁን ስራዎችና ቀጣይ ተግባራዊ የሚደረገው ስራ በተመለከተ ውይይት ተካሄደዋል።

"ውስን የሆነውን የመሬት ሀብታችንን ከህገ-ወጥ ወረራና ምዝበራ በመከላከል፣ ፍትሐዊ የከተሞች ዕድገትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል ህገወጥን ለመከላከል ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በዛሬው ዕለትም ህገወጥ ግንባታን ለመከላከል የተቋቋመው አብይና ንኡስ በሰፊው ወይይት በማድረግ የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።

የውይይት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደገለጹት መሬት ላይ የሚስተዋሉ ህገወጥና ብልሹ አሰራሮችን በጋራ መከላከል ይገባል ብለዋል።

የህገ-ወጥ መሬት ወረራ መከላከል አብይና ንኡስ ኮሚቴ የበኩላቸውን መውጣት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል።

በኢንቨስትመንት፣ በኢንተርፕራይዝ፣ በህብረት ስራ ማህበራት፣ በተለያዩ አካላት የተፈጸሙ ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገወጥ ግንባታዎች፣ ከምትክ ቦታ ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ህገወጥነት፣ በጥቅም ትስስርና በሌሎች ምክንያቶች መሬቶች ላይ እስከአሁን የተሰሩ ስራዎች በሰፊው ተመልክቷል።

በመድረኩም የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የቤት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ አቶ ንጉሴ አቢሶ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ፣ የሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ዋና ሀላፊ ተወካይና የመምሪያ ምክትልና የፕላን ዘርፍ ሀላፊ ኢንጂነር ሀቢስሰ፣ የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆችና ሌሎች የአብይ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።ስል የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

እንኳን ደስ አላችሁ!! አቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተሸላ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከዞኑ ከሉ መዋቅሮች 2ኛ ደረጃ  በማውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ በ2018 በጀት...
21/08/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!!
አቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተሸላ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከዞኑ ከሉ መዋቅሮች 2ኛ ደረጃ በማውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

በ2018 በጀት ዓመት አቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የዕውቅና ሽልማቱ ቀጣይ ከዚህ የተሸላ ህዝብን ለመገልጋል የሚያናሰሳ ስለሆነ ለተበረከተው የእውቅና ሽልማት ምስጋና አቅርባዋል ።

እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን !!

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለሁሉም ማህበራዊ መሰረት አደረጃጀት ዘርፍ ንኡሳን ኮሚቴ አመራሮች"የአባላት ምልመላ፣ ግንባታና ስንብት የአፈጻጸም መመሪያ" ዙሪያ ስ...
21/08/2026

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለሁሉም ማህበራዊ መሰረት አደረጃጀት ዘርፍ ንኡሳን ኮሚቴ አመራሮች"የአባላት ምልመላ፣ ግንባታና ስንብት የአፈጻጸም መመሪያ" ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
========
(ነሃሴ፣15/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ለሁሉም ማህበራዊ መሰረት አደረጃጀት ዘርፍ ንኡሳን ኮሚቴ አመራሮች"የአባላት ምልመላ፣ ግንባታና ስንብት የአፈጻጸም መመሪያ" ዙሪያ ስልጠና ተሰጥቷል ።

ስልጠናው በወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ሀላፊ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በሆኑት አቶ ባህረዲን ሪቦ አስተባባሪነትና አቅራቢነት የተካሄደ ሲሆን፣ ተሳታፊዎችም ጠንካራ አባላትን በማደራጀት ፓርቲው ተቋማዊ አሰራርን እንዲከተልና ጤናማ የአሰራር ሥርዓት እንዲመሠርት የሚያስችል መመሪያ መሆኑን አስረድተዋል።

የስልጠናው ዋና ዋና ይዘቶች የፓርቲ አባልነትን የሚመለከቱ አጠቃላይ ድንጋጌዎችና ትርጓሜዎች፣ የአባላት ምልመላ መስፈርቶችና መንገዶች፣ የደጋፊ አባላት አደረጃጀትና ሚና፣ የእጩና የሙሉ አባልነት ማጽደቅ ሂደቶች፣ የአባላት አቅም ግንባታ ዘዴዎች እንዲሁም የአባላት ስንብት አይነቶችና አያያዝን ያካተቱ ናቸው። እነዚህም የብልፅግና ፓርቲን በጠንካራ አባላት ባለቤትነት በመገንባት የፖለቲካ ብቃታቸውን ለማረጋገጥ የወጡ መመሪያዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ስልጠናው በጋራ ጥያቄና መልስ እንዲሁም በውይይት መልክ የተካሄደ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት አደረጃጀቶቹ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና የመልካም አስተዳደርና ሌሎች የልማት ስራዎችን በተቀነጀና በተደራጀ መልኩ በግንባር ቀደምትነት መስራትና መሰተፍ እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል። በተጨማሪም፣ የተማሪ ምዝገባ፣ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራና የልዩ ዕቅድ አካል የሆኑ ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ተልዕኮዎችን ለማሳካት ጠንክረው እንድሰሩም መልዕክት ተላልፏል።
በመድረኩ የሁሉም ማህበራዊ መሠረት አደረጃጀት ዘርፍ ንዑሳን ኮሚቴ አመራሮችና አባላት ተገኝቷል ።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል !!

በወረዳው “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የክረምት ወራት በጎ ተግባር በማጠናከር፣ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፍርድ ቤት እና የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በጋ...
20/08/2026

በወረዳው “በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የክረምት ወራት በጎ ተግባር በማጠናከር፣ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፍርድ ቤት እና የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በጋራ በሴንቄሌ ቢጠና ቀበሌ ለአንድ አቅመ ደካማ ወገን የመኖሪያ ቤት ግንባታ አስጀመሩ።

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም. በተካሄደው የድጋፍ ሥነ-ሥርዓትም ቆርቆሮና ሌሎች መሰል የግንባታ ቁሳቁሶች ለአቅመ ደካማው ቤተሰብ አስረክበዋል።

በርክክቡ ወቅት ንግግር ያደረጉት የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ሱልጣን ሀምዳ፣ የድጋፉ ዓላማ በአቅም ውስንነት የሚገኙ ወገኖችን በመደገፍ የማህበረሰቡን የመረዳዳት፣ የአብሮነትና የበጎነት ባህል ማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል። የተከበሩ አቶ ሱልጣን አክለውም፣ በጎ ተግባር የግለሰብ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን የማህበረሰብ አብሮነትን የሚያጠናክር ተግባራዊ እሴት በመሆኑ፣ ተቋሙ በቀጣይም በተቋም ደረጃ የመደገፍ ሥራዎችን እንደሚያጠናክር አስገንዝበዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰመረዲን ሽፋሌ በበኩላቸው፣ ይህ ድጋፍ ተቋማት ከዕለት ተግባራቸው ባሻገር ለማህበረሰቡ ያላቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። በጎነትና አብሮነትን በማጠናከርም ለወረዳው የልማትና የማህበራዊ ትስስር ጥንካሬ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

የተጀመረው የአቅመ ደካማው ቤት ግንባታ ሥራም እስከሚጠናቀቅ ድረስ በትኩረትና በተቀናጀ መልኩ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በርክክቡ ወቅት የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ ሱልጣን ሀምዳ፣ የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰመረዲን ሽፋሌ እንዲሁም የየጽ/ቤቱ ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ተሳትፈዋል።

በጎነት ይገነባል፤ አብሮነት ያጠናክራል!
እንደ ማህበረሰብ በመደጋገፍ የተሻለች ኢትዮጵያን እንገንባ!

ዘጋቢ፦ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ፍርድ ቤት!!!!

‎‎በብልጽግና ፓርቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በሀላባ ዞን የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ የመግቢያ ውይይት አደረገ ‎‎ነሀሴ 14/2016 ዓ.ም...
20/08/2026

‎‎በብልጽግና ፓርቲ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በሀላባ ዞን የተሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ የመግቢያ ውይይት አደረገ

‎ነሀሴ 14/2016 ዓ.ም፤ሀላባ ቁሊቶ
‎በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት የክረምት ወራት የበጎ ተግባራት ስራውችን ድጋፋዊ ክትትል ለማድረግ በዛሬ የመግቢያ ውይይት አደረገ።

‎ውይይቱ አቶ አደም ጀማል የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ም/ሀላፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ በተገኘበት ተደርጓል።

‎በዚህ ወቅት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ፖሎቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ሀላፊ አቶ ዴማሞ ሀይሌ የሱፐርቪዥን ቡድን መሪ የሱፐርቪዥኑን አላማና ግብ አብራርተዋል።

‎የሱፐርቪዥኑ አላማ በዞኑ በየደረጃው
‎በክረምት ወራት እየተገበሩ ባሉት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ እና ክትትል ማድረግ ሲሆን የጋራ መግባባት ተፍጥረዋል።

‎የሱፐርቪዥኑ ስራው ጉድለቶች እንዲታረሙ ድጋፍ እንደሚደረግና ከነገ ጀምሮ በተመረጡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንደሚደረግ ተገልጿል።

‎በመድረኩም ላይም የሀላባ ዞን የክረምት በጎ ተግበር አብይ እና ቴክኒክ ኮሚቴ አመራሮች እና ሌሎች የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ተገኝተዋል ።

‎ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ በአስተዳደር ቤተሰብ ለሚገነባ ለአንድ አቅመ ደካማ የቆርቆሮና የምስመር  ድጋፍ ተደረገ =========(ነሐሴ፣14/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡ...
20/08/2026

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ በአስተዳደር ቤተሰብ ለሚገነባ ለአንድ አቅመ ደካማ የቆርቆሮና የምስመር ድጋፍ ተደረገ
=========
(ነሐሴ፣14/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ ብልፅግና ፓርቲ ሚዲያ በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በ1ኛ ጤፎ ቀበሌ በአስተዳደር ቤተሰብ ለሚገነባ ለአንድ አቅመ ደካማ የቆርቆሮና የምስመር ድጋፍ ተደርገዋል።

በድጋፉ ላይ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ምክትልና አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ባህረዲን ሪቦ፣የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ጀማል ቤያ እንዲሁም የወረዳው አመራሮች ባለድርሻ አካላቶች ተገኝተዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

Address

Atoti Ulo Guba
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት:

Shortcuts

Share