Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ

Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ This is the official Halaba Zone Peace And Security Department page.

Detail contact information to follow us:
https://halaba.gov.et
ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የተቋቋመዉ ግጭትን በመከላከልና በመፍታት፤ በሀይማኖትና እምነቶች መካከል ዘላቂ መቻቻልና የመከባበር እሴት በማጎልበት እና ጠንካራ የፀጥታ መረጃ ስርዓት በመፍጠር የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ህገ-መንግስቱን በማስከበር የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ነዉ።

የክልሉ ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ቤቶች ለባለቤቶቹ አስረከቡ ******ነሃሴ 30/2018)፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ሴክ...
05/09/2026

የክልሉ ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ቤቶች ለባለቤቶቹ አስረከቡ
******
ነሃሴ 30/2018)፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ሴክተር ተቋማት በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ያስገነቧቸውን ሁለት የመኖሪያ ቤቶች ለባለቤቶች አስተላልፈዋል።

ተቋሟቱ የአቅመ ደካሞቹን የቤት ግንባታ ሀምሌ 14/2018 ማስጀመራቸው ይታወቃል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ኤርስኖ አቡሬ ተቋሙ የማህበራዊ ሀላፊነት ለመወጣት በርካታ ስራዎችን እየፈፀመ መሆኑን ተናግረዋል።

ደካሞችን ለመደገፍ የተጀመረውን ስራ በማጠናከር የበጎ ፈቃድ ስራዎችን ባህል ማድረግ ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ በዛሬው ዕለትም የፍትህ አካላትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት በ1.2 ሚሊዮን ብር በጋራ የተገነባ የመኖሪያ ቤት አስረክቧል

የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ንጉሴ አስረስ ዶ/ር በክልሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በልዩ ትኩረት እየተመራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

በክልሉ በሁሉም ዘርፍ በተሰራው ስራ እምርታ መጥቷል ያሉት ዋና አማካሪው የበጎ ተግባሩ ለዜጎች እፎይታን የሠጠና የመንግስትና የማህበረሰቡን ትስስርን እያጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል።

ህብረተሰቡ በጉልበቱ ፣በእውቀቱና በገንዘቡ ጠንካራ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረው እስካሁንም በክልሉ ከ13 ቢሊዮን በላይ ብር ተሳትፎ ማድረጉን ተናግረዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ አክመል አህመድን በበኩላቸው የመረዳዳትና የመተጋገዝ አካል አንዱ የሆነውን ለአቅመ ደካማ ዜጎች የመኖሪያ ቤት ገንብቶ አስረክቧል ብለዋል።

ግንባታውን የፍትህ ቢሮ እና የማረሚያ ተቋማት በጋራ ያስገነቡት መሆኑን ገልፀው ለቤቱ የሚያስፈልጉ ሙሉ የቤት እቃዎች የተሟላለትና ለእናታችን ለስራ ማስጀመሪያ የሚሆን የ50 ሺ ብር ተጨማሪ ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

‎ተግባሩ ዜጎች የተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖራቸው ያደርጋል ያሉት አቶ አክመል በአጠቃላይ ለቤቱ ግንባታና የቤት ቁሳቁስ 1 ሚሊዮን 200ሺ ብር ወጪ መደረጉን ተናግረዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ገመዳ መሀመድ በበኩላቸው መንግስት በዜጋ ተኮር ስራዎች የተለያዩ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የሆኑ አረጋዊያንና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ ተጠቃሚ ማድረጉንና ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።

አባታቸውን በሞት ያጡ 4 ልጆችና 2 ወላጅ አልባ በድምሩ የ6 ልጆች አሳዳጊ የሆኑት ወ/ሮ መድሀኒት ሀይሉ መንግስት ያደረገላቸው የተሟላ ድጋፉ ለልጆቻቸውና ለራሳቸው ተስፋን እንደጨመረላቸው ተናግረዋል።

ሁለተኛው የቤት ድጋፍ የተደረገላቸው እናት ልጃቸው የሀገር መከላከያን እያገለገለ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ አይነቴ ቦጪሶ ደግሞ ድጋፉ ከሰው ጋር እኩል መኖር እንዲችሉ ያስቻላቸው መሆኑን ገልፀዋል።
በቁልፍ ርክክቡ ወቅት የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን ለቤቶቹ ግንባታ ስኬት ድጋፍ ያደረጉ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል።

 !!የቅጥር ማስታወቂያየኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾ...
04/09/2026

!!

የቅጥር ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2019 በጀት ዓመት የተቋሙን የሰው ኃይል ለማጠናከር በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰብና ሕዝቦች፣ የጾታ ተዋፅዖን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ተመልምለው በተቋሙ ባሉት ልዩ ልዩ የሥራ ዘርፎች ተመድበው ማገልገል የሚፈልጉ ዕጩ ፖሊሶችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።

ዕጩ ተመልማዮቹ ምልመላው ተጠናቆ ወደ ኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሥልጠና ማዕከል ገብተው ሥልጠና ከመጀመራቸው በፊት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በሚያዘው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት በማሰልጠኛ ትምህርት ቤቱ አማካይነት የሚሰጣቸውን ሥልጠና በሚገባ በመከታተል ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በሥልጠና ቆይታ ጊዜያቶችም በማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ በኩል የምግብ፣ የመኝታ፣ የሕክምና እና ለሥልጠናው የሚያስፈልጉ የአልባሳት፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የኪስ ገንዘብ ይሰጣል።

ሥልጠናው ሲጠናቀቅም እያንዳንዱ ተመራቂ በተቋሙ የደመወዝ ስኬል መሰረት ወርሃዊ ደመወዝና የቀለብ ሂሳብ የሚከፈለው ሆኖ በተቋሙ ልዩ ልዩ የስራ አልባሳት፣ ነፃ የሕክምና አገልግሎት፣ በካምፕ የጋራ መኖሪያ ቤት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት ያገኛሉ።

ተመርቀው ፖሊሳዊ የሙያ አገልግሎት በሚያበረክቱባቸው ጊዜያትም በተቋሙ ውስጥ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ማቋቋሚያ አዋጅ፣ ደንብ እና የስልጠና መመሪያዎች መሠረት በሚወጡ መመዘኛዎች አማካኝነት በልዩ ልዩ የትምህርትና ሥልጠና ፕሮግራሞች በመወዳደር ተጠቃሚ የመሆን ሠፊ ዕድል የሚጠብቃቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በደስታ ይገለፃል።
የምልመላ መስፈርት (መመዘኛ)

1. ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች፣

2. ለሕገ-መንግስንቱና ለሀገሪቱ ሕጎች ተገዥና ታማኝ የሆነ/የሆነች፣

3. ከማናቸውም ደባል ሱሶች የፀዳ/የፀዳች እና መልካም ስነ-ምግባር ያለው/ያላት፣

4. በሚመለመልበት አካባቢ ነዋሪ ስለመሆኑ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

5. ከሚኖርበት ቀበሌ አስተዳደር፣ ከአካባቢው ፖሊስ እና ከተማረበት ትምህርት ቤት የተዘጋጁ ቅፆችን በማስሞላት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤

6. በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በሃይማኖት እኩልነት የሚያምን/የምታምን፣

7. ለፖሊስነት የሚያበቃ ሙሉ ጤናማ መሆኑን/መሆኗን በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

8. ዕድሜው/ዋ ከ18 እስከ 25 ዓመት ያላነሰና ያልበለጠ/ያልበለጠች፣

9. የማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች፣

10. የትምህርት ደረጃ 10ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች እንዲሁም ትምህርት ያጠናቀቀበት ካርድ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣

11. ብዝሃነትንና አካታችነትን ለማረጋገጥ ሲባል ያልተካተቱና አነስተኛ ቁጥር ባለባቸው ብሔሮች አካባቢ ለሚመለመሉ ወጣቶች ቢያንስ 6ኛ ክፍል እና በላይ የሆነ/የሆነች፣

12. ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር በላይ የሆነ፣ ለሴት 1.60 ሜትር በላይ የሆነች፣

13. የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 720/2004 እና ደንብ ቁጥር 268/2005 በተደነገገው መሠረት የ7 ዓመት የሥራ ውል ግዴታ በመግባት ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በየትኛውም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ተቋም የሥራ አከባቢ ተመድቦ/ተመድባ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፣
14. ከአሁን በፊት በወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ/ያልተቀጣች ወይም የወንጀል ሪከርድ የሌለበት/የሌለባት የአሻራ

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አደረገ የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም...
04/09/2026

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አደረገ

የዌራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የ2018 አጠቃላይ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል ።

መድረኩን የዌራ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ናስር አወል እና የዌራ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በረዲን ኬዳ በጋራ መርተዋል ።

የፖሊስ አባላትን የማስፈጸም አቅም በመገንባትና ከሌሎች የፍትህና የፀጥታ ሀይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር የህብረተሰቡን ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ እንደሚገባ አቶ በረዲን አሳስበዋል።

በጀት ዓመቱ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጎልበትና የተለዩ ውስንነቶችን በመቅረፍ በቀጣይ በ2019 በጀት አመት ይበልጥ አጠናክሮ በማስቀጠል ፖሊስ የተጣለብ አደራ በብቃት መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል።

ምክትል ኢንስፔክተር ናስር አወል በበኩላቸው የፖሊስ ተቋም የማህበረሰቡ ተግባሩን በሰላም እንዲከውን ማስቻል እና ወንጀልን መከላከል ነው ብለዋል።

ይህን ተቋም የሚመጥን ተግባር በመፈጸም የተጣለብንን ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ በአጽኖት ገልጸዋል።

በተለይም የፖሊስ አባላት የተሰጣቸውን የህዝብ ኃላፊነትን በአቅም መወጣት እንደሚያስፈልግ ምክትል ኢንስፔክተር አያይዘው አሳስበዋል።

የፖሊስ አባላት ተግባራትን በጥበብ በመምራት የወንጀል ድርጊቶችን ቀድመው በመከላከል የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ ስራን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በውይይቱ ማጡቃለያ የ2019 መሪ ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አድርገው በበጀት ዓመቱ ያለቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የፖሊስ አባላት ዕውቅና በመስጠት መድረከ ተጠናቋል ።

📢 ማስታወቂያ🇪🇹 16ኛ ዙር ብሔራዊ በጎ ፈቃደኞች ምዝገባ📅 ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም🇪🇹 ለሀላባ ዞን ለሁሉም ወጣት በጎ ፈቃደኞች!የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሰላም ሚኒስቴር በ2019 በጀት ዓመት 16ኛ...
04/09/2026

📢 ማስታወቂያ
🇪🇹 16ኛ ዙር ብሔራዊ በጎ ፈቃደኞች ምዝገባ
📅 ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም
🇪🇹 ለሀላባ ዞን ለሁሉም ወጣት በጎ ፈቃደኞች!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሰላም ሚኒስቴር በ2019 በጀት ዓመት 16ኛ ዙር ብሔራዊ በጎ ፈቃደኞችን በማሰልጠን ወደ ሥራ ለማሰማራት ይፈልጋል።
በመሆኑም፣ በብሔራዊ በጎ ፈቃድ ተግባር ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁና የሚከተሉትን የምዝገባና የምልመላ መስፈርቶች የምታሟሉ ወጣቶች በኦንላይን እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
✅ የመመዝገቢያ መስፈርቶች
1️⃣ እድሜው ከ18 እስከ 35 ዓመት የሆነ/ች፤
2️⃣ የኢትዮጵያ ዜግነት ያለው/ላት፤
3️⃣ ብሔራዊ መታወቂያ ያለው/ላት፤
4️⃣ ከሀገር አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት የመጀመሪያ ድግር ወይም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ዲፕሎማ ወይም 10+3 ያለው/ላት፤
5️⃣ ስልጠናውን ካጠናቀቀ/ች በኋላ በሀገሪቱ በማንኛውም አካባቢ ተመድቦ/ባ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
6️⃣ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስፈልገው ስፍራ ሙሉ በሙሉ ለመንቀሳቀስ የሚከለክል የጤናና የአካል ብቃት ችግር የሌለበት/ባት፤
7️⃣ መልካም ሥነ-ምግባር ያለው/ላትና ከማንኛውም ዓይነት ሱስ ነፃ የሆነ/ች፤
8️⃣ በስልጠናና በስምሪት ወቅት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ደንብና መመሪያን ለመተግበር ሙሉ ፈቃደኛ የሆነ/ች፤
9️⃣ በወንጀል ድርጊት ተሳታፊ በመሆን በፍርድ ጥፋተኛ ያልተባለ/ች፤
🔟 ከዚህ በፊት በብሔራዊ በጎ ፈቃድ ስልጠናና ስምሪት ላይ ያልተሳተፈ/ች፤
1️⃣1️⃣ ሥራ አጥ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ከመኖሪያ አካባቢው ማቅረብ የሚችል/ች።
🗓️ የምዝገባ ጊዜ፦
ከነሐሴ 28/2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 22/2019 ዓ.ም ድረስ።
🌐 የመመዝገቢያ አድራሻ፦
👉 http://yvms.mop.gov.et⁠�
📌 መስፈርቶቹን የምታሟሉና ሀገራችሁን በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል ፍላጎት ያላችሁ ወጣቶች በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እንድትመዘገቡ ጥሪ እናቀርባለን።
🤝 በጎ ፈቃደኝነት ለሀገር፣ ለህዝብና ለዘላቂ ሰላም!
#የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ!!

በሀላባ ዞን የግል የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ማሰልጠኛ ተቋማት ባለቤቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ =====ነሀሴ 28/2018 በሀላባ ዞን የግል የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ማሰልጠኛ ተቋማት ...
03/09/2026

በሀላባ ዞን የግል የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ማሰልጠኛ ተቋማት ባለቤቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ
=====

ነሀሴ 28/2018 በሀላባ ዞን የግል የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ማሰልጠኛ ተቋማት ባለቤቶች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

በዚህ ወቅት የሀላባ ዞን ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ሀ/ኑሪዬ እንደገለጹት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ በተደረጉ ማሻሻያዎች ፍላጎት መሰረት ያደረገ የሰው ሃይል የማፍራት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ጠቁመዋል።

የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዋና አላማ ዜጎች በህጋዊ መንገድ ደህንነታቸው ተጠብቆና አስፈላጊውን ስልጠና አግኝተው እንዲሰማሩ በማድረግ የራሳቸውንና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲያሳድጉ ማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።

ለዚህም ደግሞ ከመንግስት ማሰልጠኛ ተቋማት ጎንለጎን የመንግስትን አሰራር ተከትለው የግል ተቋማት በዘርፉ ላይ ተሰማርተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በወጣቶችና በዜጎች ዘንድ በሙያ ስልጠና ላይ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ለመቀየር በልዩ ትኩረት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

‎ከቅንጅት ስራዎች አኳያ በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ከተሰማሩ ኤጀንሲዎች አኳያ የሚስተዋለውን ክፍተት መቅረፍ እንደሚገባውም አመላክተዋል፡፡

ዜጎች በቂ ሙያ፣ የቋንቋና የባህል ስልጠና ወስደው ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተለይም ደላላና ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በህግ የመጠየቅና የመታገል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።

የሀላባ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ አቶ ሙበሽሪ ሁሴን እንደገለጹት የውጭ ሀገር ስራና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ለሥራው የማይተካ ሚና ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ዜጎች ክብራቸውና ጥቅማቸው ተጠብቆ በህጋዊ መንገድ እንዲሰማሩ ማድረግ እንደሚገባ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

ይህ የወጣቶች የስራ ስምሪት ተግባር ይበልጥ ይጠናከር ዘንድ ተቋማዊ በሆነ መልኩ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዞኑ የሚገኙ ‎ኤጀንሲዎች ከባለድርሻ በመሆናቸው በቀጣይም ተቀራርቦ ለመስራት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ህገወጥነቱን ገታ አድርገን ህጋዊነትንና ብቃትን በማስቀደም ለዞናችንና ለሀገራችን የተሻለ ነገር መስራት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
በመድረክ ላይም የግል የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት ማሰልጠኛ ተቋማት ባለቤቶች ጋር በሰፊው ውይይት ተደርጎበት ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ተቀምጧል።

ሀገራዊ ተልዕኮን በሚገባ የሚወጣ የፖሊስ የሰራዊቱን ብቃት ይበልጥ የሚያሳድግ የሰው ሀይል መመልመል ይገባል - አቶ ሙደስሪ ጉታጎ=====ነሀሴ 28/2018 የ27ኛ ዙር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊ...
03/09/2026

ሀገራዊ ተልዕኮን በሚገባ የሚወጣ የፖሊስ የሰራዊቱን ብቃት ይበልጥ የሚያሳድግ የሰው ሀይል መመልመል ይገባል - አቶ ሙደስሪ ጉታጎ
=====

ነሀሴ 28/2018 የ27ኛ ዙር የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ምልመላ በተመለከተ የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኦራቴሽን መድረክ አካሄደዋል።

በመድረኩ ላይ የኦራቴሽን የሰጡት የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ እንደገለጹት ሀገራዊ ተልዕኮን በሚገባ የሚወጣ የፖሊስ የሰራዊቱን ብቃት ይበልጥ የሚያሳድግ የሰው ሀይል መመልመል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

የፖሊስነት ሙያ ከፍተኛ መስዋዕትነት የሚያስከፍል፣ ቁርጠኝነትና ጽናትን የሚጠይቅ መሆኑን ሀላፊው አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በማቋቋሚያ አዋጁ ከተሰጠው ተቋማዊ ተልዕኮ አንጻር ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ደረጃውን የጠበቀ፣ በብቃትና ጥራት ላይ የተመሰረተ፣ ተደራሽነት ያለው ፈጣን ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት መሆኑን ገልጸዋል።

ዋና አላማው የፌዴራል ፖሊስ ተቋም ከሰው ሀይል ልማት አንፃር የሚታየውን ክፍተት ለመሙላታ እንዲያስችል ታስቦ ነው ብለዋል።

በዘንድሮው አመት የሚካሄደውን የ27ኛ ዙር የምልምል ሰልጣኞች ምልመላ፤ ቅበላና ስልጠና ፕሮግራምን ውጤታማነት በሚያረጋግጥ መልኩ ለመፈፀም ታስቦ የተዘጋጀ የምልመላ ስልጠና እቅድ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ተቋሙን የሚመጥን የሰው ሀይሉን በከፍተኛ ደረጃ ለማጠናከር 27ኛ ዙር መደበኛ የፖሊስ ኃይል ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሰው ሀይል መጠናከሩ ጠቀሜታው ለዞን፣ ክልል ጭምር እንደመሆኑ መጠን የሚመለከታቸው አካላት ምልመላውን ሀላፊነት በተሞላበት መልኩ እንዲፈጽሙ ጥሪ አሳስበዋል።

ምልመላው በተቀመጠው መስፈርትና የመመልመያ የጊዜ ሰሌዳ ለዞኑ በተሰጠው ኮታ መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ፈቃደኛ የሆኑ ወጣቶችን እንዲያዘጋጁ አስገንዝበዋል።

ስምመላመል ከየትኛውም የፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ መሆኑን በማረጋገጥ እንደሚገባና ተግባሩ በየግዜው እየተገመገመ እንደሚሄድ አሳስበዋል።

ተመልማዩ ወጣት ለሀገርና ለህዝብ የቆመ ከተለያዩ ወንጀሎች የፀዳ መሆኑን ማስረጃዎችን አረጋግጦ መመዝገብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለዚህም ለማህበረሰቡ ስለ ምልመላው በቂ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግም የመምሪያው ሀላፊ አቶ ሙደስሪ ጉታጎ ቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።

በኦራንቴሽኑ ላይ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኑሪዬ፣ የሀላባ ዞን ሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመቹ ወርቅቾ፣ የአራቱም መዋቅር ሰላምና ፀጥታ እና የሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ የፖሊስ ጽ/ቤት አዛዦች፣ የዞንና የወረዳ፣ ከተማ ፖሊስ አባላት ተገኝተዋል።
#በሹኩር ሀ/ሀሰን

🤝 መደጋገፍ🤝 ባህልን እና ልዩነትን ማክበር🤝 ሰብዓዊ መብቶችን እውቅና መስጠት🤝 ማኅበራዊ ሀብቶችን መጠበቅ እና መንከባከብ የአብሮነት መሠረቶች ናቸው። አብሮነት ከሌለ የሚሳካ የጋራ ርዕይ እ...
03/09/2026

🤝 መደጋገፍ
🤝 ባህልን እና ልዩነትን ማክበር
🤝 ሰብዓዊ መብቶችን እውቅና መስጠት
🤝 ማኅበራዊ ሀብቶችን መጠበቅ እና መንከባከብ የአብሮነት መሠረቶች ናቸው።
አብሮነት ከሌለ የሚሳካ የጋራ ርዕይ እና ግብ አይኖርም፤ ሰላሟ የተጠበቀ እና ጠንካራ ሀገር ለመገንባት አብሮነት ወሳኝ ነው።
🔑 ለልማት
🔑 ለሀገር ሰላም
🔑 ለማኅበራዊ ትስስር
🔑 ችግሮችን በጋራ ለመወጣት እና የጋራ ደህንነትን ለማረጋገጥ አብሮነት እጅግ አስፈላጊ ነው።
ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊
መረጃው የሰላም ሚኒስቴር ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ ነው

የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ቤተሰብ ወርሃዊ የቤተሰብ ውይይት አካሄደነሐሴ 28/2018 ዓ.ም — ሀላባ ቁሊቶየሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የብልጽግና ቤተሰብ አባላት- የነሐሴ ወር-...
03/09/2026

የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ቤተሰብ ወርሃዊ የቤተሰብ ውይይት አካሄደ

ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም — ሀላባ ቁሊቶ

የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የብልጽግና ቤተሰብ አባላት- የነሐሴ ወር-ልሳነ-ማዕከላዊ 1ኛ ዓመት ቁጥር 5 ጋዜጣ ላይ በቀረበው «ለጠንካራና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ አገረ-መንግሥት ግንባታ የአባላት ሚና» በሚል አጀንዳ ላይ በዛሬው ዕለት ወርሃዊ የቤተሰብ ውይይት አካሂደዋል።

የውይይቱን መድረክ የመሩት የመምሪያው የቤተሰቧ የፖሎቲካ ዘርፍ የሆኑት አቶ ረቢዩ በፋታ ሲሆኑ፣ በወቅቱ የጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ-መንግሥት ግንባታ ሂደት ሕብረ-ሀገራዊ ማንነትን የተላበሰ፣ ብዝኃነትን የሚያከብርና የሚያንፀባርቅ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው አገረ-መንግሥት ለመገንባት በተለያዩ መስኮች የለውጥ ሥራዎችንና ቅድመ ዝግጅቶችን እያከናወነች መሆኑ ተገልጿል። በተለይም በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ተጨባጭ ለውጥ በማምጣት ሀገራችንን የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውም ተነስቷል።

በውይይቱም የሀገራችን ዜጎች በአካታችና አቃፊ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ በመሳተፍ፣ በሁሉም የልማትና የዕድገት አጀንዳዎች ላይ የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍና የማይተካ ሚናቸውን በተገቢው መልኩ መወጣት እንደሚገባቸው ተጠቅሷል።

በተለይም የሰላምና ፀጥታ ተቋማትና ባለሙያዎች ጠንካራ አገረ-መንግሥት ለመገንባት ሰላምን በማስፈን፣ የሕዝቦችን አንድነትና መቻቻል በማጠናከር፣ የግጭት ምክንያቶችን በመከላከልና በመፍታት እንዲሁም የሰላም እሴቶችን በማስፋፋት የጎላ ኃላፊነት እንዳለባቸው በመድረኩ ተነስቷል።

በአጠቃላይ ለአንድ ሀገር ጠንካራ፣ ቅቡልነት ያለውና በሁሉም የልማትና የዕድገት መንገዶች ፊት የወጣ አገረ-መንግሥት መገንባት ለዜጎች ሰላም፣ ደኅንነትና ዘላቂ ብልፅግና ዋስትና መሆኑ ተገልጿል። በመሆኑም ሁሉም የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ቤተሰብ አባላት ለሁሉአቀፍና አካታች የፖለቲካ ሥርዓት ግንባታ፣ ለሰላም መጠናከርና ለሀገራዊ አንድነት የድርሻቸውን ኃላፊነት በትጋት መወጣት እንደሚገባቸው በውይይቱ ተስማምተዋል።
በመጨረሻም በአጀንዳው ላይ አባላት የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፣ በቀረቡ ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንዛቤና መግባባት በመፍጠር የወርሃዊ የቤተሰብ ውይይቱ ተጠናቋል።
#የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሚዲያ ዘርፍ

🚨 ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት!የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ «ሁሉ የሚታወቅባት ኢትዮጵያን» እውን ለማድረ...
03/09/2026

🚨 ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ የተላለፈ የጥንቃቄ መልዕክት!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ «ሁሉ የሚታወቅባት ኢትዮጵያን» እውን ለማድረግ ዘርፈ-ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ኤጀንሲያችን የልደት፣ የሞት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የጉድፈቻ የምስክር ወረቀቶችን ከመስጠት ባለፈ፣ ወደ ውጭ አገር ለሚሄዱ ዜጎች በልደት የምስክር ወረቀታቸው ላይ የማረጋገጥ (የመመስከር) አገልግሎት ከሐምሌ 20 ቀን ጀምሮ በክልል ደረጃ እየሰጠ ይገኛል።

ሆኖም በሚከተሉት ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን፡

* ከመንግሥት የክፍያ ደንብ ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ማስከፈል እና ሕጋዊ ደረሰኝ አለመስጠት፤
* "የምስክር ወረቀት አልቋል" በማለት ተገልጋዮችን ወደ ሕገ-ወጥ መንገድ መምራት፤
* ሀሰተኛ ማኅተምና የባለሙያዎች ስም ያለበት ቲተር በማስቀረጽ ሕገ-ወጥ የማረጋገጥ ሥራ መሥራት፤
* "የዲጂታል መታወቂያ እንሰጣለን / እንለውጣለን" በማለት ሀሰተኛ ወይም የሌላ አሻራ ያለበትን ለውጦ ማዘጋጀት።

እነዚህን ሕገ-ወጥ ድርጊቶች ሲፈጽሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በኅብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር እየዋሉ ይገኛሉ።

📌 መልዕክታችን፡
ኅብረተሰቡ ከነዚህ አጭበርባሪዎች እራሱን እንዲጠብቅና የሚፈልገውን አገልግሎት ከሕጋዊ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ብቻ እንዲያገኝ እያሳሰብን፤ አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ለሕግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንድትሰጡ እንጠይቃለን።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ

የ2018  #የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች!!  ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”ጳጉሜን 5 – ...
02/09/2026

የ2018 #የጳጉሜን ወር አምስቱ ቀናት ስያሜዎች!!
ጳጉሜን 1 – “የእመርታ ቀን”
ጳጉሜን 2 – “የማንሰራራት ቀን”
ጳጉሜን 3 – “የጽናት ቀን”
ጳጉሜን 4 – “የኅብር ቀን”
ጳጉሜን 5 – “የነገ ቀን”

Address

Halaba
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba Zone Peace And Security Department - የሀላባ ዞን ሰላምና ፀጥታ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share