11/08/2026
እ.ኤ.አ ከኦገስት 11 እስከ 20/2026 (ነሐሴ 5 እስከ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
/////////
በሚቀጥሉት አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሃገራችን ተፋሰሶች ላይ ከመካከለኛ እስከ እጅግ በጣም ከፍተኛ መጠን የሚደረስ የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት ይኖራቸዋል። በመሆኑም የሚመለከታቸው የዘርፉ አካላት የሚኖሩ መልካም ዕድሎች በአግባቡ ለመጠቀምና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ማለትም የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የመሬት መንሸራተት እንዲሁም የደራሽ ወንዝ ሙላትና ሌሎች ተያያዥ የተፈጥሮ አደጋዎች ለመቀነስ የሚከተሉትን ተፋሰስ ተኮር የውሃ ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል