የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሺንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሺንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት

የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሺንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት ይህ በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሺንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት የፌስቡክ ገጽ ነው ።

ኮሚሽኑ በየደረጃው ጠንካራ የፓርቲ ተቋም እንዲፈጠርና የአባላት መብትና ግዴታ እንዲከበር ጠንካራ ስራዎች እየሰራ ነው፦አቶ ጀማል መሀመድ‎‎የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግ...
13/08/2026

ኮሚሽኑ በየደረጃው ጠንካራ የፓርቲ ተቋም እንዲፈጠርና የአባላት መብትና ግዴታ እንዲከበር ጠንካራ ስራዎች እየሰራ ነው፦አቶ ጀማል መሀመድ

‎የዌራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን
" ሁሉአቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ" በምል መሪህ በተካሃደው ወረዳዊ ኮንፍረንስ መድረክ ላይ የ2018 በጀት ዓመት የኮሚሽን አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ኦሬንቴሽን የቀረባ ስሆን ፤፦
መድረኩ ብልጽግና ፓርቲ የሚመራበትን የመደመር እሳቤ፣እሴቶችና መርሆዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፕሮግራሞች ለአባላትና ለአመራሩ ግልጸኝነት የመፍጠር ጠንካራ ስራ መስራቱን አመለከተ።

‎ኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ በሁሉም አደረጃጀት ተቋሙን የመገንባት፣ የአባላትንና የአመራሩን መብትና ጥቅሞች እንዲሁም የፓርቲውን ሀብትና ንብረት የማስጠበቅ ስራዎች መስራቱንም ገልጿል።

‎የኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ጀማል መሀመድ በወረዳ ደረጃ በተካሄደ የወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ አፈጻጸም መጠቃለያና ፈጻሚ ዝግጅት መድረክ ላይ የጽህፈት ቤታቸውን አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

‎ጽህፈት ቤቱ ጠንካራ ፓርቲ በየደረጃው እንዲገነባ ጠንካራ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች መስራቱን የገለጹት አቶ ጀማል መሀመድ የተሻለ ተቋማዊ አቅም ለመገንባት ብርቱ ርብርብ መደረጉንም አመላክተዋል።

‎ኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ በየደረጃው የተቀናጀና ውጤታማ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ማድረጉንም ገልጸው፣በእነዚህ ጥረቶችም የፓርቲውን ህዝባዊ አላማዎች ማስረጽና ማስገንዘብ ስለመቻሉም አብራርተዋል።

[ ] ‎ሆኖም የፓርቲ መተዳደሪያ ደንቦችና መመሪያዎችን ለአባላት ለማስገንዘብ በበቂ ደረጃና ጥራት ከመስራት አኳያ፣ ደንቦችና መመሪያዎች በአንዳንድ መዋቅሮች ስራ ላይ መዋላቸውን ያለማረጋገጥ ችግር፣የሚቀርቡ ቅሬታዎችን አጣርቶ ቶሎ ምላሽ የተሰጠበት ፈይለ አደራጅቶ ከማስቀመጥ አኳያ ውስንነቶች እንዳሉም አቶ ጀማል መሀመድገልጸዋል።

‎በአዲሱ በጀት ዓመት በየደረጃው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የበለጸገ ወረዳ ዞንና ሀገር ለመገንባት ተቀናጅቶና ተናቦ ለመስራት ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንም አቶ ጀማል መሀመድ አረጋግጠዋል።

!!

10/08/2026
08/08/2026
የፓርቲውን ጥንካሬና ጤናማነት የሚጠበቀው የኢንስፔክሽን ስራ በውጤታማነትና በትኩረት ልሰራ እንደሚገባ ተገለጸ። ነሀሴ 2/2018ዐ/ም የሀላባ ዞን ብልጽግና  የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽ...
08/08/2026

የፓርቲውን ጥንካሬና ጤናማነት የሚጠበቀው የኢንስፔክሽን ስራ በውጤታማነትና በትኩረት ልሰራ እንደሚገባ ተገለጸ።

ነሀሴ 2/2018ዐ/ም የሀላባ ዞን ብልጽግና የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት የ2019 በጀት አመት የሀምሌ ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በበይነ መረብ ገምግመዋል።
በአፈጻጸም ግምገማ ላይ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ት ቤት ሀላፊ ኢ/ር መዲና ዓለሙ እንደገለጹት የብልጽግና ፓርቲ ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የኢንስፔክሽን ስራ የላቀ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
የፓርቲው ጥንካሬና ቀጣይነት የሚወሰነው በኢንስፔክሽን ስራው ጥራት መሆኑንም ሃላፊዋ ገልጸዋል።
የአመራሩና የአባላቱ ስነ-ምግባር፣ የፓርቲው ሀብትና ንብረት በአግባቡ መጠበቁንና የአባላት መብቶች መከበረቸዉንና መመሪያዎችና ደምቦች አለመጣሳቸዉን ማረጋገጥ የኮሚሽኑ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንና ይህንኑ በያዝነዉ በጀት አመት አጠናክረን መቀጠል እንዳለብን ጠቁመዋል።
በተለይ በ2018 ዓ/ም አፈጻጸም የታዩ ጉድለቶች ለቀጣይ እርምት ተውስዶበት ጠንካራ ጎን እንድቀጥል ኮሚሽን ኮሚቴው አባላት ታችኛውን መዋቅር በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በ2019 በጀት ዓ/ም በየጊዜው የሚያከናውናቸውን ጠንካራ የኢንስፔክሽን ስራዎች ግኝት ለፓርቲ ቅ/ጽ/አቤት ከነመፍትሄ ሀሳብ በማቅረብ ተፈፃሚነታቸውን በመከታተል ለላቀ ድል አስተዋፅኦ ማድረግ ይገባል ብለዋል።ከሁሉም ወረዳዎች የሀምሌ ወር ሪፖርት ቀርቦ
በተለይም ቀጣይም ኮምሽኑ ጠንክሮ መሰራት እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።
የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መዲና አለሙ አክለዉም በየግዜው የሚንሰራቸው ስራዎች በጊዜዉ ሰሌዳ መሠረት የአፈጻጸም ግምገማ በማድረግ የፓርቲውን ውስጣዊ አሰራርና አንድነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል።
‎አክለውም መድረኩ ለበጀት አመቱ የመጀመሪያ በመሆኑ ከእቅድና ሪፖርት አቀራረብ አንጻር እስከታች የጋራ ማድረግና ግዜዉን የጠበቀና ሙሉዕ በማድረግ ጠንካራ ጎኖችን የምናጠናክርበትና ያሉብንን ደካማ ጎኖች በመለየት በቀጣይ ለምናከናውነው ተግባር መሠረት የምንጥልበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ሌላው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በስነ-ምግባርና በቅሬታ አፈታት ዙሪያ በትኩረት መስራት እንደሚገባና መሰሎች በተገቢዉ መደራጀት እንዳለባቸዉም ገልጸዋል።
የሶስቱም ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደር ኮሚሽን ስራ አመራሮች በሀምሌ ወር በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎች ቀርበው በሰፊው ዉይይት በማድረግና ቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ የእለቱ ዉይይት ተጠናቅቋል።

ኮሚሽኑ በየደረጃው ጠንካራ የፓርቲ ተቋም እንዲፈጠርና የአባላት መብትና ግዴታ እንዲከበር ጠንካራ ስራዎች እየሰራ ነው፦ኢ/ር መደዲና ዓለሙ‎‎ቁሊቶ አቦክቾ፦ሀምሌ 30/2018‎‎የሀላባ ዞን ብል...
07/08/2026

ኮሚሽኑ በየደረጃው ጠንካራ የፓርቲ ተቋም እንዲፈጠርና የአባላት መብትና ግዴታ እንዲከበር ጠንካራ ስራዎች እየሰራ ነው፦ኢ/ር መደዲና ዓለሙ

‎ቁሊቶ አቦክቾ፦ሀምሌ 30/2018

‎የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብልጽግና ፓርቲ የሚመራበትን የመደመር እሳቤ፣እሴቶችና መርሆዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፕሮግራሞች ለአባላትና ለአመራሩ ግልጸኝነት የመፍጠር ጠንካራ ስራ መስራቱን አመለከተ።

‎ኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ በሁሉም የዞን መዋቅሮች ተቋሙን የመገንባት፣የአባላትንና የአመራሩን መብትና ጥቅሞች እንዲሁም የፓርቲውን ሀብትና ንብረት የማስጠበቅ ስራዎች መስራቱንም ገልጿል።

‎የኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ኢ/ር መዲና ዓለሙ በአቦክቾ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ አፈጻጸም መጠቃለያና ፈጻሚ ዝግጅት መድረክ ላይ የጽህፈት ቤታቸውን አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

‎ጽህፈት ቤቱ ጠንካራ ፓርቲ በየደረጃው እንዲገነባ ጠንካራ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች መስራቱን የገለጹት ኢ/ር መዲና ዓለሙ፣የተሻለ ተቋማዊ አቅም ለመገንባት ብርቱ ርብርብ መደረጉንም አመላክተዋል።

‎በየደረጃው በፓርቲ ጽህፈት ቤቶች የሚሰበሰቡ ገቢዎች በህጋዊ ደረሰኝ እየተሰበሰቡ መምጣታቸውን፣ በፓርቲው የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቁመዋል።

‎የኦዲት ስራዎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውን፣የአባላት መብትና ግዴታ እየተከበረ እንደመጣና ውስጠ ዴሞክራሲ እየተጠናከረ እንዲመጣ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ እንዳለም ኢ/ር መዲና ዓለሙ ገልጸዋል።


‎ኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ በየደረጃው የተቀናጀና ውጤታማ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ማድረጉንም ገልጸው፣በእነዚህ ጥረቶችም የፓርቲውን ህዝባዊ አላማዎች ማስረጽና ማስገንዘብ ስለመቻሉም አብራርተዋል።

[ ] ‎ሆኖም የፓርቲ መተዳደሪያ ደንቦችና መመሪያዎችን ለአባላት ለማስገንዘብ በበቂ ደረጃና ጥራት ከመስራት አኳያ፣ደንቦችና መመሪያዎች በአንዳንድ መዋቅሮች ስራ ላይ መዋላቸውን ያለማረጋገጥ ችግር፣የሚቀርቡ ቅሬታዎችን አጣርቶ ቶሎ ምላሽ የተሰጠበት ፈይለ አደራጅቶ ከማስቀመጥ አኳያ ውስንነቶች እንዳሉም ኢ/ር መዲና አለሙ ገልጸዋል።

‎በአንዳንድ መዋቅሮች የአደረጃጀቶች የውይይት ጊዜ መቆራረጥ፣ምልአተ ጉባኤ ሳያሟሉ ኮንፍረንሶችን ማካሄድ፣የኮሚሽኑን ተልዕኮ በአግባቡ ያለመረዳት፣የበጀትና የግብአት ውስንነት፣የመሳሰሉ ጉድለቶች መታየታቸውንም አንስተዋል።

‎በአዲሱ በጀት ዓመት በየደረጃው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የበለጸገ ዞን ክልልና ሀገር ለመገንባት ተቀናጅቶና ተናቦ ለመስራት ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንም ኢ/ር መዲና ዓለሙ አረጋግጠዋል።

07/08/2026
የአንድነት፣የትብብርና የቅንጅት ሥራ በማጠናከር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ማሟላት የሁላችንም የጋራ ትግልና ኃላፊነት መሆን ይገባዋል፦አቶ መሐመድከማል ኑርዬ፣ «በ2019...
07/08/2026

የአንድነት፣የትብብርና የቅንጅት ሥራ በማጠናከር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ማሟላት የሁላችንም የጋራ ትግልና ኃላፊነት መሆን ይገባዋል፦አቶ መሐመድከማል ኑርዬ፣

«በ2019 ዓ.ም ሁሉአቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ!» በሚል መሪ ቃል በዞኑ በዌራ ወረዳ በአቦክቾ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የሀላባ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ማጠቃለያና የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክም ተጠናቋል።

በዚህ ወቅት የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መሐመድከማል ኑርዬ በሰጡት የቀጣይ አቅጣጫዎች​ «በ2019 ዓ.ም ሁሉአቀፍ እምርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ!»በሚል መሪ ቃል የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በማጠናከር፣የዞናችንን የብልጽግና ተምሳሌት፣የላቀ ተሞክሮ ማዕከል፣የተረጋጋና ሰላማዊ፣ የፈጠራና የህብር እንዲሁም የመደመር አብነት አድርጎ የመገንባት ህልማችንን ወደ ተጨባጭ እውነታ የምንቀይርበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በተለይም ህዝባችንን ከተረጂነት አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ በማውጣት በምርታማነት አስተሳሰብ እንዲቃኝ ማድረግና በግብርና፣በሌማት ትሩፋት እንዲሁም በጓሮ ልማት ንቁ ተሳታፊነቱን ማረጋገጥ የቀዳሚነት ተግባራችን መሆን እንዳለባትም አቶ መሀመድከማል አስገንዝበዋል።

የኑሮ ውድነትንና የስራ አጥነትን ጫና በመቀነስ፣የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን በፅናት በመፍታት የህዝባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተቀመጡት የትኩረት አቅጣጫዎች በበጀት ዓመቱ በላቀ ቁርጠኝነትና በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚፈጸሙም ሀላፊ ተናግሯል።

​የዓመቱን ግቦች ለማሳካት የተቋም ግንባታ ስራችንን ማጠናከር፣ የአመራሩንና የአባሉን የፖለቲካና የአስተሳሰብ ጥራት ማሳደግ እንዲሁም የመፈጸምና የማስፈጸም አቅሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገርም ሌላኛው ቀዳሚውና አስፈላጊው ተግባር መሆኑን አንስተዋል።

የውስጠ-ፓርቲ ዴሞክራሲን በማስፋት፣የአሰራር ዲስፕሊንን በማጠናከር፣ለለውጥና ለነባራዊ ሁኔታዎች ክፍት በመሆንና ለሚገጥሙን ፈተናዎች ፈጣንና ውጤታማ መፍትሄዎችን በማመንጨት የጠራ አመራር መስጠት ይጠበቅብናልም ብለዋል ሀላፊው።

በዞኑ በየደረጃው የሚገኘው አመራራችን በመረጃ፣በተጨባጭ ማስረጃና በሳይንሳዊ ትንተና ላይ ተመስርቶ የሚወስን፣የህዝብን ብሶትና ጥያቄ አስቀድሞ የሚረዳና ምላሽ የሚሰጥ የህዝብ ወገንተኝነቱን የተረጋገጠ አቅም ሊኖረው እንደሚገባም አቶ መሀመድከማል ገልጸዋል።

ድጋፍና ክትትላችን ችግር ፈቺ መሆን አለበት ያሉት አቶ መሐመድከማል የኢንስፔክሺን ስራዎችን በማጠናከር የአሰራር ክፍተትን ማረም እንደሚገባም አሳስበዋል።

​በመጨረሻም የተጣለብንን ሀገራዊና ህዝባዊ ኃላፊነት በውጤታማነት ለመወጣት ያለንን አቅም፣እውቀትና ሀብት በተቀናጀ ሁኔታ ማስተባበር ይኖርብናል ሀላፊው በአጽንኦት መክረዋል።

በአንድነት፣በትብብርና በቅንጅት በመስራት የህዝባችንን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፍላጎቶች ማሟላት የሁላችንም የጋራ ትግልና ኃላፊነት በመሆኑ መላው የዞናችን የፓርቲ አመራርና አባል የተቀመጡትን አቅጣጫዎች ወደ ወጥ ተግባር በመቀየር፣ በየተሰማራበት መስክ የለውጡ ግንባር ቀደም መሪ በመሆንና ህዝቡን አስተባብሮ በመምራት ለ2019 ዓ.ም እቅዶቻችን ስኬታማነት በሙሉ ቁርጠኝነት እንዲረባረብም አቶ መሀመድከማል ጥሪአቸውን አቀርቧል።

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ራመቶ መሐመድ በበኩላቸው ካለፈው ዓመት ስኬቶቻችን ማስቀጠልና ክፍተቶችን በማረም የተጀመሩ ስኬቶችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባ

የዞኑ አስተዳደር የስነ ምግባርና አውታሮች የትብብርና ቅንጅት ፎረም አደረጃጀት ሰብሰቢ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ከፑል ውጭ የሉ የስነ ምግባርና የሰው ሀብት ባለሙያዎች የስልጠናና የ201...
04/08/2026

የዞኑ አስተዳደር የስነ ምግባርና አውታሮች የትብብርና ቅንጅት ፎረም አደረጃጀት ሰብሰቢ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ከፑል ውጭ የሉ የስነ ምግባርና የሰው ሀብት ባለሙያዎች የስልጠናና የ2019 በጀት ዓመት የዋና ዋና ግቦች ዕቅድ ስምምነት መድረክ እየተካሄደ ነው
====

ሀምሌ 28/2018 በሀላባ ዞን አስተዳደር የስነ ምግባርና አውታሮች የትብብርና ቅንጅት ፎረም አደረጃጀት ሰብሰቢ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ከፑል ውጭ የሉ የስነ ምግባርና የሰው ሀብት ባለሙያዎች የስልጠናና የ2019 በጀት ዓመት የዋና ዋና ግቦች ዕቅድ ስምምነት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዬ አማካሪ አቶ ከድር ቆርቾ፣ የዞኑ አስተዳደር ቅሬታ አቤቱታ አቅራቢ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ባህሩ መሀመድ፣ የሀላባ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ረሸድ ኪያር፣ የዞኑ ፓርቲ ስነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ኢንጂነር መዲና አለሙ፣ ከወረዳዎችና ከተማ አስተዳደር ከፑል ውጭ የሉየስነምግባርናየሰውሀብትባለሙያዎች ተገኝተዋል።
በዚህ መድረክ ላይ የሀላባ ዞን አስተዳደር የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ክፍል አስተባበሪ አቶ አብዱላሂ ሙንድኖ የስልጠናና የ2019 በጀት ዓመት የዋና ዋና ግቦች ዕቅድ እየቀረበ ይገኛል።

‎‎ኮሚሽኑ በየደረጃው ጠንካራ የፓርቲ ተቋም እንዲፈጠርና የአባላት መብትና ግዴታ እንዲከበር ጠንካራ ስራዎች እየሰራ ነው፦አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል‎‎ሆሳዕና፦ሀምሌ 20/2018‎‎የማዕከላዊ ኢትዮ...
28/07/2026


‎ኮሚሽኑ በየደረጃው ጠንካራ የፓርቲ ተቋም እንዲፈጠርና የአባላት መብትና ግዴታ እንዲከበር ጠንካራ ስራዎች እየሰራ ነው፦አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል

‎ሆሳዕና፦ሀምሌ 20/2018

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብልጽግና ፓርቲ የሚመራበትን የመደመር እሳቤ፣እሴቶችና መርሆዎች እንዲሁም የፖለቲካ ፕሮግራሞች ለአባላትና ለአመራሩ ግልጸኝነት የመፍጠር ጠንካራ ስራ መስራቱን አመለከተ።

‎ኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ በሁሉም የክልሉ መዋቅሮች ተቋሙን የመገንባት፣የአባላትንና የአመራሩን መብትና ጥቅሞች እንዲሁም የፓርቲውን ሀብትና ንብረት የማስጠበቅ ስራዎች መስራቱንም ገልጿል።

‎የኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ የጽህፈት ቤታቸውን አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል።

‎ጽህፈት ቤቱ ጠንካራ ፓርቲ በየደረጃው እንዲገነባ ጠንካራ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች መስራቱን የገለጹት አቶ አብዱልዋሪስ፣የተሻለ ተቋማዊ አቅም ለመገንባት ብርቱ ርብርብ መደረጉንም አመላክተዋል።

‎በየደረጃው በፓርቲ ጽህፈት ቤቶች የሚሰበሰቡ ገቢዎች በህጋዊ ደረሰኝ እየተሰበሰቡ መምጣታቸውን፣የተመደቡ በጀቶች በፓርቲው የፋይናንስ አስተዳደር መመሪያዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸው ማረጋገጥ መቻሉንም ጠቁመዋል።

‎የኦዲት ስራዎች እየተጠናከሩ መምጣታቸውን፣የአባላት መብትና ግዴታ እየተከበረ እንዲመጣና ውስጠ ዴሞክራሲ እየተጠናከረ እንዲመጣ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ እንዳለም አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል ገልጸዋል።


‎ኮሚሽን ጽህፈት ቤቱ በየደረጃው የተቀናጀና ውጤታማ የድጋፍና ክትትል ስራዎች ማድረጉንም ገልጸው፣በእነዚህ ጥረቶችም የፓርቲውን ህዝባዊ አላማዎች ማስረጽና ማስገንዘብ ስለመቻሉም አብራርተዋል።

‎ሆኖም የፓርቲ መተዳደሪያ ደንቦችና መመሪያዎችን ለአባላት ለማስገንዘብ በበቂ ደረጃና ጥራት ከመስራት አኳያ፣ደንቦችና መመሪያዎች በአንዳንድ መዋቅሮች ስራ ላይ መዋላቸውን ያለማረጋገጥ ችግር፣የሚቀርቡ ቅሬታዎችን አጣርቶ ቶሎ ምላሽ ያለመስጠት ውስንነቶች እንዳሉም አቶ አብዱልዋሪስ ገልጸዋል።

‎በአንዳንድ መዋቅሮች የአደረጃጀቶች የውይይት ጊዜ መቆራረጥ፣ምልአተ ጉባኤ ሳያሟሉ ኮንፍረንሶችን ማካሄድ፣የኮሚሽኑን ተልዕኮ በአግባቡ ያለመረዳት፣የግብአት ውስንነት፣በአንዳንድ መዋቅሮች የኮሚሽኑን አመራሮች ወደ ሌላ ሃላፊነት መውሰድና የመሳሰሉ ጉድለቶች መታየታቸውንም አንስተዋል።

‎በአዲሱ በጀት ዓመት በየደረጃው ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት የበለጸገ ክልልና ሀገር ለመገንባት ተቀናጅቶና ተናቦ ለመስራት ኮሚሽኑ ዝግጁ መሆኑንም አቶ አብዱልዋሪስ ጀማል አረጋግጠዋል።

በሆሳዕና ከተማ «ሁሉ አቀፍ እመርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ» በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም የመሪ ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ፣...
28/07/2026

በሆሳዕና ከተማ «ሁሉ አቀፍ እመርታ ለሁለንተናዊ ከፍታ» በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም የመሪ ዕቅድ ኦሬንቴሽን መድረክ፣ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ላስመዘገበው የላቀ አፈጻጸም ዕዉቅና ተበርክቶለታል። ይህ አበራተች ስኬት የተመዘገበው የአንድነት፣ የትብብር፣ የትጋትና የመደመር ዕሳቤዎችን በተግባር በመተርጎም በመሆኑ፣ ለዚህ ታላቅ ድል አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ የፓርቲው አመራሮች፣ አባላት፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሜዲያ ሰራዊትና ደጋፊዎች ከሁሉ በላይ በሰላም አምባሳደርነቱና በልማት ደጀንነቱ ሁልጊዜም ለጽኑ እሴቶቻችን ተገዥ የሆነው ቅንና ትጉህ የዞናችን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን፤ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦም የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ውጤት ለቀጣዩ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች መነሻ እንጂ የማጠቃለያ ግብ ባለመሆኑ፣ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፣ የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና ብልጽግናን እውን ለማድረግ መላው አመራር፣ አባል ፣ደጋፊዎቻችንና የዞኑ ህዝብ በአዲስ እቅድ፣ በበለጠ ቁርጠኝነትና እጥፍ ትጋት ለተሻለ ተልዕኮ በጋራ እንዲንቀሳቀስ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በአንድነታችን፣በትብብር ፣በትጋታችን፣ በጽናትና በመደመር ጉዞአችን የማንሻገር ፈተና የማይሳካ ተግባር አይኖርም!!

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሺንና ስነ ምግባር ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share