Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት

Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በከተማው የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ለህዝብ ከማስተዋወቅም ባሻገር፡ ህዝብን ከመንግሥት፣ መንግሥትን ከህዝብ ጋር ለማገናኘትና ለማስተሳሰር የሚሰራ ተቋም ነው!!
(2)

“የሕብረተሰባችንን ተሳትፎ መሠረት ያደረገ የሰፈር ልማት ፕላን እውን እናደርጋለን!” ፦  አቶ ገመዳ መሀመድነሐሴ 30/2018 ዓ/ም ሀላባ ቁሊቶበሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር እየተዘጋጁ ባሉ...
05/09/2026

“የሕብረተሰባችንን ተሳትፎ መሠረት ያደረገ የሰፈር ልማት ፕላን እውን እናደርጋለን!” ፦ አቶ ገመዳ መሀመድ

ነሐሴ 30/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር እየተዘጋጁ ባሉት የሰፈር ልማት ፕላኖች (NDPs) ዙሪያ ከነዋሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ትኩረት ያደረገ ሰፊ የችግሮች ልየታ የውይይት መድረክ ተካሄዷል።

የዕለቱን የውይይት መድረክ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ፣ የክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ እሼቱ ካሰ እና የሀላባ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ የዋና ሃላፊ ተወካይና የመመሪያ ፕላን ዘርፍ ሃላፊ ኢንጂነር ሀብሲሳ መሀመድ በጋራ መርተዋል።

በመድረኩም በከተማ አስተዳደሩ በዙሪያ ቀጠናዎች በ10 ሳይቶች የሰፈር ፕላን ትግበራ በተግባር እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሕብረተሰባችንን ተሳትፎ መሠረት ያደረገ የሰፈር ልማት ፕላን እውን እናደርጋለን ብለዋል።

ከተማችንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣው የዕድገት ፍላጎት ጋር ለማጣጣም እና ዘመናዊ መዋቅር እንዲኖራት ለማድረግ የሰፈር ልማት ፕላኖች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።

የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደርና የፕላን አፈፃፀም ችግሮችን በጋራ መፍታት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

የክልሉ ፕላን ኢንስቲትዩት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እሸቱ ካሳ እንደተናገሩት ፕላኖች በወረቀት ላይ ብቻ ሳይወሰኑ መሬት ላይ ወርደው የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረው ለዚህም የባለድርሻ አካላትና የነዋሪዎች ቀጣይነት ያለው ንቁ ተሳትፎና ባለቤትነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

አሁን ላይ የሚሰራው የሰፈር ፕላን የነገዋን የከተማ ገጽታ የሚገነባ፣ የትውልድ ዕጣ ፈንታ የሚያሳድግ እና የጋራ ብልጽግና ማዕቀፍ ነው ብለዋል። ፕላኑ ተፈጻሚ ሲሆን ከተማዋን ለኑሮ ምቹ፣ ለንግድ ማራኪ እና ለትውልድ የምትመች እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

የሀላባ ዞን ከተማ ልማት መምሪያ የዋና ሃላፊ ተወካይና የመመሪያ ፕላን ዘርፍ ሃላፊ ኢንጂነር ሀብሲሳ መሀመድ ይህ የውይይት መድረክ በሂደት ላይ ያሉ የሰፈር ልማት ፕላኖችን ክፍተቶች በመሙላት የተሻለና ኑሮን ምቹ ያደረገች ከተማ ለመፍጠር ትልቅ መሠረት የሚጥል ነው ብለዋል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተዘጋጁ በሚገኙ የሰፈር ልማት ፕላኖች ዙሪያ ከነዋሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።ነሐሴ 30/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶበሀላባ ዞን...
05/09/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ እየተዘጋጁ በሚገኙ የሰፈር ልማት ፕላኖች ዙሪያ ከነዋሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 30/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

በሀላባ ዞን ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር እየተዘጋጁ ባሉት የሰፈር ልማት ፕላኖች (NDPs) ዙሪያ ከነዋሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የፕላን ችግሮች ልየታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ የውይይት መድረክ የከተማዋን ነባራዊ የፕላን ችግሮች በመነሻነት በመውሰድ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ፣ ዘላቂ የልማት ዕንቅስቃሴዎችን የሚመሩ እና የከተማዋን እድገት ከዕቅድ ጋር የሚያስተሳስሩ ፕላኖችን የሚያስችል የውይይት መድረክ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ ገልጸዋል።

የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ፡ በዛሬው ዕለት ለተቋሙ የተሰጠውን ሽልማት ዕውቅና አስመልክተው የምስጋና መልዕክታቸውን አስተላለፉ።------------------------------ነሃሴ 29/...
04/09/2026

የማዘጋጃ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ፡ በዛሬው ዕለት ለተቋሙ የተሰጠውን ሽልማት ዕውቅና አስመልክተው የምስጋና መልዕክታቸውን አስተላለፉ።
------------------------------
ነሃሴ 29/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ ማዘጋጃ

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ኢ/ሁሴን፡ በሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አማካኝነት በዛሬው ዕለት ለተቋሙ የተሰጠውን ሽልማት አስመልክቶ የምስጋና መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፡ በመልዕክታቸውም ላይ፡ “ተቋማችን በተሰጠው ኃላፊነት በትጋት፣ በቁርጠኝነትና በቡድን ሥራ ባስመዘገበው አመርቂ አፈጻጸም የተሰጠው ሽልማትና ዕውቅና ለመላው የተቋሙ ማህበረሰብ ትልቅ ማበረታቻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አያይዘው እንደተናገሩት፡ ይህ ሽልማትና ዕውቅና የተቋማችንን ቅንጅታዊ ጥረት የሚያረጋግጥ ሲሆን፡ ለወደፊቱም በላቀ ትጋትና ኃላፊነት ለመሥራት ተጨማሪ አቅም የሚሰጥ እንደሆነም አረጋግጠዋል።

ስለሆነም በዛሬው ዕለት ለተሰጠን ሽልማትና ዕውቅና ልባዊ ምስጋናቸውን በማቅረብ፡ “ይህን ስኬታማ ጉዞ ይበልጥ በማስፋት ለላቀ ውጤት እንተጋለን” ሲሉም ዋና ስራ አስኪያጁ አክለው ተናግረዋል።

▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿

➥ የኦንላይን አገልግሎት የዌብሳይት አድራሻችንን፦ www.halabamun.gov.et ይጎብኙ!

➥ የቴሌግራም ቻናላችንን፦ https://t.me/halabakullitomunicipality ይቀላቀሉ!

➥ የፌስቡክ ገፃችንን፦ https://www.facebook.com/halabakullitomunicipality ይከታተሉ!

➥ የዩቲዩብ ቻናላችንን፦ https://www.youtube.com/ ሰብስክራይብ ያድርጉ!

 !!🏆🏆🎉🎆🙏➔ የሀላባ ቁሊቶ ማዘጋጃ ቤት በ2018 ዓ/ም አፈጻጸም 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ።------------------------------ነሃሴ 29/2018 ...
04/09/2026

!!🏆🏆🎉🎆🙏
➔ የሀላባ ቁሊቶ ማዘጋጃ ቤት በ2018 ዓ/ም አፈጻጸም 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነ።
------------------------------
ነሃሴ 29/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ ማዘጋጃ

የሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በዛሬው ባዘጋጀው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ግምገማ መድረክ ላይ፡ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በ2018 ዓ/ም ከዞኑ መዋቅሮች የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገቡ፡ በልዩ ተሸላሚነት ዋንጫና ሰርተፍኬት ተበርክቶለታል።

የከተማው ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሱልጣን ኢ/ሁሴን እንደተናገሩት፡ ይህ ውጤት እንዲሁ በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን፡ መላውን የተቋማችንን አመራሮችና ባለሙያዎች ባቀናጀ መልኩ በተደረገው ያላሰለሰ ጥረትና ትጋት የተገኘ ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ​ለተገኘው ውጤትም፡ ለመላው የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ዋና ስራ አስኪያጁ፡ ይህ ልዩ ሽልማትና ዕውቅና የ2019 የበጀት ዓመት አፈጻጸማችንም ጭምር ከፍተኛ ሞራልና ስንቅ እንደሚሆንም ተናግረዋል።

▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿▿

➥ የኦንላይን አገልግሎት የዌብሳይት አድራሻችንን፦ www.halabamun.gov.et ይጎብኙ!

➥ የቴሌግራም ቻናላችንን፦ https://t.me/halabakullitomunicipality ይቀላቀሉ!

➥ የፌስቡክ ገፃችንን፦ https://www.facebook.com/halabakullitomunicipality ይከታተሉ!

➥ የዩቲዩብ ቻናላችንን፦ https://www.youtube.com/ ሰብስክራይብ ያድርጉ!

ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ በፕላን እንዲመራ በትኩረት እንደሚሰራ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ።ነሀሴ 29/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶየሀላባ ዞን ከተማ ል...
04/09/2026

ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ በፕላን እንዲመራ በትኩረት እንደሚሰራ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ አስታወቀ።

ነሀሴ 29/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

የሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የ2018 በጀት አመት ማጠቃለያ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት አመት መሪ ዕቅድ የምክክር መድረክ ተካሄደዋል።

በዚህ ወቅት የሀላባ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ዋና ሀላፊ ተወካይና የመምሪያ ምክትልና የፕላን ዘርፍ ሀላፊ ኢንጂነር ሀቢስሰ እንደገለጹት ከተሞች ለነዋሪዎች ምቹ እንዲሆኑ ለማድረግ በፕላን እንዲመራ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዞኑ በሉን ከተሞች በመደበኛና ኢንሼቲቭ ተግባራት በኮሪደር ልማት፣ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት፣ አገልግሎትን ማዘመንና መሻሸል፣ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለይቶ ከመፍታት አንፃርና በሌሎችም ተግባራቶች የተሻሉ አፈጻጸም ተመዝግቧል ብለዋል።

ይህን የተመዘገበው ውጤቶች በተለይም በከተማና በገጠር ኮሪደር ልማት እና ሌሎች ስራዎች ከመቼውም ባላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ጽዱ ከተሞችን ለመገንባትና የኮሪደር ልማት ኢኒሼቲቭን ለማሳካት አሁን በተጠናከረ መልካም መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በከተማችን ህገወጥ ተግባርን በአንድነት እና በፅናት በመቆም እንደሚገባ ጠቁመው የከተማችን እድገት ሊገቱ የሚችሉ ቁልፍ ችግሮችን ለማስቀረትና ታዳጊዋ ከተማችን እድገቷን ለማፋጠን በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በከተማ ልማት በሁሉም ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጋራ በመፍታት የሁሉንም ርብርብ እንደሚጠይቅ የገለጹት ኢንጂነር ሀቢስሰ የከተሞ እድገት ለማፋጠን ያሉ ችግሮችን በፈጥኖ በማረምና በማስተካከል በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ከተሞች ያላቸውን ሀብት በመለየት የከተማውን ገቢ በማሳደግና አሰራሩን ቀልጣፋ በማድረግ የህብረተሰቡን እንግልት ለመቀነስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መጠናከር ይገባል ብለዋል።

በመሬት አቅርቦት፣ በቤቶች ልማት ዘርፎች ፤በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት አሰጣጥና ከፕላን ጥሰት ጋር ተያይዞ እየተሰራ ያሉ ስራ ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመቀልበስና ህገወጥነትን ለመቆጣጠር ለከተሞች እድገት ሲባል ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩልን ሚና እንድጫወት አሳስበዋል።

በአጠቃላይ በበጀት አመቱ የተከናወኑ ጠንካራ ተግባርራቶችን ለማስቀጠልና ደካማቹን በማረም ቀጣይ በጀት አመት በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የዞኑ አስተዳደር ኢኮኖሚ ዘርፍ አማካሪ አቶ ሀያት ናስር በበኩላቸው በበጀት አመቱ በዞኑ በሁሉም ዘርፍ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በትኩረት መሰረቱን ገልጸዋል።

በዞኑ በትኩረት እየተሰራ ያሉ ስራዎች አንዱ ከተማ ልማት ዘርፍ በከተሞች እድገት ማፋጠን ነው ብለዋል።

ከተሞችን ለኢንቨስትመንት እና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየትና መፍትሔ ላይ በትኩረት መስራት እንደሚባ ገልጸዋል።

ፅዱና ውብ ከተሞችን ለመፍጠር የባለድርሻ አካላት በቅንጅት መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል።

የከተሞችን ዕድገት ለማፋጠን ህብረተሰቡን አሳትፎ በቁርጠኝነት መስራት ለከተሞች እድገት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት ስሆን ቅንጅታዊ አሰራሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

ለማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ቅንጅታዊ አሰራር ተገቢ መሆኑን ገልፀው በፕላን አተገባበር እና በፕላን ስምምነት ላይ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ መድረክ ላይም በ2018 ዓ/ም የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት እና የ2019 በጀት አመት መሪ ዕቅድ ቀርበው በሰፊው ተደርጎበት ቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመድረኩ ላይም የዞኑ የምክር ቤቱ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አህመዲን መሀመድ፣ የዞኑ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የየዘርፉ ሀላፊዎችና የማኔጅመንት አበላት፣ የአራቱም መዋቅር የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጆች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተገኝተዋል።

📢  ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ¦በከተማችን በየሳምንቱ በሚካሄደው የጽዳት ዘመቻ መርሃ-ግብር መሰረት፡ በነገው ዕለት ነሃሴ 30/2018 ዓ/ም ዕለተ-ቅዳሜ...
04/09/2026

📢 ለሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ¦

በከተማችን በየሳምንቱ በሚካሄደው የጽዳት ዘመቻ መርሃ-ግብር መሰረት፡ በነገው ዕለት ነሃሴ 30/2018 ዓ/ም ዕለተ-ቅዳሜ ከንጋቱ 12:00 ጀምሮ ከተማ-አቀፍ ህዝባዊ የጽዳት ዘመቻ ንቅናቄ በተለመደው መልኩ የሚካሄድ ይሆናል።

በመሆኑም የከተማው ነዋሪ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና እንዲሁም በጎ ፍቃደኞች፡ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ላይ በመገኘት በጽዳት ዘመቻ ንቅናቄው ላይ በመሳተፍ ከተማችን ከመቼውም በላይ ጽዱ፣ ውብና ለኑሮ ምቹ እንድትሆን ለማድረግ የድርሻችሁን እንድትወጡ ሲል እያሳሰበ፡ በተጨማሪም እያንዳንዱ የከተማው ነዋሪና እንዲሁም ነጋዴ የማህበረሰብ ክፍሎች በሚኖሩባቸው መኖሪያ ሰፈሮችና በሚሰሩባቸው ድርጅቶች ዙሪያ ሁሉ አካባቢያቸውን ጽዱ በማድረግ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ሲል ጥሪውን ያስተላልፋል።

👉 ማዘጋጃ ቤቱ!

#ማሳሰቢያ፦ በየቀበሌው በሚገኙ መዋቅሮች ላይ ለጽዳት ዘመቻው ህብረተሰቡን ከማስተባበርና በነቂስ እንዲሳተፍ ከማድረግ አንፃር፡ የተለመደውን እገዛ እንድታደርጉ ሲል ማዘጋጃ ቤቱ ያሳስባል።

!!

የ2018 የጳጉሜ ቀናት አከባበር  የሞዴል ህብረቶች የተግባር አፈፃፀም ና የተማሪ ምዝገባ አፈፃፀም ዙሪያ ዉይይት ተደረገ።ነሃሴ 29/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶ‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር...
04/09/2026

የ2018 የጳጉሜ ቀናት አከባበር የሞዴል ህብረቶች የተግባር አፈፃፀም ና የተማሪ ምዝገባ አፈፃፀም ዙሪያ ዉይይት ተደረገ።

ነሃሴ 29/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የከተማውን የልማትና የማህበራዊ ጉዳዮች አፈጻጸም ለማጠናከር ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለመለየትና የተያዙ ዕቅዶችን በተገቢው ሁኔታ ለማስፈጸም ከአመራሩ ጋር የሥራ ውይይት ተካሄደ።

‎የጳጉሜ ቀናት የተሻለ ነገን ለመገንባት በትልልቅ ዕቅዶችና በተግባራዊ እሴቶች ላይ በመመስረት የሚከበሩ ቀናት በመሆናቸው በከተማ ደረጃ በድምቀትና በልዩ መርሃ-ግብሮች ለማክበር የተያዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ እንደሆነ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ ገልጿል።

‎በዚህም ጳጉሜን 1 የእመርታ ቀን ጳጉሜን 2 የማንሰራራት ቀን ጳጉሜን 3 የጽናት ቀን ጳጉሜን 4 የኅብር ቀን ጳጉሜን 5 የነገ ቀን በሚሉ መርሃ-ግብሮች የጳጉሜ ቀናትን በድምቀት ለማክበርና ህብረተሰቡን በንቃት ለማሳተፍ የሚያስችሉ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲከናወኑ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

‎የሞዴል የብልጽግና ህብረቶች የልማት ሥራዎችን የኑሮ ማሻሻያ ተግባራትንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ተጨባጭ ለውጥ የሚፈጠርባቸው በመሆናቸው የተያዙ ዕቅዶች በተግባር ያሉበት ደረጃ የተገኙ ውጤቶችና ቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸው ሥራዎች ተገምግመዋል።

‎በተለይም የሞዴል ህብረቶች የሚጠበቅባቸውን ለውጥ እንዲያመጡ በተግባር የሚታዩ ሥራዎችን በማፋጠን ህብረተሰቡን በማሳተፍና የተሻለ የአፈጻጸም ባህል በመፍጠር ላይ ትኩረት እንዲደረግ ተጠቁሟል።

‎የተማሪዎች ምዝገባ በተያዘለት ጊዜና ዕቅድ መሠረት መከናወኑን ተማሪዎች ከትምህርት ውጭ እንዳይቀሩ የሚደረጉ ጥረቶችንና የምዝገባውን ሂደት የበለጠ በማጠናከር ሊሳካ የሚገባውን ውጤት ማስመዝገብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተደርጓል።

‎በዚህም የተማሪዎች ምዝገባ ሥራ በትኩረት እንዲመራ ቀሪ ሥራዎች በአፋጣኝ እንዲጠናቀቁና ህብረተሰቡ ወላጆችና የትምህርት ማህበረሰቡ በንቃት እንዲሳተፉ ትኩረት ተሰጥቷል።

‎በውይይቱ ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/መጅድ ፊጣሞ፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ም/ኃላፊና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሁሴን አብደላ እንዲሁም የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ም/ኃላፊና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መላኩ ወ/ኪዳን ተገኝተው በተነሱት የሥራ አጀንዳዎች ዙሪያ መልዕክትና አቅጣጫ አስተላልፈዋል።

‎አመራሩ በመስክ ላይ ያለውን የሥራ አፈጻጸም በቅርበት መከታተል የተጀመሩ ሥራዎችን በጥራት ማጠናቀቅ ቀሪ ሥራዎችን በተያዘላቸው ጊዜ ማስፈጸምና ለህብረተሰቡ የሚጨምሩ ተጨባጭ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

‎ውይይቱ የተነሱ ጉዳዮችን በጋራ በመገምገም ችግሮችን በጋራ በመፍታትና ቀጣይ ሥራዎችን በተጠናከረ አመራር ለማስፈጸም ጠቃሚ አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን በቀጣይም በተነሱት አጀንዳዎች ላይ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ ሁሉም የሥራ አካላት በቅንጅት እንዲሰሩ ተጠቁሟል።

03/09/2026
❝የከተሜነት ምጣኔ በመጨመር እና የከተሞችን እድገት በማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል❞~ እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ~[የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር]
03/09/2026

❝የከተሜነት ምጣኔ በመጨመር እና የከተሞችን እድገት በማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል❞

~ እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ~
[የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር]

“የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል” :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ነሐሴ 28/2018 ዓ/ምበማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ...
03/09/2026

“የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ላይ በትኩረት መስራት ይገባል” :- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በቀጣይ አምስት ዓመታት የከተሞችን እድገት ማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ የከተሞች እድገት በቀጣይ ዓመታት እየተሻሻለ መምጣት እንዳለበት በሀገር አቀፍ ደረጃ የጋራ ተግባቦት መፈጠሩን ተናግረዋል።

የከተሜነት ምጣኔ መጨመር እና የከተሞችን እድገት ማሻሻል ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

ከተሞች ለኑሮ፣ለንግድ እና ለኢንቬስትመንት ተመራጭ በማድረግ ሂደት ያልተሟሉ ጉዳዮች መኖራቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ባለፉት ዓመታት ከተሞችን ለማሻሻል የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ ነገር ግን በሚፈለገው ደረጃ የተሟላ አለመሆኑን ጠቅሰዋል።

በክልሉ በቀጣዩ አምስት ዓመታት ሰባት ዋና ዋና ከተሞች ሊተገበሩ በታቀዱ ስራዎች ላይ የጋራ ተግባቦት መፍጠር አስፈላጊ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በሚቀጥሉት ዓምስት አመታት በከተሞች እድገት ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት አስቀድሞ ማቀድ አስፈላጊ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመድረኩ የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች የአምስት ዓመታት ስትራቴጂክ እቅድ አቅርበው ምክክር እንደሚካሄድበት ይጠበቃል ሲል የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዘግቧል ።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba kullito Municipality-የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share