Amanuel city communication office

Amanuel city communication office Government website.

 # # #ሰለም በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ሁሉም ሰው የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።          **********በምስራቅ ጎጃም ዞን በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር "የጋራ መነሻና መዳረሻ...
31/07/2023

# # #ሰለም በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ሁሉም ሰው የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ።
**********
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር "የጋራ መነሻና መዳረሻ ካበጀን ከአሸናፊነት መንገድ ላይ እንገናኛለን!" በሚል መሪ ቃል በውቅታዊ ሀገራዊ የሰላም ውይይት ተካሄደ።

በውይይቱ ላይ የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ከፍለ ሙላቴ፣ አቶ አለምሸት ቢያዝን፣አቶ አየነው እብስት የዞን አመራሮች የከተማና የወረዳ አመራሮች ፣የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች ፣ወጣቶች፣ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ አማረ ሰውነት በመግብያ ንግግራቸው እንደገለፁት በከተማችን ብሎም በክልላችን የሚሰተወሉ ችግሮችን መፍትሄ በማበጀት ሰላም እንዲረጋገጥ ወጣቶች፤ የሃገር ሽማግሌዎች፤የሃይማኖት አባቶች ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የሚስችል ውይይት እንደሆነ አብራርተዋል።

ያአደሩ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን መሰከን ባለብን ስዓት ሰክነን መፈጠን ባለብን ሰዓት ፈጥነን ችግሮችን መፍታት ያስፈልጋል ያሉት ከንቲባው ስለዚህ ሌላውን ለመታገል እኛ አንድ ሁነን በመደማመጥ ለችግሮቹ እልባት እስክናገኝ ድረስ ልንታገል ይገባል ብለዋል።

የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አየነው እብስት አማራን አማራ በመግደል ገዳዮች በዘተው እርዕስ በዕራስ የመጠፋፋት ሴራ እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀው ስለዚህ አንድነትን ሊያመጣ በሚችል መንገድ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

የአማራ ህዝብ አንድ ሁኖ እንዳይቀጥል የተለያዩ አክቲቪስቶች ያልሆነ ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ነው ያሉት ደግሞ የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ አለምሸት ቢያዝን ሲሆኑ ለመረጠን ህዝብ በክልላችን ላይ የሚታዩ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እንዲፈቱ እኛም ትግል እያደረግን ነው ብለዋል።

የክልል ም/ቤት ተወካይ የሆኑት አቶ ከፍለ ሙላቴ በአማራ ላይ የተጋረጠውን ችግር የሚፈታ ህዝብ አለ ነገር ግን ያለመደማጥ ችግሮች አሉ ሰከነን ስንነጋገር አሸናፊ እንሆናለን ብለዋል።

አያይዘውም የጋራ የሆኑ ጠላቶቻችን በመለየት እና ከመንግሥት ጎን በመሆን ሁላችንም ትግላችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረኤልያስ ወረዳ በአንድ ጀምበር የስንዴ ማሳን በኩታ ገጠም በዘር እየተሸፈነ ነዉ።የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ክልል አቀፍ የ2015/2016 የመኸር...
31/07/2023

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረኤልያስ ወረዳ በአንድ ጀምበር የስንዴ ማሳን በኩታ ገጠም በዘር እየተሸፈነ ነዉ።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ በደብረ ኤልያስ ወረዳ ክልል አቀፍ የ2015/2016 የመኸር ምርት ዘመን የስንዴ ሰብል የኩታ ገጠም የዘር ማስጀመሪያ ፕሮግራም እያካሄደ ነው።

አገራችን ስንዴን በስፋት በማምረት በምግብ እራስን ለመቻልና ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት በአገር ውስጥ ምርት በመተካት የዜጎችን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት በምስራቅ ጎጃም ዞን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በአገሪቱ የስንዴ ምርት በሰፋት ከሚመረትባቸው አካባቢዎች አንዱ ነው - የምስራቅ ጎጃም ዞን። በዞኑ በተያዘው 2015/2016 የመኸር ምርት ዘመን የስንዴ ሰብል በስፋትና በጥራት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጿል።

በዞኑ በስፋት የስንዴ ሰብል ከሚመረትባቸው አካባቢዎች መካከል አንዱ በሆነው ደብረ ኤልያስ ወረዳ ጥጃጎጠር ቀበሌ የአንድ ጀንበር ኩታ ገጠም የስንዴ ዘር ክልላዊ በዓል በማካሄድ ላይ ነው።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አቶ ፈንታሁን ቸኮል በተያዘው 2015/2016 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን ከ607 ሽህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር በመሸፈን ከ22 ሚሊዮን ኩንታል በሊይ ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በመኸር ምርት ዘመኑ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የኩታ ገጠም አሰራር በስፋት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት መምሪያ ኀላፊው በዞኑ 212 ሽህ 068 ሄ/ር የሚሆነው በስንዴ ሰብል የሚሸፈን መሆኑን አስረድተዋል።

በዛሬው ዕለት ክልላዊ የአንድ ጀንበር የስንዴ ዘር በዓል እየተከበረ በሚገኝበት ደብረ ኤልያስ ወረዳ ከ5 ሽህ ሄክታር በላይ መሬት በአንድ ጀንበር የስንዴ ዘር ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑን አቶ ፈንታሁን አስረድተዋል።

በዞኑ በምርት ዘመኑ በዘር ከሚሸፈነው አጠቃላይ ማሳ ጤፍ ፣ስንዴና በቆሎ ሰብሎች 497 ሽህ ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም አሰራር እንደሚሸፈን የገለፁት መምሪያ ኀላፊው በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የኩታ ገጠም አሰራር እየተተገበረ ነው ብለዋል።

በተያዘው 2015/2016 የመኸር ምርት ዘመን በዘር ከሚሸፈነው ከ607 ሽህ ሄክታር በላይ ማሳ 68 በመቶ የሚሆነው በማሳ ኩታ ገጠም አሰራር እንደሚሸፈን አቶ ፈንታሁን ጨምረው ገልፀዋል።

በአማራ ክልል በተያዘው የመኸር ምርት ዘመን 5 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር ለመሸፈን መታቀዱንና እስካሁን ባለው ጊዜ 3.5 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ በዘር መሸፈኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አቶ ቃል ኪዳን ሽፈራው አስረድተዋል።

ከ160 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የግብርና ምርት ለማግኘት መታቀዱን የገለፁት ምክትል ቢሮ ኀላፊው
በክልሉ በተያዘው የመኸር ምርት ዘመን 1 ማሊዮን ሄክታር ማሳ በስንዴ ሰብል ለመሸፈን ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

እስካሁን በዘር ከተሸፈነው ማሳ ውስጥ 1 ነጥብ 1 ሄክታር ማሳ በኩታ ገጠም አሰራር መዘራቱን ያስረዱት አቶ ቃልኪዳን በአጠቃላይ በዘር ከሚሸፈነው ማሳ ውስጥ 2 ሚሊዮን ሄክታር በኩታ ገጠም አሰራር እንደሚሸፈን ጨምረው አስረድተዋል።

ማሳቸውን በኩታ ገጠም አሰራር በስንዴ ሰብል እየሸፈኑ የሚገኙ በደብረ ኤልያስ ወረዳ የጥጃጎጠር ቀበሌ ነዋሪዎች በበኩላቸው ሰብላቸውን በኩታገጠም ዘዴ መዝራታቸው ለአሰሳ ስራ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠረ በተጨማሪ በምርት ጭማሪ ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው ብለዋል ያለዉ የዞኑ ኮሙኒኬሽን ነዉ።

 # #የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲቸው ተሸኙ።************************************************በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻ...
30/07/2023

# #የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ዩኒቨርስቲቸው ተሸኙ።
************************************************

በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳ እና በከተማ አስተዳድሩ የሚገኙ የ2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከል ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተሸኝተዋል።

በሽኝት ኘሮግራሙ ላይ የወረዳው የትምህርት አመራሮች፣ የተማሪ ወላጆች እንዲሁም የወረዳው እና የከተማ አስተዳድሩ የጸጥታ አካላት በተገኙበት ወደ ወደ መፈተኛ ጣቢያቸው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ተሸኝተዋል።

በሽኝኝቱ የተገኙት የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በላቸው አበበ በ2ኛው ዙር የ12 ኛ ክፍል ፈተና መርሃ ግብር በወረዳው በግልና በመደበኛው በተፈጥሮ ሳይንስ 6 መቶ 18 ተማሪዎችን ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና እንደ ሚያስፈትኑ በመግለጽ በመጀመርያው ዙር ፈተና የወሰድትን የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ስነ-ምግባር እንዲደግሙት ጥሪ አቅርበዋል ሲል ማቻክል ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
መልካም ዕድልን እንመኛለን !!!

~~~ገቢያችን ለልማታችን ለዕድገታችን ! ➡️ግብር በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር የማይተካ ሚና አለው፡፡➡️  የምስራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ባለፉት አራትና አምስት አ...
29/07/2023

~~~ገቢያችን ለልማታችን ለዕድገታችን !

➡️ግብር በዜጎች መካከል ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር የማይተካ ሚና አለው፡፡
➡️ የምስራቅ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ባለፉት አራትና አምስት አመታት ወጭውን በገቢ የመተካት አቅምን ለማሳደግ ሁሉንም የገቢ አርእስቶች አሟጦ በመጠቀም የተጀመረው ጅማሮ እጅግ አበረታች ነበር፡፡

✅ ለዚህ ደግሞ ማሳያው ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ስርዓት በመዘርጋት ዜጎች በተለይም የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች በአንድ ጀንበር ግብራቸውን እንዲከፍሉ የተደረገው ጥረት ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

የዞናችን የግብር አሰባሰብ ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እድገት እያመጣ የዜጎች የመክፈል ፍላጎች መሻሻል እያሳዬ ነው፡፡
📲 ለአብነት ከንግዱ ማህበረሰብና ከልዩ ልዩ አርዕስቶች
✔ በ2011 ዓም ደብረ ማርቆስ ከተማን ጨምሮ ከመደበኛ ገቢና የከተማ አገልግሎት አገልግሎት 818 ሚሊዬን 333ሽ 673 ብር የተሰበሰበ ሲሆን
✔ በ2012 ዓም 1ቢሊዬን 002 ሚሊዬን 718ሽ 071 ብር
✔ በ2013 በጀት አመት 1ቢሊዬን 351 ሚሊዬን 682ብር 485 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡
✔ በ2014 በጀት አመት ደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ወደ ሪጂኦ ፖሊታንትነት በማደጉ ከእርሱ የሚሰበሰበው ቢቀርም ዞኑ የገቢ ማግኛ ዘዴዎችን አፈላልጎ ለመጠቀም ባደረገው ጥረት 1 ቢሊዬን 365 ሚሊዬን 309ሽ 056 ብር መሰብሰብ ችሏል፡፡
✔ በዚህ አመት ደግሞ በዚህ አመት 1 ቢሊዮን 725 ሚሊዮን 599ሽ 973 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡
✔ በዚህ አመት የተሰበሰበው ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 360 ሚሊዮን 290ሽ 918 ብር ብልጫ ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
📲ከመሬት መጠቀሚያ ግብር አንጻር ሲታይ፦

✔ በ2011 በጀት አመት 32 ሚሊዬን 571ሽ 143 ብር የተሰበሰበ ቢሆን የማይከፍሉ አካላትን በማጥናት በተሰራው ስራ በ2015 በጀት አመት 40 ሚሊዬን 644 ሽ 107 ብር መሰብሰብ ተችሏል፡፡

በአጠቃላይ እንደ ምስራቅ ጎጃም ዞን የገቢዎች መምሪያ ከዓመት ዓመት የጥራትና የዕድገት አቅሙን በማሻሻል የተጀመረውን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማሳካት እየሠራ ይገኛል ።
መረጃው የዞኑ ኮሙኒኬሽን ነው።

"የህብረተሠቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ግብርን በአግባቡ መሠብሠብ ወሣኝነት አለው።"          አቶ እንዳዎቀ አዳሙ የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት ሃላፊ  በምስራቅ ጎጃም ...
29/07/2023

"የህብረተሠቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ግብርን በአግባቡ መሠብሠብ ወሣኝነት አለው።"

አቶ እንዳዎቀ አዳሙ
የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት ሃላፊ

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ ገቢ 33,999,548 ብር እንዲሁም ከአገልግሎት ገቢ9,104,943 በድምሩ 43,104,491ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ሲሰራ መቆየቱን የገለፁት የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ እንዳዎቀ አዳሙ

እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከሁለቱም የገቢ አርዕስቶች በድምሩ 52,815,404.11ብር መሰብሰብ የተቻለ መሆኑን አብራርተዋል። ሃልፊው አያይዘውም የማህበረሰቡን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ ግብርን በአግባቡ መሰብሰብ ወሳኝነት አለው በማለት ይህን ለማሣካት የህብረተሠቡ፣የአመራሩ፣የፈፃሚ አካላት የባለሙያውና እንዲሁም የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም አቶ እንዳዎቀ
በአዲሱ በጀት ዓመትም ከዚህ የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ በከተማ አስተዳድራችን ለሚሰሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች ገቢያችን አስተዋፅኦ እንሚያደርግ በመገንዘብ በጋራ ለመስራት ጥሪ አስተላልፈዋል።
አማኑኤል ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት

27/07/2023
ምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያና ሸበል በረንታ ወረዳ  በበጀት አመቱ ዜጎችን ከዐይነስውርነት በመታደግ  በክልል ደረጃ በተካሄደ ውድድር 1ኛ በመውጣታቸዉ የዋን...
27/07/2023

ምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያና ሸበል በረንታ ወረዳ በበጀት አመቱ ዜጎችን ከዐይነስውርነት በመታደግ በክልል ደረጃ በተካሄደ ውድድር 1ኛ በመውጣታቸዉ የዋንጫና የቁሳቁስ ተሸላሚ ሆኑ፡፡

ዞኑ አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ የሆነው በአንድ ዓመት ውስጥ 13ሽ 874 ሰዎችን ከዓይነ ስውርነት በመታደጉ በክልል ደረጃ በተካሄደ ውድድር 1ኛ በመውጣቱ ነው፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ሽልማት የተበረከተለት ትራኮማን በመከላከልና መቆጣጠር ሥራው የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለመገምገምና በቀጣይም በሽታውን ለማስወገድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር በተካሄደበት የማጠቃለያ ስነ ስርዓት ላይ ነው፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው የትራኮማ በሽታን ከዞኑ ነጻ በማድረግ ዜጎችን ከዓይነ ስውርነት ለመታደግ ሌትና ቀን የሰሩ አካላትን አመስግነዋል፡፡ አቶ አብርሃም በመልእክታቸው ይህ ተግባር ተወዳድሮ አንደኛ ከመውጣት በላይ በዓይነ ስውርነት የሚሰቃዩ ዜጎችን ቀዶ ጥገና በማድረግ ከአይነ ስውርነት በመታደግ ብርሃን እንዲያገኙ ማድረግ የሚሰጠው የህሌና እርካታ ይበልጣል ብለዋል፡፡

በዚህ ስራ የተሳተፉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች አስተዳደሩ በእጅጉ ያመሰግናል ያሉት አቶ አብርሃም በቀጣይ ትራኮማን ለማስወገድ ለምንሰራው ስራ ሁሉም አካል ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለስራችን መሳካት በጤናው ዘርፍ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በተጨማሪ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የአጋር አካላት ሚና ከፍተኛ ነበር ያሉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ መልካሙ ጌትነት በበጀት አመቱ በተደረገ ርብርብ 13ሽ 874 ሰዎችን ከዓይነ ስውርነት መታደግ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ ስራ በርካቶች እንዲሳተፉበት አድርገናል ያሉት አቶ መልካሙ የታካሚ ልየታ በሚካሄድበት ወቅት ከፍተኛ እርብርብ ያደረጉ የምስራቅ ጎጃም ህዝብ፣የመንግስት ሰራተኛ፣ጤና ባለሞያዎች፣በየደረጃው ያሉ አመራሮች እና አጋሮች ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በሽታው የዞኑ ህዝብ የጤና ችግር ከማይሆንበት ደረጃ ለማድረስ በሚደረገው ትግል የሚጠበቅብንን እንድንወጣ በማለት ጠንካራ ጥሪ አቅርበዋል።

✅ምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር 1ኛ በመውጣት
✔ ዋንጫና ሰርተፍኬት
✅ ምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ 1ኛ በመውጣት
✔ ዲስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ✔ ኤልሲዲ✔፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን
✅ ሸበል በረንታ ወረዳ 1ኛ በመውጣት
✔ ዲስክቶፕ ኮምፒዩተር፣
✔ ኤልሲዲ✔፣
✔ ፎቶ ኮፒ ማሽን፣
✔ ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሲሆኑ ከዞኑ

✅ 3 ትምህርት ቤቶች እያንዳንዳቸው ሰርትፍኬትና 2000 ሊትር የሚይዝ ሮቶ እና 4 የዓይን ቆብ ቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ከ16-12ሽ ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡
East Gojjam Communication

 # # #ሰዉን ለአዳጋ በማጋለጥ  ወንጀል የተጠረጠረችዉ ግለሰብ ላይ የፍርድ ውሳኔ ተሰጠ፡፡***********************************************ሰዉን ለአዳጋ በማጋለጥ ...
27/07/2023

# # #ሰዉን ለአዳጋ በማጋለጥ ወንጀል የተጠረጠረችዉ ግለሰብ ላይ የፍርድ ውሳኔ ተሰጠ፡፡
***********************************************
ሰዉን ለአዳጋ በማጋለጥ ወንጀል የተጠረጠረችዉ ግለሰብ በ1 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

በአማኑኤል ከተማ አስተዳድር 02 ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ የ21 አመቷ ካሳነሽ እንየዉ ሚያዚያ15/2015 ዓመተ ምህረት በግምት ከጥዋቱ 12፡30 ሰዓት ላይ በአማኑኤል ከተማ አስተዳድር 01 ቀበሌ ልዩ ቦታዉ አማኑኤል ጤና ጣቢያ አካባቢ 1 ዓመት ከ9 ወር የሆነዉ ወንድ ልጇን ጥለዉ የተገኘ በመሆኑ ክስ ተመስርቶባታል፡፡

በዚህም ተከሳሽ ካሳነሽ እንየዉ የፈፀመችዉ ሰዉን ለአዳጋ የማጋለጥ ወንጀል በኢ.ፊ.ድ.ሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 574/1 ላይ የተመለከተውን የተላለፈ ነዉ በማለት በፈፀመችዉ ሰዉን ለአዳጋ የማጋለጥ ወንጀል የማቻክል ወረዳ አቃቢ ህግ በመስረተው ክስ አመላክቷል፡፡

የማቻክል ወረዳ ፍርድ ቤትም ክሱን በመቀበል በሰዉና በሰነድ ማስረጃ ካረጋገጠ በኋላ ጥፋተኛ ናት በማለት ሀምሌ 6 ቀን 2015 ዓመተ ምህረት በዋለው ችሎት ተከሳሽ ካሳነሽ እንየዉ በተከሰሰችበት ወንጀል በ1 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት እንድትቀጣ መወሰኑን የማቻክል ወረዳ ፍርድ ቤት ህዝብ ግንኙነት ክፍል መረጃውን አድርሶናል ሲል ማቻክል ኮሙንኬሽን ዘግቧል።

የመኖሪያ ቤት መስረያ ቦታ ለማግኘት ተደራጅተው ሲጠባበቁ ለነበሩ የ22 የቤት ማህበሮች እና ለ17 ተነሽ አርሶ አደሮችን የቦታ ርክክብ ተደረገ።           **********በምስራቅ ጎጃም...
27/07/2023

የመኖሪያ ቤት መስረያ ቦታ ለማግኘት ተደራጅተው ሲጠባበቁ ለነበሩ የ22 የቤት ማህበሮች እና ለ17 ተነሽ አርሶ አደሮችን የቦታ ርክክብ ተደረገ።
**********
በምስራቅ ጎጃም ዞን በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት መስረያ ቦታ ለማግኘት ተደራጅተው ሲጠባበቁ ለነበሩ የ22 የቤት ማህበሮች እና ለ17 ተነሽ አርሶ አደሮችን የቦታ ርክክብ ተደርጓል።

በቦታ ርክክቡ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ አማረ ሰውነት እና የከተማው አመራሮች ጨምሮ እንዲሆም የማህበሩ አባለት ተገኝተዋል።

 # # #እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ!!!                  ****** የብዙ ሰዎችን የውሃ እጦት ችግር ይቀርፋል ተብሎ ተስፍ የተጣለበት በየውላ እየተቆፈረ የሚገኘው ጥልቅ የመጠ...
26/07/2023

# # #እንኳን ደስ አለን ደስ አላችሁ!!!
******
የብዙ ሰዎችን የውሃ እጦት ችግር ይቀርፋል ተብሎ ተስፍ የተጣለበት በየውላ እየተቆፈረ የሚገኘው ጥልቅ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ ቆፋሮ ስራው ተጠናቀቀ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ከ7.5 ሚሊዮን ብር በላይ በየውላ እየተቆፈረ የሚገኘው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሮ ስራው ተጠናቅቆ ተቆፍሮ የወጣውን ውሃ የማጥራት ስራ እየተከናወነ እንደሆነ የከተማው ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ገለፀ።

የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ስራአስኪያጅ አቶ እንየው እብሰት ጥልቅ የመጠጥ ውሃ ቁፋሮ ስራውን ለማከናወን ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ታያይዞ ብዙ ውጣ ውረዶች እንደነበሩ በመግለፅ አሁን ላይ የቁፍሮ ስራው ተጠናቆ የውጣውን ውሃ ንፁህ እንዲሆን የማጥራት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። ከዚህ ስራ በመቀጠልም ከተቆፈረበት ቦታ የውላ እስከ አማኑኤል ከተማ የውሃ መስመር ዝርጋት ስራ ይቀጥላል ብለዋል።

የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባና የውሃ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አማረ ሰውነት በከተማችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ አለመኖር አሁን ላይ ተቆፍሮ የተጠናቀቀው የንፁህ መጠጥ ውሃ ለከተማችን ነዋሪ ትልቅ ተሰፍ ሰጭ ነው ስለዚህ ለከተማችን ነዋሪ በሙሉ እንኳን ደስ አለን ደሰ አለችሁ ማለት እወዳለሁ ብለዋል።

የከተማውን የውሃ እጥርት በመረዳት የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮውን ስራው እንዲጠናቀቅ ከጎናችን በመሆን አሁን በደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ በተለያዩ ነገሮች ሲደግፉ ለነበሩ አካላት በአስተዳደር ምክርቤቱ ስም ልባዊ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ህዝባችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ስራውን ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በምናደርገው የስራ እንቅስቃሴ ድጋፍ እንድታደርጉ በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።

"ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለዞናችን"!እጅግ ውድና የከበሩ ማዕድናት መገኛ ምስራቅ ጎጃም ዞን 👇👇👇ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ ጥናቶች የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳር ከሰብል ልማት በተጨማሪ...
26/07/2023

"ማዕድን አዲስ የንጋት ተስፋ ለዞናችን"!

እጅግ ውድና የከበሩ ማዕድናት መገኛ ምስራቅ ጎጃም ዞን 👇👇👇

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚወጡ ጥናቶች የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳዳር ከሰብል ልማት በተጨማሪ በማዕድን ሀብቱ ዘርፈ ብዙ ዕምቅ ሀብት ያለው መሆኑ እየታወቀ የመጣ ዞን ነዉ፡፡

መምሪያዉ ራሱን ችሎ ከተቋቋመ የአንድ አመት ብቻ እድሜ ያለዉ ቢሆንም ዉጤታማ ስራ እየሰራ ነዉ። ከተሠሩ ስራዎች በጥቂቱ ፦

✅ ለዞናችንን በክልል ደረጃ የተሰጡ ፈቃዶች👎
👉 የስሚንቶ ምርመራና ማምረት ፈቃድ የወሰዱ ብዛት 5
👉 ከፍተኛ ደረጃ ጥቁር ድንጋይ ጠጠር ማምረት ፈቃድ የወሰዱ ብዛት 16
👉 የግራናይት ምርመራና ማምረት ፈቃድ የወሰዱ ብዛት 114 የማምረት ፈቃድ የወሰዱ 64
👉 እምነበረድ ምርመራና ማምረት ፈቃድ የወሰዱ ብዛት 12 የማምረት ፈቃድ የወሰዱ 3
👉 የጅብሰም ማምረት ፈቃድ የወሰዱ ብዛት 21
👉 ሲሊካ ላንድ ማምረት ፈቃድ የወሰዱ ብዛት 3 ናቸው፡፡
✅ በ2015 በተሰበሰበ የማዕድን ሃብት መረጃ ውስጥ ዋና ዋናዎቹ👎
➡️ የኢንደስትሪ ማዕድናት 👇
✔ ግራናይት፣
✔ የኖራና የሲሚንቶ ድንጋይ፣
✔ የጀሶ ድንጋይ፣
✔ ሸክላ አፈር፣
ሲሊካ ላንድ
➡️ የኮንስትራክሽን ማዕድናት 👇
✔ አሸዋ ድንጋይ ፣
✔ ሰሌክትድ ማቴሪያል
➡️ ብረት ነክ ማዕድናት የሚገኙባቸው ወረዳዎች👇
✔ እነብሴ ሳር ምድር፣
✔ እናርጅ እናውጋ፣
✔ ሸበል በረንታ
➡️ የጅኦተርማል የማዕድን ውሃክምችት
✔ በደብረ ኤልያስ ወረዳ

ከ2011 እስከ 2015 ድረስ ባለው ጊዜ በዘርፉ በባህላዊና በአነስተኛ 1282 ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡

👉 በዚህም በባህላዊ 13ሽ 317 በአነስተኛ 2ሽ 280 ወጣቶች የስራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
👉 ፈቃድ ከተሰጣቸው ውስጥ 2468 የሚሆኑ በባህላዊና በአነስተኛ ደረጃ ፈቃዳቸውን ጨርስው ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡
👉 በማእድን ዘርፍ 47 ሚሊዬን 039ሽ 745 ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል፡፡

ዛሬም ላይ በህግ ማዕቀፎች መሠረት ልዩ ልዩ ማዕድናት እየተጠኑ ይገኛሉ ።

መረጃው የዞን ኮሙንኬሽን ነው።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ በመጀመሪያዉ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑባቸዉ ዩንቨርስቲዎች እንዲገቡ ያደረጉ አጋርና ባለድርሻ አካላትን አመስግኗ...
25/07/2023

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ በመጀመሪያዉ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑባቸዉ ዩንቨርስቲዎች እንዲገቡ ያደረጉ አጋርና ባለድርሻ አካላትን አመስግኗል፤ በ4ቱም የፈተና ማዕከላት በሰላም ገብተዋል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ እንደገለጽት በመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ 14,279 ተማሪዎች በ4ቱም የፈተና ማዕከላት በሰላም ገብተዋል።

ተማሪዎች ከሀምሌ 19_21/2015 ዓ.ም በባህርዳር፣ በመካነሰላም እና በደብረማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ለተከታታይ 3 ቀናት ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

ይህን ጉዞ በማስተባበር ሂደት ትልቁን ኃላፊነት የወሰዳችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች፤ የጸጥታ መዋቅር አባላትና አመራሮች፤ የተሽከርካሪ ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች፤ የመንገድ ደህንነት ባለሙያዎች፤ የትምህርት ቤተሰብ፤ በየአካባቢው ያላችሁ የዩንቨርሲቲ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎችም አካላት ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ይህ የቅንጅት ስራ ቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነቴ ጽኑ ነው።

እነዚህ ተማሪዎች ቀጣይ ሀምሌ 22 እና 23 ወደ አካባቢያቸው ስለሚመለሱና የሁለተኛ ዙር ተፈታኞችም በተመሳሳይ ቀናት ወደ ዩንቨርስቲ ስለሚገቡ ይህንን ሊመጥን የሚችል ቅድመ ዝግጅት እንዲደረግ አደራ እላለሁ !!

ሁላችንም ዓመቱን ሙሉ የደከምንበትን ውጤት እንደምናስመዘግብ ተስፋ በማድረግ ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን መሌካም የፈተናና የስኬት ጊዜ እንዲገጥማቸው ከልብ እመኛለሁ !!

አቶ ጌታሁን ፈንቴ
የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ
#ምስራቅ ጎጃም ኮሚዩኒኬሽን

Address

Amanuel
Amanu'el
AMANUEL

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanuel city communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amanuel city communication office:

Share