Ambo Agricultural Research Center - AARC

Ambo Agricultural Research Center - AARC Ambo Agricultural Research center official page.

Technical Research Field Visit @ Ambo ARC with top management of EIAR, National & International partners.
24/10/2025

Technical Research Field Visit @ Ambo ARC with top management of EIAR, National & International partners.

አምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የአርሶ አደሮች መስክ ቀን አካሄደ፤ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም. አምቦ፤በማዕከሉ በግብርና ኤክስቴንሽን ምርምር ዘርፍ አማካይነት በወሊሶ ወረዳ ጉሩራ ባካ እና ኦቢ...
18/10/2025

አምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የአርሶ አደሮች መስክ ቀን አካሄደ፤
ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም.
አምቦ፤
በማዕከሉ በግብርና ኤክስቴንሽን ምርምር ዘርፍ አማካይነት በወሊሶ ወረዳ ጉሩራ ባካ እና ኦቢ ኮጂ ቀበሌዎች የደጋ በቆሎ እና የስንዴ ዝርያዎችን ለማስተዋወቅ በተሰራው ስራ ላይ የመስክ ቀን አከናውኗል። “አምቦ” እና “ጅባት” የደጋ በቆሎ ዝርያዎች እንዲሁም “ አባይ” እና “ዳካ” የስንዴ ዝርያዎችን የማስተዋወቅ ስራ ተሰርቷል፡፡

የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የመስክ ቀን አካሄደ፤ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም.አምቦበመስክ ቀኑ በማዕከሉ በግብርና ኤክስቴንሽን ምርምር ዘርፍ በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የተሰራውን የደ...
10/10/2025

የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የመስክ ቀን አካሄደ፤
መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም.
አምቦ
በመስክ ቀኑ በማዕከሉ በግብርና ኤክስቴንሽን ምርምር ዘርፍ በአርሶ አደሮች ማሳ ላይ የተሰራውን የደጋ በቆሎ ዝርያ ማስተዋወቅ ስራዎችን እንዲሁም በአፈርና ውሃ ምርምር ዘርፍ የበቆሎ ሰብልን መሰረት በማድረግ የተሰራውን የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ማዳበሪያ (Vermicompost) ቅንጅታዊ አጠቃቀም ላይ በምዕ/ሸዋ ዞን ቶኬ ኩታዬ ወረዳ ሌንጫ እና ኮልባ አንጨቢ ቀበሌዎች ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን አርሶ አደሮች፣ ግብርና ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም. የመስክ ቀን አካሄዶአል፡፡
ማዕከሉ ባካሄደው የአርሶ አደሮች መስክ ቀን በዓል ላይ የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ጀማል ቶላ እንደተናገሩት ማዕከሉ የአካባቢው ተጠቃሚ ማህበረሰቦች ምርትና ምርታማነታቸው እንዲያድግ የተለያዩ የምርምር ውጤቶችና ሙከራዎች እያደረሰ ይገኛል ያሉት ዳይሬክተሩ በዚሁ መስክ ቀን በቶኬ ኩታዬ ወረዳ በአርሶ አደር ማሣ ላይ ለጉብኝት የበቃው ከምርምር ማዕከሉ በምርምር የተገኘው የደጋ በቆሎና የማዳበሪያ አጠቃቀም ቴክኖሎጂዎች አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም የምርምር ማዕከሉ ከበቆሎ ቴክኖሎጂ ጎን ለጎንም በአካባቢው ላይ የተለያዩ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የምርምር አድማሱ ሰፊ መሆኑን በመግለጽ ለወደፊትምን የተጠቃሚውን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቴክኖሎጂ በማቅረብ ለአርሶ አደሮች ለማዳረስ ሰፊ ስራ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ በማዕከሉ የአፈርና ውሃ ምርምር ቡድን ግኝት ወይም ውጤት የሆነውን የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ቅንጅታዊ አጠቃቀም በበቆሎ ሰብል ላይ ያስገኘው ውጤት የተጎበኘ ሲሆን፤ በማዕከሉ የአፈርና ውሃ ምርምር አስተባባሪ የሆኑት አቶ ቶልቻ ቱፋ በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ገለጻ ይህ የማዳበሪያ አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግም ብሎ የአፈር ለምነትን የሚጠብቅ እንዲሁም በአሁን ወቅት እየናረ የመጣውን የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ወጪ በመቀነስ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የዕፅዋት ጥበቃ እና ደጋ በቆሎ ምርምሮችን በብሔራዊ ደረጃ የሚያስተባብር መሆኑ ይታወቃል፡፡

የትምህርት መሳሪዎች ድጋፍ ተደረገ፤14/1/2018 ዓ.ም.ማዕከሉ ለአካባቢ ማህበረሰብ በተለያዩ ድጋፎች ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የ2018 ዓ.ም. የት...
24/09/2025

የትምህርት መሳሪዎች ድጋፍ ተደረገ፤
14/1/2018 ዓ.ም.
ማዕከሉ ለአካባቢ ማህበረሰብ በተለያዩ ድጋፎች ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የ2018 ዓ.ም. የትምህርት ዘመንን አስመልክቶ በአምቦ ወረዳ ቢሎ ቀበሌ ዳባ ቢሎ ትምህርት ቤት ለሚገኙ የአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የመማሪያ ደብተርና እስኪብርቶ ድጋፍ አድርጓል፡፡ በዚሁ የትምህርት ዘመን በአምቦ ከተማ ለሚገኙ ቁጥራቸው 42 ለሚሆኑ ተመሳሳይ ቤተሰቦች ድጋፍ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡
Deeggarsi Meeshaaleen barnootaa taasifame
14/1/2018 A.L.I.
Giddugalichi deeggarsa adda addaa hawaasa naannichaaf taasifamuun itti gaafatamummaa hawaasummaa isaa bahachaa jira; Kanaan wal qabatee bara 2018 bara barnootaa ilaalchisee, Aanaa Amboo Gandaa Biloo mana barumsaa Dhaabaa Bilootti ijoollee maatii harka qalleeyyiif barullee fi qalama kenneera. Bara barnootaa kana keessatti magaalaa Ambootti maatii walfakkaataa 42f deeggarsi taasifamee akka ture ni yaadatama.

በማዕከሉ ሁለት ሁነቶች ተካሄዱ፤ መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.አምቦ በማዕከሉ ለሚገኙ ጥበቃ ሰራተኞች ወቅታዊ እና የጥበቃ አሰራሮችን ማዘመንን መሰረት ያደረገ እንዲሁም በተመሳሳይ ለማዕከ...
23/09/2025

በማዕከሉ ሁለት ሁነቶች ተካሄዱ፤
መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም.
አምቦ
በማዕከሉ ለሚገኙ ጥበቃ ሰራተኞች ወቅታዊ እና የጥበቃ አሰራሮችን ማዘመንን መሰረት ያደረገ እንዲሁም በተመሳሳይ ለማዕከሉ ሴት ሰራተኞች “leadership management” ጋር የተገናኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተስጥቶአል፤

16/09/2025
የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል በአካባቢው ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፤አምቦ 06/01/2018 ዓ.ም.ማዕከሉ ከምርምር ስራዎች ጎን ለጎን ማህበራዊ ሃ...
16/09/2025

የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል በአካባቢው ለሚገኙ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ልጆች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፤
አምቦ
06/01/2018 ዓ.ም.
ማዕከሉ ከምርምር ስራዎች ጎን ለጎን ማህበራዊ ሃላፊነቶችን እየተወጣ የሚገኝ ሲሆን በዘንድሮው 2018 ዓ.ም. ትምህርት ዘመን ከአምቦ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ጋር በመተባበር በተለያየ ምክንያት ድጋፍ ለሚያሻቸው እና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ 42 አቅም ለሌላቸው ልጆች ድጋፍ አድርጓል፡፡

08/08/2025

New Breakthrough on Faba Bean Root Rot in Ethiopia
************
EIAR, 07 August 2025

A study led by researchers from the Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR) and the University of Western Australia has uncovered a complex mix of soilborne pathogens affecting faba bean crops across seven major zones in Ethiopia. This groundbreaking new study has revealed that root rot is triggered by a complex of soilborne pathogens, causing significant yield losses in Ethiopian faba bean production. Using advanced molecular tools, including the quantitative PRIDICTATM B test, PCR and Next Generation Sequencing (NGS), or DNA metabarcoding, researchers analyzed 150 soil samples across seven major growing zones and detected over 60 soilborne pathogens, of which 20 are new records.
The Paper Novelty Findings
• Pioneering Pathogen Identification: This study is the first to comprehensively identify the full spectrum of soilborne pathogens and their complex interactions affecting faba bean crops in Ethiopia. Unlike earlier research, which often depended on less accurate diagnostic methods, this investigation offers a detailed and reliable picture of the actual pathogen communities.
• First Records in Ethiopia: The research documents, for the first time in Ethiopia, the presence of several critical pathogens, including Aphanomyces euteiches, Phytophthora megasperma, Thielaviopsis basicola, and five Rhizoctonia solani anastomosis groups (AG2.1, AG2.2, AG3, AG4, and AG5).
• New Fusarium Discoveries: Utilizing Next-Generation Sequencing (NGS), the study identified numerous Fusarium species that had not previously been reported in Ethiopia, such as F. redolens, F. ananatum, F. brachygibbosum, F. brevicaudatum, F. clavum, F. flagelliforme, F. keratoplasticum, F. napiforme, F. nelsonii, F. neocosmosporiellum, F. torulosum, and F. vanettenii.
• Use of Cutting-Edge Tools: The study applied highly sensitive and accurate molecular diagnostics, including species-specific quantitative

በማዕከሉ አምቦ ወረዳ የስንዴ ክላስተር ዘር ማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሄዶአል፤ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም. አምቦ፤በማዕከሉ በግብርና ኤክስቴንሽን ክፍል አማካይነት በአምቦ ወረዳ ቢሎ ቀበሌ 1...
18/07/2025

በማዕከሉ አምቦ ወረዳ የስንዴ ክላስተር ዘር ማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሄዶአል፤
ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም.
አምቦ፤
በማዕከሉ በግብርና ኤክስቴንሽን ክፍል አማካይነት በአምቦ ወረዳ ቢሎ ቀበሌ 15 ሄክታር ላይ የሚሰራውን የስንዴ ክላስተር ዘር ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም. የምዕ/ሸዋ ዞን እና የአምቦ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ዘር የማስጀመሪያ መረሃ-ግብር ተካሄዶአል፡፡
በማስጀመሪያ መረሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምዕ/ሸዋ ዞን ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ አበበ ሁማ እንደተናገሩት የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል በዞናችው በርካታ ወረዳዎች በበርካታ የምርምር ዘርፍ ስራዎችን በማስፋት እና በማጠናከር ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ እና አርሶ አደሩ የተሻሻለ የግብርና ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ የእርሻ ሕይወቱን ከመለወጥ አንፃር በርካታ አመርቂ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው ለማዕከሉ ምስጋናና እውቅና ሰጥተዋል፡፡

Address

West Shewa Zone
Ambo
037

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ambo Agricultural Research Center - AARC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share