የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ/Konta Zone Justice Department

  • Home
  • Ethiopia
  • Ameya
  • የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ/Konta Zone Justice Department

የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ/Konta Zone Justice Department We stand for truth and Justice⚖️

03/07/2026
በተገባደደው በጀት ዓመት ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በወንጀልና ፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነትን ለማሳደግ የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል። ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨...
02/07/2026

በተገባደደው በጀት ዓመት ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር በወንጀልና ፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነትን ለማሳደግ የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል። ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፍትህ ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የ2018ዓ/ም ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ መክሯል።

በመድረኩም የተገኙት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል በፌደራል እና በክልሉ ህገመንግስት እና በሌሎች ህጎች የተደነገጉ የግልና የቡድን መሰረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች መከበራቸውን በማረጋገጥ የህግ የበላይነት እንዲከበር በበጀት ዓመቱ ትኩረት በመስጠት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል።

ይህንን ተግባርና ኃላፊነት ከመወጣት አንጻር ከተለመደው ኃላፊነት ባሻገር 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላም የሰፈነበት ፣ዲሞክራሲ የተረጋገጠበት፣የህግ የበላይነት የተከበረበት እንዲሆን እና ምርጫው ሰላማዊ ፍትሃዊ እና ነጻ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቢሮው የጎላ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

በምርጫው ወቅት ከጸጥታ አካላት ጋር በትብብር በመስራት ከምርጫ ህግና ስነስርዓት ውጭ የሆኑ ጉዳዮችን በመቀበል የተፋጠነ ምርመራና ክስና ክርክር በማድረግ ፈጣን ውሳኔ በማሰጠት ወንጀለኞችን እስከ አንድ ዓመት እስራት ማስቀጣት ተችሏል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ የወንጀልና የፍትሐብሔር ፍትህ አስተዳደር ውጤታማነትን በማሳደግ ጥራት ያለው ህግ በማርቀቅና በማስረጽ በኩል በቅንጅት በመስራት ጥሩ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውንም ገልጸዋል።

በ2018 በጀት ዓመት በመሰረተ ማህበረሰብ ፍትህ 758 ባህላዊ ፍርድቤቶች ተቋቁመው 2424 መዝገቦችን በማየት እልባት መስጠት እንደቻሉም ኃላፊዋ አብራርተዋል ።

በተመሳሳይ በመደበኛ ተግባር በሁሉም ወንጀሎች የምርመራ መዝገቦችን የማጥራት ምጣኔ 96.6 ከመቶ፣ በሁሉም ወንጀሎች የማስቀጣት ምጣኔ 94 ከመቶ ማድረስ መቻሉንም ወ/ሮ ቤተልሔም ገልጸዋል።

በበጀት ዓመቱ በርካታ ተግባራት የተከናወኑ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ተከሳሽና ምስክር በመጥፋት የሚዘጉ መዝገቦችን ከመቀነስ አንጻር ፣ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስእና የህግ ተገዢነትን ሙሉ በሙሉ ከማረጋገጥ አንጻር በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባልም ብለዋል።

ዛሬ በሚኖረው የአፈጻጸም መድረክ የዞኖችና የክልሉ የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት ቀርቦ የተሻለ አፈጻጸሞችን የማስቀጠልና በዕጥረት የታዩትን የ2019 በጀት ዓመት የዕቅድ አካል አድርጎ ለመፈጸም ከወዲሁ ትኩረት እንዲሰጠውም ተጠይቋል።

በመድረኩ የክልሉን ፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች ጨምሮ የስድስቱም ዞን የስር መዋቅሮች ተገኝተዋል።
ዘገባው የቤንች ሸኮ ቴሌቪዥን ነው።

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠበቆች እና የህግ ጉዳይ ፀሐፊዎች ድጋፋዊ ክትትል ተደረገቀን 16/8/2018 ዓ.ም፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠ...
25/04/2026

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠበቆች እና የህግ ጉዳይ ፀሐፊዎች ድጋፋዊ ክትትል ተደረገ
ቀን 16/8/2018 ዓ.ም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የጠበቆች እና የህግ ጉዳይ ፀሐፊዎች ድጋፋዊ ክትትል ተደረገ። ድጋፋዊ ክትትሉ የተደረገው በዞኑ ውስጥ በሚገኙት ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ማለትም በአመያ እና ጪዳ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በሚገኙ የጠበቆች ቢሮዎችና የህግ ጉዳይ ፀሐፊዎች ቢሮ በመገኘት ሲሆን ድጋፋዊ ክትትሉን ያደረገው ደግሞ ከፍትህ መምሪያ የጠበቆችና ሲቪክ ማህበራት ው/ፍ/ም/ዋና ሥራ ሂደት እና ከፍትሐብሔር ጉዳዮች አሰ/ር ዋና ሥራ ሂደት የተዋቀረው የድጋፋዊ ክትትል ቡድን ነው። የድጋፍ ክትትሉ ዋና ዓላማም በዞኑ ውስጥ ያሉት ጠበቆች የአገልግሎት አሰጣጣቸው ከጠበቆች ስነ ምግባር ደንብ አንፃር የተቃኘ እንዲሆን፤ ለደንበኞቻቸው ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻልና ለፍትህ ዘርፉ አጋዥ እንዲሆኑ ለማድረግ ነው ተብሏል። በድጋፍ ክትትል ወቅትም የጠበቆች ቢሮ ለተገልጋዮች ምቹ እና በግልፅ በሚታይ ቦታ ላይ ስለመሆኑ ምልከታ የተደረገ ሲሆን ከተዘጋጀው ቼክ ሊስት መነሻ በዋናነት ስለደንበኞች ክፍያ ፍትሐዊነት፣ስለአገልግሎት ጥራት፣ስለ ጉዳይ መጓተት አላስፈላጊነት እና በጥቅሉ ስለ ስነ ምግር ጉዳዮች በማንሳት ድጋፍ ተደርጓል። ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችንም በመለየት ግብረ መልስ የሚሰጥበትም ይሆናል። የድጋፍ ክትትሉ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ይሰራልም ተብሏል።

የወንጀል ሕግ ዓላማና ግብ    መግቢያየወንጀል ሕግ መደረግ ያለባቸውንና መደረግ የሌለባቸውን ድርጊቶች በዝርዝር የሚያመለክት እና በመደረጋቸውና ባለመደረጋቸው የተነሳ በድርጊቱን ፈፃሚዎች ላይ...
22/04/2026

የወንጀል ሕግ ዓላማና ግብ
መግቢያ
የወንጀል ሕግ መደረግ ያለባቸውንና መደረግ የሌለባቸውን ድርጊቶች በዝርዝር የሚያመለክት እና በመደረጋቸውና ባለመደረጋቸው የተነሳ በድርጊቱን ፈፃሚዎች ላይ የሚጣለውን የቅጣት መጠን የሚወስን ሕግ ነው። የወንጀል ሕጉ ይህ ሲያደርግ የራሱ ዓላማና ግብ ያለው ሲሆን ይህ ጽሑፍም የወንጀል ሕጉን ዓላማ እና ግብ በአጭሩ የሚዳሰስ ይሆናል።

የወንጀል ሕግ ዓላማ
ወንጀል የአገርንና የጠቅላላውን ማሕበረሰብ ጥቅም የሚጎዳ ተግባር ነው፡፡ በዚሁ መነሻነትም የወንጀል ሕጋችንን ዓላማ ለጠቅላላው ጥቅም ሲባል የአገሪቱን መንግሥት፣ የህዝቦቹን፣ የነዋሪዎቹን ሰላም፣ ደህንነት፣ ሥርዓት፣ መብትና ጥቅም መጠበቅና ማረጋገጥ እንደሆነ በሕጉ አንቀጽ 1 ተመልክቷል፡፡ ይህም ሲባልም የአገሪቱን ሉአላዊነት፣ አጠቃላይ ሰላምና ደህንነት፣ የመንግሥትና የሕዝብን ደህንነትን እንዲሁም አንድ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም የጠቅላላው ኅብረተሰብ ጥቅም የሚጎዳ ከመሆኑ አንፃር የዜጎችን ግለሰባዊ መብትና ደህንነት ማስጠበቅን የሚያካትት ነው፡፡

የወንጀል ሕግ ግብ
የወንጀል ሕጉ የተጠቀሰውን ዓላማ ለማሳካት የሚያስችሉትን ግቦችም ያካተተ ነው፡፡ የወንጀል ሕጉ ዋነኛ ግብ ወንጀል እንዳይፈፀም መከላከል እንደሆነ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 1 ተደንግጓል፡፡ ይህንን ግብ ለማሳከትም የወንጀል ሕጉ ወንጀሎችንና ቅጣታቸውን በቅድሚያ በመደንገግ ሰዎች ድርጊቶቹን ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡፡

ሆኖም ማስጠንቀቂያ ብቻውን በቂ ላይሆን የሚችልበት ሁኔታ መግጠሙ የነበራዊው ዓለም ሐቅ ነው፡፡ ሕጉ ይህን ታሳቢ በማድረግ ማስጠንቀቂውን በመተላለፍ ወንጀል የሚፈፅሙ አጥፊዎች ሕጉ ባስቀመጠው መሠረት በጥፋታቸው ልክ ተቀጥተው ሌላ ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እና ሌሎችም ከዚህ በመማር ከወንጀል እንዲታቀቡ በማድረግ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ መከላከል ሌላኛው የወንጀል ሕጉ ግብ መሆኑን ከሕጉ አንቀጽ 1 መረዳት ይቻላል፡፡ ይህ ማለት ወንጀል ፈፃሚዎችን መቅጣት አንድም ወንጀል ፈፃሚዎች በሚጣልባቸው ቅጣት ታርመው/ተምረው/ በሚወጡበት ጊዜ ተመልሰው ወደ ሌላ ወንጀል ተግባር እንዳይገቡ የማድረግ ሚና የሚኖረው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ሰዎች ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ማስተማሪያ ይሆናል።

ማጠቃለያ
ወንጀል የጠቅላላውን ማኅበረሰብ ብሎም የአገርን ሰላምና ደህንነት የሚጎዳ ተግባር በመሆኑ በአገራችን ወንጀልን መከላከል፣ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ወንጀል ተፈፅሞ ሲገኝም አጥፊዎችን ማረም ብሎም ሌሎችን ማስተማር ዓላማ እና ግብ ያለው የወንጀል ሕግ በሥራ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል የሕጉን ዓላማ እና ግብ በመገንዘብ ለሕጉ ዓላማ እና ግብ መሳካት የራሱን አስተዋፅኦ ማበርከት ይኖርበታል።

ከፍትሕ ሚኒስቴር fb ገጽ የተወሰደ

02/04/2026

ከ60 ዓመታት በላይ ያገለገለውን የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ የሚተካ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1410/2018 ሆኖ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ!
**************************
የ1954 የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕጉ ለበርካታ አሥርት ዓመታት በሥራ ላይ የቆየ በመሆኑ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ በ1997 ከወጣው የወንጀል ሕግ፣ ሀገራችን ከምትተገብረው የወንጀል ፍትሕ ፖሊሲ እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በዘርፉ ካሉ አዳዲስ አሠራሮችና የቴክኖሎጂ እድገቶች አኳያ ከዘመኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ መከለሱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ባለፉት ዓመታት የአዲስ ሕግ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። ዛሬ የጸደቀው የሕግ መድብል አዳዲስ አሠራሮችን ከማስተዋወቁ በተጨማሪ የማስረጃ ሕግ በማካተት በኢትዮጵያ የወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የቆየውን አንድ ትልቅ ክፍተት ለመሙላት አስችሏል። ሕጉ የወንጀል ምርመራ፣ ክስና ማስረጃ ሥርዓቱን ወደአዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው።

የወንጀል ሥነ ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በማርቀቅ ሂደት ከ15 ዓመታት በላይ የወሰደ ሲሆን ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከተለዩ ቁልፍ የሕግ ሪፎርሞች አንዱ ሆኖ፣ ብዙ ምክክር ተደርጎበት ሊጸድቅ ችሏል። ሕጉ ሀገር አቀፍ ተፈጻሚነት ያለው ሲሆን ከዚህ ሪፎርም የሚጠበቀውን ውጤት እውን ለማድረግ የፍትሕ ሚኒስቴር በሁሉም ደረጃ ከሚገኙ የፍትሕ አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል።

የፍትሕ ሚኒስቴርን የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆችን እና ድረ-ገፅን ይቀላቀሉ
Website
https://www.justice.gov.et
Facebook
https://www.facebook.com/MOJEthiopia/
(x) Twitter
https://x.com/MOJEthiopia
YouTube channel
https://youtube.com/...3701...
Telegram
https://t.me/fdreattorneyGeneral_external

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የኤች አይቪ/ኤድስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ።   መጋቢት 23/2018 ዓ.ም ኮንታ_አመያየግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው ለአጠቃላይ የመምሪያው ሠራተኞች ሲሆ...
01/04/2026

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የኤች አይቪ/ኤድስ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ።
መጋቢት 23/2018 ዓ.ም ኮንታ_አመያ
የግንዛቤ ማስጨበጫው የተሰጠው ለአጠቃላይ የመምሪያው ሠራተኞች ሲሆን በአቅራቢያ የሚገኙ የሌላ መ/ቤት ሠራተኞችም እንዲሳተፉ መደረጉም ተገልጿል።
በመድረኩ ላይ የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ተፈራ የተገኙ ሲሆን የመምሪያው ኃላፊ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሰለ ኤች አይ ቪ አስከፊነት፣ መከላከልና ተጎጂዎችን መርዳት በተመለከተ የሚሰጠው ትኩረት ከጊዜ ወደጊዜ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ገልፀው በዚህም ምክንያት የቫይረሱ ስርጭት እየጨመረ የመጣ በመሆኑ ሁሉም ሰው ቫይረሱን ከመከላከልና ተጎጂ ዜጎችን ከመደገፍ አንፃር የድርሻውን መወጣት አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
ስልጠናውን የሰጡት የጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ስለ ቫይረሱ ምንነት፣ስለመተላለፊያ መንገዶችና ስለመከላከያ መንገዶች እንዲሁም ስለአጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታዎች በዝርዝር አቅርበው ግንዛቤ አስጨብጠዋል። በውይይቱም የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርበው መልስ ተሰጥቶባቸዋል።

የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ተዓማኒነት ያለው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጥ አገልግሎት በወረዳና ከተማ ...
27/03/2026

የፍትህ አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ተደራሽና ተዓማኒነት ያለው ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ የሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጥ አገልግሎት በወረዳና ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ላይ ለማስጀመር የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል።

የስልጠና መድረኩን የመሩት የዞኑ ም/አስተዳዳሪና ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወጁ እንደገለፁት የሰነዶችን ምዝገባና ማረጋገጥ አገልግሎት አሰጣጥ በቅንጅትና በባለቤትነት ስሜት መምራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ተግባሩ እጅግ ወሳኝ እንደመሆኑ መጠን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩረት ሊሰሩ ይገባል ያሉት አቶ ወንድማገኝ ተቋማት ተናበው በመሥራት የህብረተሰቡን መብትና ጥቅም ማረጋገጥ ላይ አጽንኦት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የስልጠናውን ሰነድ ያቀረቡት የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ተፈራ በበኩላቸው በፍትህ ተቋም ከሚሰጡ መጠነ ሰፊ አገ/ቶች ውስጥ አንዱ የሰነድ ምዝገባና ማረጋገጥ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው አያይዘውም አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም በዞን ደረጃ ብቻ የተወሰነ በመሆኑ ሩቅ አካባቢ ያሉ የተለያዩ የህ/ሰብ ክፍሎች ሲቸገሩ መቆየታቸውን አውስተው አሁን ላይ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ የሰነድ ምዝገባና ማረጋገጥ አገልግሎት መመሪያ ቁጥር 33/2018 እንዲወጣ ማድረጉን ተከትሎ ህ/ሰቡ በያለበት መዋቅር አገልግሎቱን በቅርበት እንዲያገኝ የሚያስችል ዕድል መፈጠሩን ገልፀዋል።

አያይዘውም የሰነድ ምዝገባና ማረጋገጥ ሥራ በዋናነት በዜጎች ሀብትና ንብረት ባለቤትነት ላይ ዋስትና የሚሰጥ ጉዳይ በመሆኑ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

መመሪያው ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ተዓማኒነት ያለው አገ/ት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ግልጽ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረው በትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ባለድርሻ አካላት ተናበው መስራት አለባቸው ብለዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ለወደፊት ስራቸው አቅም የሚፈጥር ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀው ተግባሩን ውጤታማ ለማድረግ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጠናከር፣ የግብዓትና የሰው ኃይል እጥረት ችግሮችን መቅረፍ እና ችግር ፈቺ የሆነ ድጋፍና ክትትል ማጠናከር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በስልጠናው መድረክ ላይ የዞኑ ም/ል አስተዳዳሪና የገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወጁ፣ የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ተፈራን ጨምሮ የ5ቱም መዋቅሮች የፍትህ እና የገቢ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዞንና የወረዳ አቃቤያን ህጎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዘገባው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው!

ማስታወቂያ ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ለህግ ባለሙያዎች👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
30/01/2026

ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ ለህግ ባለሙያዎች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ ድጋፋዊ ክትትል ተደረገ።  22/5/2018 ዓ.ም ኮንታ-አመያ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የ2018ዓ/ም ግማሽ አመት አፈጻጸም በተመለከተ የተ...
30/01/2026

በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ ድጋፋዊ ክትትል ተደረገ።
22/5/2018 ዓ.ም ኮንታ-አመያ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የ2018ዓ/ም ግማሽ አመት አፈጻጸም በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራት ላይ ያተኮረ ድጋፋዊ ክትትል በኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ ተደርጓል።
የድጋፍ ክትትል ያደረጉት የኮንታ ዞን ፐ/ሰ/ሰ/ሀ/ል/መምሪያ የመ/አስ/ር ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ታገል እሸቱ እና የሪፎርም ጉዳዮች ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት ገብሬ በተዘጋጀው ቼክ-ሊስት መሰረት የተቋሙን አፈፃፀም የገመገሙ ሲሆን ከተነሱት አንኳር ነጥቦች መካከልም ተቋማዊ ዕቅድና አፈጻጸም፣ የመልካም አስ/ር ዕቅድ አፈፃፀም፣ የቲም ውይይት፣ የዜጎች ቻርተር፣ ፈጣን ለውጥ ማምጫ መሳሪያዎች፣ ቅሬታ አፈታት፣ ፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ቅንጅታዊ አሰራር፣ የሰራተኛ ጥቅም፣ የጡረታ መረጃ ጉዳዮች ተነስተው በሰፊው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ተፈራ ተቋሙ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ መሆኑን ገልፀው የተለያዩ መረጃዎችንና ሰነዶችን በማቅረብ አፈፃፀሙን አብራርተዋል።
የማኔጅመንት አካላትም በየሥራ ሂደታቸው የተሰሩትን ሥራዎች በሚገባ ገለፃ አድርገዋል።
የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ታገል እሸቱ እንደገለፁት ተቋሙ ከላይ ከተነሱት ነጥቦች አንፃር በጣም ጥሩ በሚባል ደረጃ ያለ መሆኑን ገልፀው እነዚህን መልካም ነገሮችን አጠናክሮ እንዲቀጥል እና በጉድለት የተነሱ ጉዳዮችን የዕቅድ አካል በማድረግ መሥራት እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይቱ ተጠናቋል።

ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓል በኮንታ ዞን ፍትሕ መምሪያ ተከበረ።17/03/2018 ዓ.ም ኮንታ አመያ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስ...
27/11/2025

ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓል በኮንታ ዞን ፍትሕ መምሪያ ተከበረ።
17/03/2018 ዓ.ም ኮንታ አመያ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀን በዓል "ትውልድን በስነ-ምግባር፣ተቋምን በአሰራር" በሚል መሪ ቃል በኮንታ ዞን ፍትሕ መምሪያ ተከብሯል።
በዓሉን የ3(ሦስት) ተቋማት ሠራተኞች በጋራ በመሆን ያከበሩ ሲሆን እነዚህም የዞኑ ፍትሕ መምሪያ፣ የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የዞን ሠላም፣ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ መሆናቸው ታውቋል።
በዕለቱ በዓሉን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዞን ሠላም፣ፀጥታና ሚሊሻ መምሪያ ተወካይ የሆኑት አቶ አያሌው ከበደ በንግግራቸው ሙስና የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ በእጅጉ የሚጎዳ እና የትውልድ ገዳይ በመሆኑ ሁሉም ሠራተኛ አምርሮ ሊታገለው ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በዕለቱ በዓሉን በማስመልከት የመወያያ ሰነድ የዞን ፍትህ መምሪያ ተወካይ በሆኑት አቶ ሀብታሙ ሀደሮ የቀረበ ሲሆን በሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጓል።
በዕለቱም በዓሉን አስመልክቶ የተዘጋጀ ግጥም እና አስተማሪ ታሪኮችም ለተሳታፊዎች ቀርበዋል።
ውይይቱንም የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ዘላለም ግዛው ከሌሎች የመምሪያዎች ተወካዮች ጋር በጋራ የመሩ ሲሆን ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።
ዘገባው የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ ነው።

Address

Konta Zone
Ameya

Telephone

+251472270002

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኮንታ ዞን ፍትህ መምሪያ/Konta Zone Justice Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share