የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት //Konta Zone Youth Wing Branch office

  • Home
  • Ethiopia
  • Ameya
  • የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት //Konta Zone Youth Wing Branch office

የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት //Konta Zone Youth Wing Branch office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት //Konta Zone Youth Wing Branch office, Political organisation, Southwest Ethiopia Peoples Regional State, Ameya.

‎በጪዳ ከተማ አስተዳደር ከጫ ቀበሌ 7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ይምረጡኝ ቅስቀሳ እና የቡና ጠጡ ፕሮግራም ተደርጓል።‎‎በመርሃግብሩ ተገኝተው ለወጣቶች መል...
20/05/2026

‎በጪዳ ከተማ አስተዳደር ከጫ ቀበሌ 7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ይምረጡኝ ቅስቀሳ እና የቡና ጠጡ ፕሮግራም ተደርጓል።

‎በመርሃግብሩ ተገኝተው ለወጣቶች መልዕክት ያስተላለፉት የጪዳ ከተማ አስ/ር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ካንሳ የተሻለችና የበለጸገች ኢትዮጵያን ማየት የሚፈልግ ሁሉ ምርጫውን ብልጽግና ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል።

‎የተጀመሩ ልማቶች ወደ ግብ እንድደርስ ወጣቱ ትውልድ የብልጽግና ፓርቲን መምረጥ እንዳለበት ያሳሰቡት የፓርቲው ኃላፊ ወጣቶች መምረጥ ብቻ ሳይሆን ከማስመረጥ ረገድም ድርሻ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

‎ወጣቱ የአከባቢውን ሰላምና ፀጥታ ከማስከበር አኳያም ከፍተኛ ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አቶ ደምሴ አክለው ገልጸዋል።

‎የቀበሌ ወጣቶችም ፓርቲው በርካታ ራዕይ ያለው በመሆኑ ነገ ላይ የተሻለችውን ኢትዮጵያን ለማየት ምርጫችን ብልጽግና ነው ሲሉ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን አጋርነት በግልጽ አሳይተዋል።

‎በመድረኩም የከተማ አስ/ር ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ካንሳ፣የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ብራሞ በቀለ እና ሌሎችም ደጋፍ አመራርና የቀበሌ ወጣቶች ተገኝተዋል።
‎ዘገባው፦ብልጽግና ፓርቲ የጪዳ ቅ/ጽ/ቤት ነው።

ለሀገረ መንግስት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።በኮንታ ዞን በአመያ ዙሪያ ወረዳ "የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ ምርጫ" በሚል መሪ ቃል 7ተኛዉን ሃገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከመዲ ...
20/05/2026

ለሀገረ መንግስት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።

በኮንታ ዞን በአመያ ዙሪያ ወረዳ "የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ ምርጫ" በሚል መሪ ቃል 7ተኛዉን ሃገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከመዲ ጎተራ ቀበሌ ወጣቶች ጋር የምርጫ ቅስቀሳ እና ዉይይት መድረክ ተካሂደዋል።

በውይይት መድረክ ላይ የተገኙ የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሻግሬ አለማየሁ የብልጽግና ፓርቲ እንደ ኮንታ ዞን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እንዳከናወነ ገልፀው የወጣቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እስከታችኛው ቀጠና ድረስ በመውረድ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።

የኮንታ ዞን ፐ/ሰ/ሰ/ሀ መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ ይልማ ለሀገረ መንግስት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተው በቀበሌው የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በቀጣይም አጠናክሮ ለማስቀጠል የመዲ ወጣቶች የዘንድሮው ምርጫ በፍትሃዊነት፣ በስሌትና በሰላም እንዲጠናቀቅ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የወረዳው ሥራ ክሂሎት እና ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሣሁን ዳዕሞ እንደገለፁት በወረዳ መንግስት ለሁሉም ቀበሌዎች የሚወርደው በጀትም ሆነ ተግባር እኩል እንደሆነ አብራርተው ወጣቶች በተለያዩ ስራ ዕድል ተጠቃሚ እንድሆኑ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በውይይት መድረክ ላይ ከቀበሌው ወጣቶች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስትያየቶች የተነሱ ሲሆን ለተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የወረዳው ብልጽግና ፓርት ቅ/ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ የዞኑና የወረዳ ድጋፍ ሰጪ አመራሮች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ውይይቱ
ተጠናቅቋል።

ዘገባዉ:- የኮንታ ዞን የአመያ ዙሪያ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው::

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!''በሚል መሪ ቃል በኦፓ ላሼ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የይምርጡኝ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ በአመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓ ላሼ ቀበሌ "ኢትዮጽያን...
15/05/2026

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!''በሚል መሪ ቃል በኦፓ ላሼ ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የይምርጡኝ ቅስቀሳና ድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

በአመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓ ላሼ ቀበሌ "ኢትዮጽያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!"በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ አባል ወጣቶች የይምረጡኝ ቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በቅስቀሳው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አሻግሬ አለማየሁ ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶችን ዘላቂ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ እንደሆነ በመናገር ወጣቶች ከብልጽግና ፓርቲ ጎን በመቆም የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ሊያፋጥኑ ይገባል ጥሪ አቅርበዋል።

ወጣቶች በሀገር እድገትና ለውጥ ያላቸው አስተዋጽኦ የጎላ እንደሆነ ያወሱት ኃላፊው ብልጽግና ፓርቲም ይህንን በመገንዘብ ለወጣቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት ወጣቶችን አምራች ዜጋ የሚያደርጉ የተለያዩ አማራጮችን በመዘርጋት እና በማደራጀት እያሰማራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

በማከለም አቶ አሻግሬ መጪው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የራሳቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱም ጥሪ አቅርበዋል።

የወጣቶች ክንፍ ኃላፍ ወጣት ሀብታሙ ነገሮ ብልጽግና ፓርቲን መምረጥ የተጀመሩ እንሸትቮችን ማስቀጠል እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስለሆነ ሁሉም ወጣት በአደረጃጀት ወጥተው ድምፅ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በይምረጡኝ ቅስቀሳ እና ድጋፍ ሰልፉ ላይ የዞንና የወረዳው ከፍተኛ አመራሮችም ተገኝተውበታል።

ዘገባው የአመያ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ነው

‎የኢትዮጵያ ብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ  ተገለጸ‎‎በኮንታ ዞን ጪዳ ከተማ አስተዳደር 7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ "የወጣቶች ተሳትፎ፥ ለሰላማዊ ...
13/05/2026

‎የኢትዮጵያ ብልፅግና ጉዞ እውን እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተገለጸ

‎በኮንታ ዞን ጪዳ ከተማ አስተዳደር 7ኛ ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫን አስመልክቶ "የወጣቶች ተሳትፎ፥ ለሰላማዊ ምርጫ" በሚል መሪ ሀሳብ ከከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባል ወጣቶች ጋር ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

‎የወጣቶች መድረክን ያጠቃለሉት የጪዳ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳምሴ ካንሳ ወጣቱ ትውልድ የለውጡ ሞተርና የሀገር ግንባታ ዋነኛ መሳሪያ መሆናቸውን ጠቁመው ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸው ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ድሎች ላይ የወጣቶች ተጠቃሚነት እየተረጋገጠ መጥቷል ብለዋል።

‎አክለውም አቶ ደምሴ ለወጣቱ ትውልድ አዳዲስ ተስፋዎችን የፈጠሩ ታሪካዊ ስራዎች የተሰሩ
‎መሆናቸውን አስረድተው እነዚህ የተጀመሩ የልማትና የለውጥ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ወጣቱ ብልፅግናን እንዲመርጥና እንዲያስመርጥ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የጪዳ ከተማ አስ/ር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ብራሞ በቀለ በበኩላቸው የተሻለች ኢትዮጵያን ለመረከብና ለቀጣይ ትውልድም ለማሸጋገር ወጣቱ ትውልድ ምርጫውን ብልጽግና ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

‎ወጣቶች መምረጥ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ግንዛቤ ከመፍጠር ረገድም ድምጻቸውን ለብልጽግና እንዲሰጡ በሚገባ መቀስቀስ እንዳለባቸው አሳስበው ምርጫውም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

‎የተጀመሩ ልማቶች እንዲጠናቀቅ፣ያልተጀመረውም እንዲጀመርና የተሻለች ኢትዮጵያን ለማየት ምርጫችን ብልጽግና ነው ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
‎ዘገባው፦ የጪዳ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።

13/05/2026
‎በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሸጋገር እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ በጽኑ ያምናል፦ አቶ ደምሴ ካንሳ‎‎በኮንታ ዞን ጪዳ ከተማ አስተዳደር "የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ...
13/05/2026

‎በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሸጋገር እንደሚቻል ብልጽግና ፓርቲ በጽኑ ያምናል፦ አቶ ደምሴ ካንሳ

‎በኮንታ ዞን ጪዳ ከተማ አስተዳደር "የወጣቶች ተሳትፎ ለሰላማዊ ምርጫ" በሚል መሪ ቃል ከከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አባል ወጣቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጪዳ ከተማ አስ/ር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደምሴ ካንሳ በሀገራችን ኢትዮጵያ ባሉት ህዝቦች ከግማሽ በላይ ወጣት መሆኑን ጠቅሰው በላቀ የወጣቶች ተሳትፎ የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ማድረግና ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ማሸጋገር እንደሚቻል በጽኑ ያምናል ብለዋል።

‎ከዚህም ረገድ እንደሀገር ለወጣቶች የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎የጪዳ ከተማ አስ/ር ብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ብራሞ በቀለ ሀገራችን ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት የሚታካሂደው ምርጫ ሰላማዊ ምርጫ እንዲሆን የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው መንግስት ምርጫውን ሰላማዊ፣ፍትሃዊ፣ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች የድርሻቸውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

‎የወጣቶች መድረክ በተለያዩ ክዋኔዎች ደምቆ ቀጥሏል።
‎ዘገባው፦ብልጽግና ፓርቲ የጪዳ ቅ/ጽ/ቤት ነው።
‎በተለያዩ አማራጮች ይከታተሉን👇👇👇
‎👉የፌስቡክ ገጻችንhttps://www.facebook.com/profile.php?id=61580278634827
‎👉በዋትስአፕ ገጻችንhttps://chat.whatsapp.com/ በመከታተል ይወዳጁን!!
‎ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!

የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ እንዴት ምልክት ማድረግ ይችላሉ?  National Election board
12/05/2026

የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ እንዴት ምልክት ማድረግ ይችላሉ?
National Election board

19/04/2026

የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የኢትዮጵያዊነት ክብራችንን ታሪካችንን እና ስማችንን በዓለም ከፍ ያደረገ እንጂ ያኮሰሰ አይደለም::

እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር የተለያዩ ሀገራት ልኡካንን ተቀብለን የክብር አበባ ጉንጉን እንዲያሳርፉ የሚያስችል አንድ ምቹ ዘመኑንና የድል ታሪካችንን የሚመጥን ስፍራ የሌለን ሀገር መሆናችንን ያስቀረ አኩሪ አሻራ ነው።

አድዋ ሙዚየም የመላው የኢትዮጵያዊያን ድል እንዲሁም የመላው አለም የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆነውን ድል ማሳያ ለጀግኖች አባቶች ህያው መታሰቢያ ያበጀና የየትኛውም ዓለም ልዑክና መሪ ወደ መዲናችን ሲገቡ ለድል ታሪካችን ክብርና እውቅና በሚመጥነው ልክ እንዲሰጡ ያስቻለና የሚያስችል አሻራ ነው።

እንዲሁም ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነትና የወል ትርክት ግንባታ ለቀጣዩ ትውልድ በክብርና በኩራት ሚተላለፍ ውድ የኢትዮጵያዊያን አንጡራ ሀብታችን ነው።

Address

Southwest Ethiopia Peoples Regional State
Ameya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኮንታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት //Konta Zone Youth Wing Branch office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share