Arbaminch Zuria Woreda Women & Social Affairs Office

Arbaminch  Zuria Woreda Women & Social Affairs Office This page is the media center of Arbaminch Zuria woreda Women and Social Affairs Office

11/07/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Eyob Boda, Ras Teferi Tek

07/07/2026
የCRC የባለድርሻ ተቋማት ቴክንክ ኮሚቴ ውይይት ተካህዷል፡፡የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት   በዩኒሴፍ የበጀት ድጋፍ በ2018 በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት በ...
03/07/2026

የCRC የባለድርሻ ተቋማት ቴክንክ ኮሚቴ ውይይት ተካህዷል፡፡
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በዩኒሴፍ የበጀት ድጋፍ በ2018 በጀት ዓመት የሶስተኛ ሩብ ዓመት በህፃናት ላይ በሚደርሱ የተለያዩ ጥቆቶችን በጋራ ከመከላከል አንፃር የባለድርሻ ተቋማት ሚና እና ጉዳይ አያያዝ ዙሪያ በሴቶችና ህፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ ሰነድ ቀርቦ በስፋት ውይይት ተደርጎ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የአፍርካ ህፃናት ቀን በዓል በድምቀት ተከብሯል።የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የአፍርካ ህፃናት ቀን በዓል ማጠቃለያ መደረክ በወረዳ ደርጃ በ...
30/06/2026

የአፍርካ ህፃናት ቀን በዓል በድምቀት ተከብሯል።
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የአፍርካ ህፃናት ቀን በዓል ማጠቃለያ መደረክ በወረዳ ደርጃ በድምቀት ተከብሯል። በአፍርካ ደረጃ ለ 36 ሀገራችን ኢትዮጵያ ደረጃ ለ35 ጊዜ በቀበሌያት በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሲከበር የቆየው የዘንድሮ የአፍርካ ህፃናት ቀን በዓል ማጠቃለያ መደረክ በወረዳ ደረጃ ተከብሮ ውሏል።
ዕለቱን አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ዝዋይ ደለለኝ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢና ተተኪ ተውልድ በመሆናቸው ልዩ ጥበቃና ክትትል ልደረግላቸው እንደምገባ አሳስበዋል። ኃላፊዋ አክለውም በህፃናት ላይ የሚደርሱ የተለያዩ ጥቃቶችን መከላከል የሁሉም ባለደርሻ አካላትና የህብረተሰቡ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰዋል በተጨማም ለተጋላጭ እና አካል ጉዳተኛ ህፃናት ምቹ ሁኔታዎች መፈጠር እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤና የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት አቶ አያለው አልታዬ ዕለቱን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር የአፍርካ መሪዎች ተሰብስበው ባወጡት የአፍርካ ህፃናት ቻርተር መሰረት ለህፃናት ትኩሬት ተሰጥቶ ኢየተሰራ መሆኑንና ሀገራችንም የነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናትን ከተለያዩ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ጥቃቶችና አደጋዎች የመጠበቅ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ መሆኑን ገልፀዋል።
በዓሉን አስመልክቶ የተቋሙ ሴቶችንና ህፃናት መብት ደህንነት ማስጠበቅ ቡድን መሪ በሆኑት በአቶ ኩራባቸው ካቻራ ሰነድ ቀርቦ በስፋት ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ተርሶ በዓሉ ተጠናቋል።
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት
ሰኔ 2018 ዓ.ም አርባ ምንጭ

አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከብሮ ዋለ።የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት "አ...
25/06/2026

አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል የአካል ጉዳተኞች ቀን ተከብሮ ዋለ።
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት "አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብ መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል በአለም ለ34ኛ በኢትዮጵያ ለ33ኛ በወረዳ ደግሞ ለ5ኛ ጊዜ የአካል ጉዳተኞችን ቀን ተከብሮ ውሏል።
በመድረኩ ላይ ወ/ሮ ዝዋይ ደለለኝ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ የመክፈቻ ንግግር በማድረግና በወረዳው የሚገኙ አካል ጉዳተኞች የአካል ጉዳት ከሌለባቸው በላይ መስራት እንደሚችሉ እና በወረዳው የተለያዩ የአመራርነት ሚና ላይ ሊሳተፉ እንደሚችሉ ይህንንም ለማድረግ ሁላችንም የበኩላችንን መወጣት እንደሚቻል ገልጸዋል።
ሌላው በወረዳው ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የማህበራዊ ደህንነት ጥበቃ ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሪት ኢየሩሳሌም ወርቁ ስለአካል ጉዳተኞች የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የተለያዩ ስለአካል ጉዳተኞች የተደነገጉ መመሪያዎችን የያዘ ሰነድ እና በወረዳው ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት የተደረጉ የተለያዩ ድጋፎችን፣ስልጠናዎችን በማሳየት አቅርበዋል።
እንዲሁም በጽ/ቤቱ የማህበራዊ ችግሮችን መከላከል ቡድን መሪ አቶ ስንታየሁ ምትኩ ተቋማትን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ማድረግ እና አካቶ ትግበራን በተመለከተ እንዲሁም በወረዳዎችና በቀበሌያት የሚገነቡ ተቋማት በአጠቃላይ አካል ጉዳተኞችን ያገናዘበ በሆነ መልኩ መገንባት እንዳለበትና ዛሬ ሙሉ አካል የሆነ ሰው ነገ የአካል ጉዳት ሊገጥመው ይችላልና ተቋሟትን ስንገነባ ለራሳችን እንደምንገነባ መገንዘብ እንዳለብን በመግለጽ ስልጠና ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ኃላፊ ከታዳሚው ጋር ውይይት በማድረግ የተለያዩ ጥያቄዎች የተነሱት በግልጽ በማብራራት በቀጣይ ከዚህ ቀደም ከተሰራው በላይ ለመስራት ቃል በመግባት ዕለቱን አስመልክቶ የተደረገው ውይይት ተጠናቋል።
በፕሮግራሙ ላይም በወረዳው ከሚገኙ የአካል ጉዳተኛ ማህበረሰብ የተወጣጡ ተወካዮች እንዲሁም የዞኑ የአካል ጉዳተኞች ሰብሳቢ ተሳታፊ ሆነዋል።

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የህፃናት "ፓርላማ" ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ።በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ህፃናት ፓርላማ ምክር ቤት ዋና አፈ_ጉ...
26/04/2026

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የህፃናት "ፓርላማ" ምክር ቤት 4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሄደ።

በዕለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የወረዳው ህፃናት ፓርላማ ምክር ቤት ዋና አፈ_ጉባኤ ህፃን እሱባለው መብራቱ ህፃናት ማለት የዛሬ አበባዎች የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች መሆናቸውን መንግስ በአመቻቸላቸው የተለያዩ የተሳትፎ መድረኮች በንቃት በመሳተፍ አቅማቸውንና አስተሳሰባቸውን ሚሊዮን ሊገነቡ እንደሚገባ አሳስበዋል ።
በተጨማሪም ወ/ሮ ዝዋይ ደለለኝ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በጉባኤው ማስጀመሪያ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋማቸው የህፃናት መብት፣ደህንነት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆን ተናግረዋል።

ከዚህም መነሻ መንግስት ለህፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት የተለያዩ ፖሊሲዎችን ቀርፆ እየሰራ እንደሚገኝ ወ/ሮ ዝዋይ ጠቁመው የህፃናት በተለያዩ መድረኮች ተሳታፊ እና ተጠቃሚ መሆን ይችሉ ዘንድ በወረዳው ተቋቁሞ በተግባር ላይ የሚገኘው የህፃናት ፓርላማ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የወረዳው ህፃናት ፓርላማ ምክር ቤት ተወካዮች ለ4ኛ ዙር 10ኛ ዓመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለመሳተፍ እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ጉባኤውን አስጀምረዋል፡፡

በጉባኤ የ2018 በጀት አመት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት፣ የ2018 በጀት ዓመት የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የ2019 በጀት አመት ዕቅድ በክብርት ህፃን ቃልክዳን ውዱሜ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ህፃናት ፓርላማ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ አማካኝነት ቀርቦ በተሳታፊ አባላት ሰፊ ውይይት ውይይት ተደርጓል።

በጉባኤው አቶ ገረሱ ታቦ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት ምክትል አፈ- ጉባኤ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8)ቀንበድምቀት ተከበረ።በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶች ማህበ...
26/03/2026

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረዉ ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8)ቀን
በድምቀት ተከበረ።
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት በዓለም ለ115 ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን (ማርች ''የሴቶች ድምጽ እኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ'' በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል።
የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን (ማርች ምክንያት በማድረግ በወረዳው በሚገኙ ቀበሌያት በተለያዩ ዝግጅቶች ስከበር መሰንበቱን ወ/ሮ ዝዋይ ደለለኝ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ሴቶች ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት ተናግረዋል።
የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ( ማርች 8 ) ታሪካዊ መነሻው የሠራተኞች እንቅስቃሴ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በተመድ ዕውቅና የተሰጠው ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሆን መብቃቱን ወ/ሮ ዝዋይ አስታውሰዋል።
በመሆኑም ሴቶች ከወንዶች እኩል የመስራት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ፣ የመሰብሰብ እና የመምራት መብቶቻቸዉን ለማስከበር መደራጀትና በጋራ መስራት እንደሚገባ ወ/ሮ ዝዋይ ገልፀው ሴቶች ለራሳቸውም ይሁን ለሀገራቸው ለውጥና እድገት ተግተው መስራትም ይጠበቅባቸዋል ስሉ አሳስበዋል።
በመድረኩ የሴቶችን መብት ከማስከበር ባለፈ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ሴቶች ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በወሪት/ ቤተልሔም ይልማ የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የወረዳው ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አማካኝነት ተላልፏል።
በመድረኩ ዕለቱን አስመልክቶ ስለማርች 8 የተዘጋጀ ሰነድ በአቶ መርጊያ ማንቻ የጽ/ቤቱ ሴቶች ንቅናቄና ተሳትፎ ማስፋፊያ ባለሙያ የቀረበ ሲሆን፤ ከህግ ማዕቀፍ ተጠቃሚነት እረገድ የተዘጋጀ ሰነድም በወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት አቃቤ ህግ በሆኑት በአቶ ጎሳ ጎጆ ቀርቦ ዉይይት ተደርጓል።

Address

Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch Zuria Woreda Women & Social Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Arbaminch Zuria Woreda Women & Social Affairs Office:

Shortcuts

Share