Gamo Zone Finance and Plan Department

Gamo Zone Finance and Plan Department የሀብት ብክነትን በጋራ እንከላከል!!

26/08/2026

I got over 500 reactions on my posts last week! Thanks everyone for your support! 🎉

የጋሞ ዞን የ2019 በጀት ዓመት የመዋቅሮች በጀት ድልድል
20/08/2026

የጋሞ ዞን የ2019 በጀት ዓመት የመዋቅሮች በጀት ድልድል

19/08/2026
Bayra Boarding School
14/08/2026

Bayra Boarding School

10/08/2026
09/08/2026
በጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ግንባታ ጀመረ።‎‎ሐምሌ 26 ፣ 2018 ዓ.ም‎ ዋጫ‎...
02/08/2026

በጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር አካል የሆነውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ግንባታ ጀመረ።

‎ሐምሌ 26 ፣ 2018 ዓ.ም
‎ ዋጫ

‎መምሪያው በጋሞ ዞን ዋጫ ከተማ አስተዳደር "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪቃል የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር አካል የሆነ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ግንባታ ተጀምሯል።

‎በዋጫ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አቅመ ደካማ ለሆኑት አቶ ጊሌ ዱማሌ የመኖሪያ ቤት ግንባታ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

‎ግንባታውን ያስጀመሩት የመምሪያው ሀላፊ አቶ ያርሳ ያሜ ባደረጉት ንግግር የበጎ ፈቃድ ስራ ማህበራዊ ትስስርና አብሮነት ያጠናከረ እና የመተጋገዝ ባህላችንን የሚያዳብር ተግባር መሆኑን ጠቁመው፤ ባለፉት ዓመታት በተሰሩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች የበርካታ ነዋሪዎቻችን ህይወት ተሻሽሏል በማለት በተለይ በቤት ግንባታው ዘርፍ በተሰራ ስራ የበርካታ አቅመ ደካሞች ጎጆ በማቃናት ሸክማቸውን ማቃለል ተችሏል ብለዋል።

‎በመረሃ-ግብር ላይ የዋጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አልማዝ አባይነህ በበኩላቸው በዚሁ በጎ ተግባር ላይ የተሳተፉ ወጣቶችን አመስግነው ካለን ሀብት በማካፈል የተቸገሩትን መደገፍ፣ ጠያቂ የሌላቸውን መጠየቅ፣ የወደቁትን ማንሳት፣ የተቸገሩትን ማልበስና የተራቡትን መመገብ የሁሉም ኃላፊነት መሆን እንዳለበት ገልፀው ለሚደረገው በጎ ስራ የከተማ አስተዳደሩ እገዛ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

‎የቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሆኑት አቶ ጊሌ ዱማሌ በበኩላቸው መምሪያው በችግራችን ለመኖሪያ ቤታችን ግንባታ በበጎ ፈቃድ፣ በቅንነት ያደረገውን ድጋፍ በእጅጉ እንደሚያመሠግኑ ገልጸው በጎ ተግባር ከቤት ግንባታው በላይ ተስፋን፣ ደስታን እና መተሳሰብን የሚገነባ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

‎በግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ከዋጫ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ መስሪያ ቤቶች እና አደረጃጀቶች የተወከሉ አካላት ተገኝተዋል።

Vacancy
25/07/2026

Vacancy

Address

Arba Minch'

Telephone

+251468810007

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Finance and Plan Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gamo Zone Finance and Plan Department:

Shortcuts

Share