Gamo Zone Selamber City Adm Gov't Comm.Affairs Office

Gamo Zone Selamber City Adm Gov't Comm.Affairs Office Communication ,follow us!

ሆስፒታል ኦሞ ባንክን 2ለ1 አሸነፈ።ሠላምበር፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት) በዛሬ ከሰዓት በኋላ መርሃግብር ከ8:00 ጀምሮ ኦሞ ...
04/09/2026

ሆስፒታል ኦሞ ባንክን 2ለ1 አሸነፈ።

ሠላምበር፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

በዛሬ ከሰዓት በኋላ መርሃግብር ከ8:00 ጀምሮ ኦሞ ባንክ ከሆስፒታል ጋር ያደረጉት ጨዋታ በሆስፒታል 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

ለሆስፒታል ባህሉ በለጠ እና በቃሉ አለፈ አንድ አንድ ግብ ስያስቆጥሩ፤ ለኦሞ ባንክ ብቸኛውን ግብ ፍልሰሱ ደበበ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።

ከሆስፒታል በቃሉ አለፈ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።

ቀጥሎ ቤላ ከቃንዶሬ የማያደርጉት ጨዋታ የምጀመር ይሆናል።

ጎርማ ምንጭ ከማስታ አዲስ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ።ሠላምበር፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት) በነሐሴ 29 በጠዋ...
04/09/2026

ጎርማ ምንጭ ከማስታ አዲስ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቀቀ።

ሠላምበር፣ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

በነሐሴ 29 በጠዋት የጨዋታ መርሃግብር ጎርማ ምንጭ ከማስታ አዲስ ከተማ 1ለ1 በሆነ ውጤት ተጠናቅቋል።

በከሰዓት በኋላ መርሃግብር ኦሞ ባንክ ከሆስፒታል 7:00 እና በላ ከቃንዶሬ በ9:00 ጨዋታቸውን የምያደርጉ ይሆናል።

ማስታወቂያከዚህ በፊት በሠላምበር ከተማ አስተዳደርር ትምህርት ዩኒት በቀን 29/12/2018 ዓ/ም በትምህርት አመራር ወይም አንደኛና መካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በርዕሰ መም...
04/09/2026

ማስታወቂያ

ከዚህ በፊት በሠላምበር ከተማ አስተዳደርር ትምህርት ዩኒት በቀን 29/12/2018 ዓ/ም በትምህርት አመራር ወይም አንደኛና መካከለኛ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በርዕሰ መምህርነት፣ በም/ርዕሰ መምህርነት እና በሱፐርቫይዘርነት የጽሑፍ ፈተና እንደሚሰጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀን መግለጻችን ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይመዘገቡ የቀሩ አካላት ስለምኖሩ የመጨረሻ የመመዝገቢያ ጊዜ እስከ ጳጉሜ 02/2018 ዓ/ም ድረስ መመዝገብ የሚቻል መሆኑን እየገለጽን የጽሑፍ ፈተና የምሰጥበት ቀን ጳጉሜ 04/2018 ዓ/ም በአንላይን (በበይነመረብ) በዞን ማዕከል የሚሰጥ መሆኑን ጭምር እናሳዉቃለን፡፡

ማሳሰቢያ :- ሴት መምህራንና ርዕሰ መምህራን ወደ ትምህርት አመራርነት እንድመጡ እናበረታታለን!!

የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ትምህርት ዩኒት

የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በሶፍትዌር ሲስተም የማዘመን ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልጠና ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ይገኛል ሰላምበር ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም ...
03/09/2026

የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በሶፍትዌር ሲስተም የማዘመን ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልጠና ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ይገኛል

ሰላምበር ነሀሴ 28/2018 ዓ.ም (የሰላምበር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በሶፍትዌር ሲስተም የማዘመን ስራ ለመስራት የሚያስችል ስልጠና ለባለድርሻ አካላት እየተሰጠ ይገኛል

ከተማ አስተዳደሩ ለህብረተሰቡ የሚሰጠጡ አገልግሎቶች ቀልጣፋና የዘመነ እንዲሁም በአንድ ማዕከል እንዲሆን ከመሀመድአሚን አባቡና ጓደኞቻቸው የሶፍትዌር ዲዛይን ልማትና ትግበራ ድርጅት ጋር ውል በመግባት ወደ ሥራ መግባት የሚያስችል ስልጠና ለባለሙያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ በስልጠናው መክፈቻ ንግግር የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር ዳኜ ዳላዬ የገለፁት።

ስልጠናው መሀመድአሚን አባቡና ጓደኞቻቸው የሶፍትዌር ዲዛይን ልማትና ትግበራ ድርጅት ባለሙያዎች ለማዘጋጃ ባለሙያዎችና አመራሮች፣ ለመሬት አስተዳደር ዩኒት ባለሙያዎችና አመራሮች እንዲሁም ለገቢ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት በሰላምበር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወላድ እናቶችንና ህፃናትን ጎበኙ ሰላምበር ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (የሰላምበር ከተማ...
03/09/2026

የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት በሰላምበር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ወላድ እናቶችንና ህፃናትን ጎበኙ

ሰላምበር ፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (የሰላምበር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት)፦

በጋሞ ዞን የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ከከተማው ሴት አመራሮችና ሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀቶች ጋር በሰላምበር መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመገኘት ወላድ እናቶችንና ህፃናትን ጉብኝት ያደረጉት

ሴቶች በየጊዜው እርስበርስ የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህልን ልናጎለብት ይገባናል ያሉት የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አበበች የልኣ የሴቶች ክንፍ ከሴቶች ልማት ኅብረት ጋር በመቀናጀት ለእናቶችና ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ሴቶች በይቻላል መንፈስ በሁሉም መስክ ያላቸው ተሳትፎ የሚበረታታ ነው ያሉት የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ህዝብ ምክርቤት ዋና አፈጉባዔ ክብርት ወ/ሮ አስናቀች ጥላሁን በሰላምበር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተደረገው ድጋፍ የበጎ ተግባር አካልና ቀጣይነት ያለው ልሆን ይገባል ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ከአራቱ ቀበሌ ሴቶች ልማት ህብረት ጋር በመቀናጀት በሰላምበር የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለወላድ እናቶችና ህፃናት ለስላሳና ጁስ መጠጦች እንዲሁም የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና ድጋፍ ማድረጉን የጠቆሙት የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ንጋቷ በቀለ በተግባሩ የተሳተፉ የሁሉም ቀበሌ ሴቶችን አመስግነዋል።

ሴቶች በሆስፒታሉ ወላድ ለነበሩ ለሁሉም ሴቶች ተዘዋውረው ስጠይቁ የመመረቅ፣ በጭቅላታቸው ቅቤ የመቀባትና የታመሙ ህፃናትን የመጠቅ ተግባር በሴቶችና ጨቅላ ህፃናት ህክምና ክፍል አከናውኗል።

የከተማ አስተዳደሩ ሴት አመራሮችና የሴቶች ልማት ህብረት አባላት በሆስፒታሉ ላደረጉት አስተዋጽኦ የሆስፒታሉ ሥራአስኪያጅ አቶ ሶፎኒያስ ሶርሳ በሆስታሉ ስም አመስግነዋል።

ዞብል ማደያ ኮሌጅን 2ለ1 አሸነፈ።ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት) በነሐሴ 27 ከሰዓት በኋላ መርሃግብር ዞብል ማደያ ከኮ...
02/09/2026

ዞብል ማደያ ኮሌጅን 2ለ1 አሸነፈ።

ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

በነሐሴ 27 ከሰዓት በኋላ መርሃግብር ዞብል ማደያ ከኮሌጅ ያደረጉት ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በዞብል አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

በጠዋቱ መርሃግብር ልዩ ምንጭ ከቃንዶሬ ያደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ተጠናቅቋል።

በነገው ዕለት ሶስት ጨዋታዎች የምካሄዱ ስሆን፤ ጠዋት 2:00 አስተዳደር ከሼቶ ልማት፤ ከሰዓት በኋላ 7:00 ሎላሼ ከደሜ ሳን አንቶንዮ እና 9:00 ኦጋዴ ከሶላ ካዎ ጋሮ ጋር የምገናኙ ይሆናል።

ዞብል ማደያ ከኮሌጅ የምያደረጉት ጨዋታ እየተካሄደ ይገኛል።
02/09/2026

ዞብል ማደያ ከኮሌጅ የምያደረጉት ጨዋታ እየተካሄደ ይገኛል።

የሠላምበር ከተማ አስተዳደር “ደረሰኝ ይስጡ፤ ይቀበሉ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሕጋዊ ግብይት፣ ለጤናማ የንግድ ሥርዓት እና ለፍትሃዊ የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ መጎልበት ያለውን ጠቀሜታ  ከባለድ...
02/09/2026

የሠላምበር ከተማ አስተዳደር “ደረሰኝ ይስጡ፤ ይቀበሉ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሕጋዊ ግብይት፣ ለጤናማ የንግድ ሥርዓት እና ለፍትሃዊ የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ መጎልበት ያለውን ጠቀሜታ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

በመድረኩ የከተማው የእስካሁን ገቢ አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ተገመገመ

ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

በጋሞ ዞን የሠላምበር ከተማ አስተዳደር “ደረሰኝ ይሰጡ፤ ይቀበሉ” በሚል መሪ ሀሳብ ለሕጋዊ ግብይት፣ ለጤናማ የንግድ ሥርዓት እና ለፍትሃዊ የታክስ አወሳሰንና አሰባሰብ መጎልበት ያለውን ጠቀሜታ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

‎በውይይት መድረኩ የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ደርዛ ደምሴ እንደገለጹት ግብር ከፋዮች ለሚያከናውኑት ማንኛውም ግብይት ሕጋዊ ደረሰኝ መስጠት ግዴታ ከመሆኑ ባሻገር፣ ለፍትሐዊ የንግድ ውድድርና ለአገራዊ ልማት የሚደረግ አስተዋፅዖ መሆኑን ተረድተው ደረሰኝ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበው፣ደረሰኝ ክፍያን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ማስረጃ ከመሆኑም በላይ ግልጽነትን ለማስፈንና የግብር ገቢ በትክክል እንዲመዘገብ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

‎ህብረተሰቡም ደረሰኝ በመስጠት፣ በመቀበል እና ያለደረሰኝ ወይም በሐሰተኛ ደረሰኝ የሚካሄዱ ሕገ-ወጥ ግብይቶችን በመከላከልና በመጠቆም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግም ተጠቁሟል።

ገቢ አሰባሰባችን በታቀደው ልክ እየተሰራና እየተገመገመ እንደሚሄድ በመድረኩ ያነሱት የሰላምበር ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታምራት ባራና በቅንጅት የገቢ አሰባሰብ ሥራዎችን በመስራት የተሻለ አፈጻጸም እያስመዘገብን ልንሄድ ይገባናል ተብለዋል።

‎በየደረጃው የሚገኙ የገቢ ተቋማትም ደረሰኝ በማይሰጡ አካላት ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ በሕግ መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስዱ ተቀምጧል።

‎ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ የመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎችም የደረሰኝ አሰጣጥና አቀባበል ሥርዓትን ለማስጠበቅ ክትትሉ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አስቀምጠው፣ ቀደም ሲል ግንዛቤ ከተሰጠ በኋላ ደረሰኝ የማይቆርጡ አካላት ላይም በሕጉ መሠረት እርምጃ እንደሚወሰድ አመላክተዋል።

ገቢን ከመሰብሰብ አኳያ ያሉ ሁሉንም የገቢ አማራጮች ከተማ አስተዳደሩ ልጠቀም እንደሚገባ የጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ባለሙያዎች በመድረኩ የጠቆሙት።

‎በተጨማሪም፣ ለእያንዳንዱ ሽያጭ ተገቢው ደረሰኝ መቆረጥ እንዳለበት በመጠቆም፣ ህብረተሰቡ ደረሰኝ ሳይቀበል ክፍያ እንዳይፈጽም አስገንዝበዋል።

ገቢ ሥራዎች ውጤታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉም የዞኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ገልጸዋል።

በሠላምበር ከተማ አስተዳደር የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ...
02/09/2026

በሠላምበር ከተማ አስተዳደር የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

በሠላምበር ከተማ አስተዳደር የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዙሪያ የከተማ አስተዳደሩ አስፈፃሚ አካላት እና አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ማህበር አስተባባሪ ኮሚቴ ዶ/ር ጴጥሮስ ሰኞ ሁሉም የጋሞ ማህበረሰብ ለክለቡ ባለድርሻ መሆኑን በመረዳት ዘወትር ድጋፍ ማድረግ እንደምያስፈልግ ገልጸዋል።

የሠላምበር ከተማ አስተዳደር ዋና ከንቲባ አቶ ደርዛ ደምሴ የጋሞ ጨንቻ እግር ኳስ ክለብ የምያስፈልገውን ድጋፍ የከተማ አስተዳደሩ ህዝብ እንደምያደርግ ገልጸዋል።

አቶ ኡታ ሆሮጎ ለሠላምበር ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች የበዓል ማዕድ ለማጋራት 1,500 ብር ድጋፍ አድርገዋል። ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላም...
02/09/2026

አቶ ኡታ ሆሮጎ ለሠላምበር ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ ለአቅመ ደካሞች የበዓል ማዕድ ለማጋራት 1,500 ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ሠላምበር፣ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት)

አቶ ኡታ ሆሮጎ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባለሙያ ከሳውላ ክላስተር ላደረጉት አስተዋጽኦ የሠላምበር ከተማ አስተዳደር መንግሥት ምስጋናውን ያቀርባል።

Address

Arba Minch'

Telephone

+251910720746

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gamo Zone Selamber City Adm Gov't Comm.Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share