Department of Agriculture Gamo zone

Department of Agriculture Gamo zone ይህ የጋሞ ዞን ግብርና መምሪያ ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው። ገጹን follow, like, comment and share በማድረግ ትኩስና ወቅታዊ መረጃ ይከታተሉ።

በጋሞ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት በዋና ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር አዳነ ደስታ የወረዳችን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት  የፖለቲካና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ዋና ኃላፊ ሆነው በ...
07/09/2026

በጋሞ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት በዋና ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር አዳነ ደስታ የወረዳችን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ዋና ኃላፊ ሆነው በመሾማቸው ለተቋሙ አዲስ ዋና ኃላፊ ሆነው ለተሾሙት ለኢንጂነር ለገሰ ጮቆ የሥራ ርክብክብ ፈጽመዋል።

ዶ/ር አዳነ ደስታ፡ በተቋማችን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እያመሰገንን፣ ለላቀ የሕዝብና የመንግሥት ኃላፊነት የተመደቡ በመሆንም ውጤታማ የሥራ ጊዜ እንድሆን ከልብ እንመኛለን።

ኢንጂነር ለገሰ ጮቆ፡ ወደ ተቋማችን እንኳን በደህና መጡ እያልን፤ አዲሱ የኃላፊነት ዘመንዎ የላቀ ስኬት፣ ልማትና መልካም ውጤት የሚመዘገብበት እንዲሆንልዎ እንመኛለን!

በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ በሌማት ትሩፋት በሥጋ መንደር የደለቡ ምርጥ ሰንጋዎች ለበዓል ገበያ ቀረቡጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)​የ2019 ዓ.ም አዲሱን ዓመት እና ደ...
07/09/2026

በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ በሌማት ትሩፋት በሥጋ መንደር የደለቡ ምርጥ ሰንጋዎች ለበዓል ገበያ ቀረቡ

ጳጉሜ 2/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)

​የ2019 ዓ.ም አዲሱን ዓመት እና ደማቅ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ በጋሞ ዞን ዳራማሎ ወረዳ በሚገኙ በመነና አባያ እና ሴሎ ቀበሌዎች በሌማት ትሩፋት በሥጋ መንደር በልዩ ጥንቃቄ ያደለቧቸውን ጥራት ያላቸው ምርጥ ሰንጋዎች (የግብርና ምርቶች) ለበዓል አቅርቦት ዝግጁ ሆነዋል።

​ይህ አቅርቦት በአካባቢው በሥጋ መንደር የተደራጁ አምራቾች በቴክኖሎጂና በስነ-ምግብ ድጋፍ ያከናወኑት የግብርና ልማት ስኬት ውጤት ሲሆን ጥራት ያለው የሥጋ ከብት ምርትን በቀጥታ ከአምራቹ ለሸማቾችና ለነጋዴዎች ለማቅረብ ያለመ ነው።

በጋሞ ዞን በጋርዳ ማርታ ወረዳ በጋርሳ ጋርዳ ቀበሌ በመስኖ አማራጮች እየለማ የሚገኝ ሰብል አሁናዊ ቁመና በምስል!!
07/09/2026

በጋሞ ዞን በጋርዳ ማርታ ወረዳ በጋርሳ ጋርዳ ቀበሌ በመስኖ አማራጮች እየለማ የሚገኝ ሰብል አሁናዊ ቁመና በምስል!!


ጳጉሜ ፩ የእመርታ ቀን በጋሞ ዞን የሆርቲካልቸር ልማት ስኬት! #ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)ዛሬ ጳጉሜ ፩  የእመርታ ቀንን ስንከብር በጋሞ ዞን ብርብር ከተማ አስተ...
06/09/2026

ጳጉሜ ፩ የእመርታ ቀን በጋሞ ዞን የሆርቲካልቸር ልማት ስኬት!

#ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)

ዛሬ ጳጉሜ ፩ የእመርታ ቀንን ስንከብር በጋሞ ዞን ብርብር ከተማ አስተዳደር በአልጌ ቀበሌ የሚገኘው ሳውዝ አግሮ (South Agro) በሆርቲካልቸር ልማት ያስመዘገበው ውጤት የዞናችንን የግብርና እመርታ በተግባር የሚያሳይ ሆኗል።

​የሳውዝ አግሮ ኢንቨስትመንት እርሻ በአሁኑ ወቅት የደረሱ የአትክልት ሰብሎችን ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ አምርቶ በመሰብሰብ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ ።

ይህ የግብርና እመርታ የተመዘገበው በግብርናው ተቋም ሙያዊ ድጋፍ ታክሎበት ሲሆን ባለሙያዎች ከተከላ እስከ ድህረ-ምርት አያያዝ ያደረጉት የቅርብ ክትትልና የቴክኒክ ድጋፍ ዋና መሰረት እንደሆነ ተመላክቷል ።

​የምርቱ በዚህ ወቅት መድረስ ገበያ በማረጋጋት ትልቅ ሚና እንዳለውና ትኩስ ምርቶች ለአካባቢው ማህበረሰብ በተጣጣመ ዋጋ በመቅረባቸው የአትክልት ገበያን ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።

​የሳውዝ አግሮ የግብርና እንቅስቃሴ በዛሬው የእመርታ ቀን በዞናችን በግብርናው ዘርፍ እየታየ ያለውን ትልቅ ሽግግርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚያንጸባርቅ ህያው ማረጋገጫ ነው።

 #ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀንእመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!​ጳጉሜን የሽግግር ወርኅ ናት፤ የአሮጌው ዘመን ማብቂያ፣ የአዲሱ ተስፋ መባቻ። በዚህ የተቀደሰ የሽግግር ወቅት የመጀመሪያውን ዕለት «የ...
06/09/2026

#ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን

እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!

​ጳጉሜን የሽግግር ወርኅ ናት፤ የአሮጌው ዘመን ማብቂያ፣ የአዲሱ ተስፋ መባቻ። በዚህ የተቀደሰ የሽግግር ወቅት የመጀመሪያውን ዕለት «የእመርታ ቀን» ብለን ስንሰይመው፣ በቃላት ያሸበረቀ ድባብ ለመፍጠር ሳይሆን የሀገራችንንና የዞናችንን የነገ ጉዞ አቅጣጫ በቁርጠኝነት ለመወሰን ነው።

«እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት!» የሚለው መሪ ቃል የትውልዱ ታሪካዊ ኃላፊነት፣ የሀገራዊና ቀጣናዊ ሉዓላዊነት ማረጋገጫ፣ እንዲሁም የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት ጥሪ ነው።

​በታሪካችን ውስጥ ኢትዮጵያ የብዙ ፈተናዎችና የውጭና የውስጥ ጫናዎች ማለፊያ ሆና አልፋለች፤ ነገር ግን ውድቀቷ ፈጽሞ ዘላቂ ሆኖ አያውቅም። ዛሬ ሀገራችንም ሆነች የጋሞ ዞናችን የሚያስፈልጋቸው ቀስ በቀስ የሚመጣ ተራ ለውጥ ሳይሆን፣ በሁሉም ዘርፍ የሚታይ የጥራትና የፍጥነት እመርታ ነው።

በኢኮኖሚው ዘርፍ ከጥገኝነት ተላቆ በራስ አቅም መቆም፣ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ በቴክኖሎጂና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የዘመኑን ዕውቀት ጨብጦ ወደፊት መራመድ የዚህ እመርታ መሠረቶች ናቸው።

ይህ እመርታ ሊረጋገጥ የሚችለው ደግሞ በህዝባዊ አግልግሎት ብስለት፣ በጠንካራ ተቋማት ግንባታና በዜጎች እውነተኛ የሥራ ባህል ብቻ ነው።

​ማንሰራራት የሚጀምረው ከውስጥ አንድነትና ከጽኑ ሀገራዊና ቀጣናዊ ራእይ ነው። የእመርታ ቀን ስንል ልዩነቶቻችንን ከሀገርና ከህዝብ ህልውና በላይ ሳናስበልጥ፣ የጋራ ቤታችንን ኢትዮጵያን በጥበብና በፍትሕ ለመገንባት የምንገባው አዲስ ቃል ኪዳን ነው።

እመርታ ማለት ትላንት የሰራናቸውን ስህተቶች ደግሞ አለመስራት፣ በችግሮች ላይ ከመማረር ይልቅ መፍትሔ አመንጪ መሆን፣ እና የአገልግሎትና የአመራር ባህላችንን ከንትርክና ከሴራ ወደ ገንቢ ውይይት፣ አብሮነትና ውጤታማነት መለወጥ ማለት ነው።

​የዘመናት የታሪክ ባለቤት የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ተገባት ታላቅነትና ክብር የምትመለሰው በእያንዳንዳችን ትጋትና ቁርጠኝነት ነው። ጳጉሜን 1ን ስናከብር፣ የትላንት እጣ ፈንታችንን ቀይረን የነገዋን የበለፀገች፣ የተከበረችና ሰላሟ የተረጋገጠች ኢትዮጵያን እንዲሁም ሞዴል የሆነ የጋሞ ዞንን ለመገንባት የመጨረሻውን የኃላፊነት እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆናችንን በማረጋገጥ ነው።

​አዲሱ ዓመት የጽናት፣ የሥራ፣ የሰላምና የዓይነተኛ እመርታ ዘመን ይሁንልን!

​ዶ/ር ደምሴ አድማሱ
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ

በርካታ የታሪክ እጥፋቶች የተመዘገቡበት፤ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ከዕዳ ወደ ምንዳ በብዙ መስክ እመርታ ያስመዘገበች ኢትዮጵያ !
06/09/2026

በርካታ የታሪክ እጥፋቶች የተመዘገቡበት፤
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት
ከዕዳ ወደ ምንዳ
በብዙ መስክ እመርታ ያስመዘገበች ኢትዮጵያ !

የእመርታ ቀን! አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላ...
06/09/2026

የእመርታ ቀን!

አባቶቻችን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በደምና በአጥንታቸው አስከብረው ታላቅ ሀገር አውርሰውናል፤ ዛሬ ደግሞ እውነተኛ ሉዓላዊነትን እያረጋገጥን ያለነው ከልመናና ከጥገኝነት በተላቀቀው አዲሱና ታሪካዊው መንገዳችን ነው!

በሚሊዮን በሚቆጠር ዶላር ስንዴ ከማስገባት ተነስተን ዛሬ የአፍሪካ ቀዳሚ ስንዴ አምራች በመሆን የሚሊዮን ዶላሮችን ወጪ ማስቀረት ችለናል።

በ«ሌማት ትሩፋት» የምግብ ዋስትናን በተግባር እያረጋገጥን፣ በ«ኢትዮጵያ ታምርት» ንቅናቄም አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋትና የሥራ ዕድል በመፍጠር ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን እንገኛለን።

ከዚህ ቀደም የማይደፈሩና አይነኬ ይባልላቸው የነበሩ ከባድ የማክሮ-ኢኮኖሚ ሪፎርም ውሳኔዎችን በቁርጠኝነት በመተግበር፤ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በፅኑ መሠረት ላይ እየገነባን እንገኛለን።

እነዚህ ሁሉ ታላላቅ ድሎች ኢትዮጵያ በሚያጋጥሟት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ሸብረክ ሳትል በፅናት መጓዝ መቻሏን የሚያረጋግጡ ህያው ምስክሮች ናቸው፤ ይህ የእመርታ ጉዟችን ለመጪው ዓመት የሰነቀው ተስፋ እጅግ ግዙፍ ነው!

 #ከእልሎ መንደር ጓሮ የታየው የቀይ ሽንኩርት ምርት እመርታ!​ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)​በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ በሃማሳ ቀበሌ የሚገኘው የእልሎ መንደር ...
06/09/2026

#ከእልሎ መንደር ጓሮ የታየው የቀይ ሽንኩርት ምርት እመርታ!

​ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ጋሞ ዞን ግብርና ኮሙኒኬሽን)

​በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ በሃማሳ ቀበሌ የሚገኘው የእልሎ መንደር በገጠር ኮሪደር ልማት ፕሮግራም አማካኝነት በአጭር ጊዜ ውስጥ አስደናቂ የአትክልት ልማት እመርታ በማስመዝገብ ላይ ይገኛል።

​በዚሁ መንደር የሚኖሩ አርሶ አደሮች በጓሮአቸው ያለሙት የቀይ ሽንኩርት ሰብል በአሁኑ ወቅት ጥሩ እመርታ በማሳየቱ ለምርታማነት በቅቶ መሰብሰብ ጀምረዋል።

​ከጥቂት ጊዜያት በፊት ተጀምሮ የመንደሩን ገጽታ ሙሉ በሙሉ የለወጠው ይህ የኮሪደር ልማት ህብረተሰቡ በጓሮው የሚያመርተው ምርት የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጡ ባሻገር ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የሚያስችለውን ሰፊ እድል ፈጥሯል።

​የአካባቢው አርሶ አደሮች እንደገለጹት ለዚህ ድንቅ ሀሳብ አመንጪዎች እና ሀሳቡን በተግባር አስፈጻሚ ለሆኑ አካላት ልባዊ ምስጋናቸውን በማቅረብ የተከናወነው ታላቅ ስራ በነዋሪዎች ዘንድ ሁሌም ሲታወስ እንደሚኖር ተናግረዋል።

በእልሎ መንደር የታየው ይህ የቀይ ሽንኩርት ምርት እመርታ የገጠር ኮሪደር ልማት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምን ያህል አዎንታዊና ተጨጣጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል ማረጋገጫ ሆኗል።

05/09/2026

#ጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን!!
#እመርታ ለኢትዮጵያ ማንሰራራት

Address

Arbaminch
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Department of Agriculture Gamo zone posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share