20/08/2026
በጋሞ ዞን የሚገኙ #ወጣቶች የክረምቱን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር መነሻ በማድረግ የልማት ስራ እያከናወኑ ይገኛሉ።
በወረዳው የሚገኙ ወጣቶች በበጎ ፈቃደኝነት የወቅቱን የመኸር እርሻ በመደጋገፍ ስሜት ለአቅመ ደካማና አረጋውያን በነፃ እያረሱ ይገኛሉ።
ወጣቶቹ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ለአካባቢያቸው ልማትና ለወገኖቻቸው ደጋፊነት ማዋላቸው ትልቅ የውስጥ እርካታ እንደፈጠረላቸውም ገልጸዋል።