25/06/2026
ነፍሰጡሯ ታዳጊ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች
#ፍትህ እንሻለን ቤተሰብ 😥
በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ አንኮበር ቀበሌ ለሰሚ የሚከብድ ጆሮን ጭዉ ያስባለ አሳዛኝ ክስተት ተከስቷል።
ምስጋና ቦራና በቤት ስሟ ዲቦራ የተባለች የ14 ዓመት ታዳጊ ህፃን ሰኔ 14/2018 ዓ.ም አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በወንዝ ዳርቻ ተገድላ ተገኝታለች።
በጊዝያዊነት በግድያ ወንጀል የተጠረጠረዉ ግለሰብ ልጅቱን እንዳስረገዘ እና አገባሻለዉ በማለት ይዟት እንደሄዴ የታወቀ ሲሆን "ሰዉ ገድያለዉ" በማለት ለፖሊስ ቃል በመስጠት እጁን እንደሰጠ ሰምተናል።
በዚህም ፖሊስ የአስከሬን ምርመራ በአርባምንጭ ሆስፒታል አድርጎ ለቤተሰብ ለቀብር ስነስርዓት ካስረከበ በኋላ ለተጨማሪ ምርመራ በግድያ የተጠረጠረዉ ግለሰብ ቤተሰቦችን ፖሊስ አስሮ በሚጠይቅበት ጊዜ "ገድያለዉ" ያለዉን ቃል ቀይሮ "አልገደልኩም" በማለት ቃል በመስጠቱ ምክንያት ለተጨማሪ የአስከሬን ምርመራ ወደአዲስ አበባ መላኩንም ሰምተናል።
የ ምዕራብ ዓባያ ወረዳ እንዲሁም የሚመለከታቸዉ የፍትህ አካላት ተገቢዉን ምርመራ እና የማጣራት ስራ በመስራት ወንጀለኛዉን ተገቢዉን ፍርድ እንዲያገኝ እንዲደረግ በማለት የሟች ቤተሰብ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።