የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council

  • Home
  • Ethiopia
  • Arba Mintch
  • የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council ይህ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው።

የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የፓርቲና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሳውላ ማረሚያ ተቋም  የልማት ስራዎች ጉብኝት አደረጉ ነሐሴ 18/2018 ...
24/08/2026

የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የፓርቲና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በሳውላ ማረሚያ ተቋም የልማት ስራዎች ጉብኝት አደረጉ

ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስትና የፓርቲ የስራ ኃላፊዎች በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ጉብኝት እና የቀጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብርም አከናውነዋል።

ኃላፊዎቹ በጎፋ ዞን ሳውላ ማረሚያ ተቋም እየተከናወነ የሚገኘው የሽመና ስራዎች በመጎብኘት ላይም ይገኛሉ።

በዞኑ ሳውላ ማረሚያ ተቋም በግብርና ልማት እና በእንስሳት እርባታ ስራና በሌሎች ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በማረሚያ ተቋሙ ግብርናን ለማዘመን የተተገበሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውም በጉብኝቱ ወቅት ተጠቁሟል ።

በተጨማሪም በተቋሙ አረንጓዴ አሻራ የማኖር እና ለአረጋውያን የቤት ግንባታ ስራዎች ተከናውነዋል ።

"ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን" የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ አርባምንጭ  ነሐሴ 16፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ...
22/08/2026

"ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን" የተከበሩ አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

አርባምንጭ ነሐሴ 16፣ 2018 ዓ.ም፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ፣ የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም፣ አንድነት እና አብሮነት በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለመው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን በማስመልከት ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው፣ ይህ ጉባዔ ለነገዋ ጠንካራ ኢትዮጵያ መሠረት የተጣለበት እና የሀገራችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በጋራ የተቀረጸበት ታሪካዊ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

የዚህ የምክክር ሂደት ዋና ዓላማ በሀገራችን ለረጅም ጊዜያት የግጭት መነሻ የሆኑ መሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በውይይት መፍታት መሆኑን ያነሡት አቶ ታገሰ፣ ምክክሩ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው አካታች እና አጠቃላይ ሀገራዊ መድረክ መሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው አስረድተዋል።

የምክክር ሂደቱ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወጣው አዋጅ ቁጥር 1265/2014 መሠረት ራሱን የቻለ እና ገለልተኛ የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካይነት በሕጋዊ ሥርዓት መመራቱን አፈ-ጉባኤው አስታውሰዋል።

ኮሚሽኑ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ወረዳ እና ቀበሌ ድረስ በመውረድ አርብቶ አደሮችን፣ አርሶ አደሮችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የሃይማኖት ተቋማትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ የሲቪክ ማኅበራትን እና ዳያስፖራውን ያካተተ ሰፊ ሥራ ማከናወኑ የምክክሩን ተአማኒነት እና ሕዝባዊ ቅቡልነት ማረጋገጡን አብራርተዋል።

ከሕዝብ እና ከባለድርሻ አካላት በተሰበሰቡ አጀንዳዎች መሠረት ተለይተው በቀረቡ ስምንት ዐበይት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከመላው ሀገራችን የተውጣጡ ከ4,000 በላይ ተሳታፊዎች በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ሰፊ ምክክር በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

በዚህም የኃይል እና የጦርነት ፖለቲካን በማስቀረት ችግሮችን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት እንደሚቻል ማሳየት መቻሉን አፈ-ጉባኤው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጉባዔው በስኬት ሲጠናቀቅ ለሀገራችን ዘላቂ መፍትሔ የሚሆኑ በርካታ ዐበይት ምክረ ሐሳቦች መፍለቃቸውን የጠቆሙት አቶ ታገሰ ጫፎ፣ እነዚህ ምክረ ሐሳቦች ለቀጣይ የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ ለሕገ-መንግሥታዊ እና ተቋማዊ ለውጦች፣ እንዲሁም ለዘላቂ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

የምክክሩ ዋነኛ ግብ የትናንት ታሪካዊ ስብራቶችን በማከም ለቀጣዩ ትውልድ ሰላሟ የተጠበቀ እና ብልጽግናዋ የተረጋገጠ ሀገር ማስረከብ በመሆኑ፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፖለቲካ ኃይሎች እና የመንግሥት አካላት ከምክክሩ የተገኙ ውጤቶችን በባለቤትነት በመጠበቅ ወደ ተግባር እንዲተረጉሟቸው አፈ-ጉባኤው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም በራሳቸው እና በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

"የሀገር ብርታት ጥበብ ብልሃቱ ምክክር ነው"፦ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ን...
22/08/2026

"የሀገር ብርታት ጥበብ ብልሃቱ ምክክር ነው"፦ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

ነሐሴ 16/2018 ዓ.ም

ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ መዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የኢትዮጵያን አሸናፊነት የሚያረጋግጡ እና አንድነትን የሚያጸኑ የጋራ መሻቶች መገለጻቸውን ገልጸዋል።

ምክክሩ ለትውልድ የሚበጅ ጠንካራ ሐሳብ የተንሸራሸረበት ልዩ ቀን መሆኑን በማንሣት፣ ምክክር የሀገር ብርታት እንዲሁም የጥበብ እና ብልሃት መሠረት መሆኑን አስገንዝበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በመልእክታቸው 130 ሚሊዮን ሕዝብን በመወከል ለ46 ቀናት በቆየው ውይይት ላይ የተሳተፉትን ተመካካሪዎች በልዩ ሁኔታ አመስግነዋል።

ተሳታፊዎቹ የአካባቢያቸውን መልካም ተሞክሮ በማምጣት ለኢትዮጵያ በሚበጅ መልኩ ማቅረባቸውን አድንቀው፣ ይኸው የሰላም ውይይት እንዲሳካ ላስቻሉ የመከላከያ ሠራዊት እና መላው የጸጥታ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተጨማሪም ብሔራዊ ጥቅምን ያማከለ ምቹ የመወያያ መድረክ ላዘጋጁት የምክክር ኮሚሽኑ አባላት እና የዛሬ ሳንሆን የነገው ትውልድ ተስፋ እንድንሆን ላስቻሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ከፍ ያለ ዕውቅና ሰጥተዋል።

ፕሬዚዳንት ታየ ምክክር የነባር ባሕላችን አካል ቢሆንም ለፖለቲካ እና ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ለማዋል ከዚህ ቀደም ተሞክሮ እንደማያውቅ አስታውሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደዚህ ዓይነት የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ በቁርጠኝነት ኃላፊነታቸውን በመወጣታቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ውይይቱ ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ የተወጠነ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፣ ጉባኤው የሁላችንንም ኢትዮጵያ የሚያጸና እና ለመጻኢው ዕጣ ፈንታ ብሩህ ተስፋ የፈነጠቀ መሆኑን አስረግጠዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ነሐሴ 16፣ 2018 ዓ.ም ኢትዮጵያ ያካሄደቸው ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ለአፍሪካ ምሳሌ ...
22/08/2026

ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው - ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ

ነሐሴ 16፣ 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ያካሄደቸው ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላም በማስፈን ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ነው አሉ በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ፡፡

ከመላው ሀገሪቱ በሕዝቡ በተወከሉ 4ሺህ ተመካካሪዎች መካከል ከሐምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ በስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምክክሩ ለአፍሪካ ትልቅ ተምሳሌት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ አካታችና ሁሉን አሳታፊ ምክክር ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ተግባር ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ሰላምን ለማምጣት መነጋገርና መመካከርን መምረጣቸው የሚደነቅ ተግባር መሆኑን ገልጸው፤ ምክክር የቱንም ያህል ጊዜ ቢፈጅ ግጭትና ጦርነት ከሚያመጣው ጉዳት አንጻር ጠቃሚ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ምክክሩ በኢትዮጵያ ሰላም መስፈን ልማትና ብልጽግና ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡

አዲሱ የአርባምንጭ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ግንባታ ለተሟላ የማረም ማነጽ አገልግሎት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፦ ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ ነሐሴ 16 / 2018 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ...
22/08/2026

አዲሱ የአርባምንጭ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም ግንባታ ለተሟላ የማረም ማነጽ አገልግሎት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፦ ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ

ነሐሴ 16 / 2018 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ የተመራ የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የአርባምንጭ ማረሚያ ፖሊስ ተቋም የግንባታውን አፈጻጸምን ተመልክተዋል።

ኮሚሽነር ብርቱካን መንግስቱ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለፁት የግንባታውን ሂደት በተያዘለት ጊዜና የጥራት ደረጃ እንዲጠናቀቅ የተጠናከራ ክትትልና ቁጥጥር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ለአዲሱ ተቋም ግንባታ በክልሉ መንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱ የግንባታው ሂደት እንዲፋጠንና ፕሮጀክቱ በተያዘለት ደረጃ እንዲጠናቀቅ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ለሕግ ታራሚዎች የሚሰጡ የማረም ማነጽ፣ የሙያ ስልጠና፣ የጤና፣ የሥነ-ልቦናና ሌሎች የተሟላ አገልግሎቶችን በተሻለ ደረጃ ለማስፈጸም አቅም እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ስራ አስኪያጅ አቶ ውባየሁ ትዕዛዙ በበኩላቸው የተከናወኑ የግንባታ ሥራዎችን ከተደረገላቸው የቴክኒክ መስፈርትና ከተያዘላቸው የሥራ ዕቅድ አንጻር በመገምገም፣ አሁን ላይ ስራው 45% መድረሱን ገልፀው ቀጣይ ሥራዎችም በተቀመጠው የጥራት ደረጃና ጊዜ ለመጨረስ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

የግንባታ ሥራው በተፈለገው ጥራት እንዲከናወን ተቋራጩ፣ አማካሪዎችና ባለሙያዎች በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመው፣ በግንባታው ሂደት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ቴክኒካዊ ጉዳዮች በወቅቱ እየተለዩ መፍትሔ እንዲያገኙ ትኩረት እንደሚሰጥ አመላክተዋል።

ግንባታው ሲጠናቀቅም ለሕግ ታራሚዎች ተስማሚ የኑሮና የማረም ማነጽ አካባቢ ከመፍጠር ባለፈ፣ ታራሚዎች ወደ ማኅበረሰቡ በተሻለ ዝግጅት እንዲመለሱ የሚያግዝ ዘመናዊና ተሟላ የማረም ማነጽ ሥርዓትን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

መረጃው የክልሉ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው።

የወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2019 በጀት ዓመት  የሥራ ክንውን 1 ቢሊዮን 321 ሚሊዮን ብር  በላይ በማጽደቅ ...
20/08/2026

የወላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2019 በጀት ዓመት የሥራ ክንውን 1 ቢሊዮን 321 ሚሊዮን ብር በላይ በማጽደቅ ተጠናቋል

የቦዲቲ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ተካሂዷል።

ጉባኤው በቀረበው የከተማው አሰተዳደር ምክር ቤት የአስፈጻሚ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በማየት በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ በጥልቀት መክሯል።

ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች የከተማው ከንቲባ አቶ ዘካርያስ ጃታ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ህዝቡን ያሳተፈ የልማት ሥራዎችን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ከንቲባው በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የህዝቡ መሠረተ ልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ተሰርተው አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ጠቁመዋል።

በተለይም በጤና፣ ገቢዎች፣ በከተማው ግብርና፣ በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከተማውን ለማዘመን በተጀመረው የኮሪደረ ልማት ሥራ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበበት ነው ሲሉ አክለዋል።

በቀጣይም የህዝቡን አዳጊ ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የልማት ተግባራትን በማከናወን የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተመዘገቡ ስኬቶችን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ተቀናጅተው ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ምክር ቤቱ ባደረገው 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን ከ1 ቢሊዮን 321 ሚሊዮን 138 ብር በላይ በጀት በማጽደቅ ተጠናቋል።

ዘገባው ደሬቴድ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሶስተኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልን  በምክር ቤቱ  ደረጃ  አከበረ አርባምንጭ ነሀሴ 13/2018 ዓ/ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሶስተኛ ዓመ...
19/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሶስተኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልን በምክር ቤቱ ደረጃ አከበረ

አርባምንጭ ነሀሴ 13/2018 ዓ/ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የሶስተኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል ቀኑን በምክር ቤቱ አጠቃላይ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት አክብሯል።

እንኳን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 3ተኛ ዓመት የምስረታ ቀን በሠላም አደረሰን/ አደረሳችሁ!!

የኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ ነፀብራቂ፤ የብዝኃ ሕዝቦች የጋራ ቤት የሆነው ክልላችን፤ በክልሉ ሕዝቦች ነፃ ፍላጎትና ይሁንታ፤ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕገ-መንግስታዊ ሂደት፤ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ ታሪካዊ የምስረታ ጉባኤ የፌደረሽኑ 12ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ከተመሠረተ እነሆ ዛሬ ሦሥተኛ ዓመቱ ላይ ይገኛል፡፡

ባለፉት ሦስት የሥራ ዓመታት ምክር ቤቱ የሕዝቡን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እና ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማስመዝገብ የሚያገዙ ዘረፈ-ብዙ ፋይዳ ያላቸውን ፖሊሲዎች፣ አዋጆችና ደንቦችን በማውጣትና በማፅደቅ፤ ለወከሉት ማኅበረሰብ ሕገ-መንግሥታዊ ተልዕኮውን በብቃት በመወጣት ባለፉት ሦስት የሥራ ዓመታት በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ሕዝባችንን ተጠቃሚ ለማድረግ ለወከሉት ማኅበረሰብ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፤ ሕጎችንም አጽድቋል ብለዋል ምክትል አፈጉባኤዋ በመከፈቻ ንግግራቸው።

ክልሉ በአዲስ መልክ ከተደራጀ ወዲህ ምክር ቤቱ ፈጥኖ ቢሮና የሰው ኃይልን በማደራጀት ባለፉት ሦሥት ዓመታት ውስጥ ጉባኤዎችን በማካሄድ ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ፣ህጎችን በማውጣት፣የውክልና ሥራዎችን በማስተባበር እና የክትትል ቁጥጥር ሥራውን በማጠናከር በሁሉም መስኮች የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን ለይቶ በማረም ስኬታማ አመታት ማሳለፉን አብራርቷል።

ምክር ቤቱ ባለፉት በ3 ዓመታት አበይት ተግባራትን በዕውቀትና በብቃትት በመምራት በርካታ ውጤቶችን አስመዝግቧል፦በዚሁ መሠረት በክልሉ ምክር ቤት መሪነትና አስተባባሪነት ልዩ ልዩ ኩነቶችን ተቀብሎ በመምራት የክልሉን እምቅ የማልማት አቅሞችን በማስተዋወቅና ኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን እንዲጎለብት ምክር ቤቱ ህግ ማውጣቱ ላይ ትልቁን ድርሻ የተወጣበት ዓመት እንደሆነም አመላክቷል።

የ19ኛው የኢትዮጵያ ብ/ብ/ሕ/ቀን በዓልን በክልላችን አስተናጋጅነት ተቀብሎ ስናከብር የክልሉ ምክር ቤት ኩነቱን በመቀበል የክልሉ እምቅ ፀጋዎች ፣የኢንቨስትመንት መደረሻዎች እና በክልሉ የሚገኙ 32ቱ ነባር ብ/ብ/ሕ/ አኩሪ ባህልና ወግ በአገባቡ እንዲተዋወቅ በማድረጉ ላይ ከፍተኛ ሚና መተጫወቱን አንስተዋል።

እንኳን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓል አደረሰን/አደረሳችሁ!!መጪው ጊዜ ለሁላችን የስኬት የቡሩህ ተስፋና ውጤታማ ዓመት እንዲሆን እንመናለን።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አለማየሁ ባውዲ የክልሉ  ሦሥተኛ ዓመት የምሥረታ ቀንን  አስመልክቶ  ለመላው የክልሉ ሕዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላ...
19/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አለማየሁ ባውዲ የክልሉ ሦሥተኛ ዓመት የምሥረታ ቀንን አስመልክቶ ለመላው የክልሉ ሕዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

አርባምንጭ ነሀሴ 13/2018 ዓ/ም የኅብረ-ብሔራዊት ኢትዮጵያ ነፀብራቂ፤ የብዝኃ ሕዝቦች የጋራ ቤት የሆነው ክልላችን፤ በክልሉ ሕዝቦች ነፃ ፍላጎትና ይሁንታ፤ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሕገ-መንግስታዊ ሂደት፤ ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደ ታሪካዊ የምስረታ ጉባኤ የፌደረሽኑ 12ኛው ክልል ሆኖ በይፋ ከተመሠረተ እነሆ ዛሬ ሦሥተኛ ዓመቱን ይዟል፡፡

የክልላችን ሦሥተኛ የምሰረታ ዓመት ስናከብር በትላልቅ ድርብ ተልኮዎችን በድል ያጠናቀቅንበት ስኬታማ ዓመት ሲሆን ባህላዊ እሴቶችን ማእከል በማድረግ ከመነታረክ ይልቅ ሃሳብን በወንበር ዙሪያ በማውጣት ተነጋግሮ መፍታትን፣ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርንና ወንድማማችነትን ለማጎልበት፣ ከመከፋፈል ይልቅ ተደምሮ ለመበልፅግ፣ ከእኔነት/ከሰፈር እይታ በመሻገር አካታችና ሁሉ አቀፍ ተግባራትን ለመከወን ከመጠላለፍ በመላቀቅ ሀገራችን የውጤታማነት ምሳሌ ለማድረግ እና ነጠላ ትርክትን በመቅበር ገዢ ትርክትን የሁሉም ተግባሮች ማዕከል በማድረግ ህዝቡን በሁሉም ዘርፎች ለመካስ ተግባቦት ላይ ለመደረስ በሀገረ-መንግስት ታሪካችን ሲንከባለሉ የመጡ ጥልቅ ፖለቲካዊ ልዩነቶችንና ታሪካዊ ቅራኔዎች በታሪካዊው ሀገራዊ ምክክር ቋጭተን በምክክር የፀናች ተምሳሌታዊ ኢትዮጵያን ለማሻገር ከጫፍ በደረሰንበት አጓጊ የታሪክ ምዕራፍ ላይ መሆኑ በእጅጉ ያስደስታል፡፡

የክልላችን መመስረት፤ ለክልሉ ህዝቦች የአደረጃጀት ጥያቄዎች አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ታሪካዊ ምላሽ መስጠት ከመቻሉም በላይ የክልሉ ህዝብ ከግጭት አዙሪት ወጥቶ ፍቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት በማዞር በጋራ የመልማት ትልሙን ዕውን ለማድረግ በኅብረት በመትጋት ላይ እንዲገኝ አድርጓል፡፡

የክልሉ መመሰረት ተከትሎ የክልሉ ምክር ቤት ባለፉት በሶስት ዓመት ለክልሉ ሕዝብ ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች መከበር ፋይዳ ያላቸውን ፖሊሲዎች፣ አዋጆችና ደንቦች በማውጣትና በማፅደቅ፤ ለወከሉት ማኅበረሰብ ሕገ-መንግሥታዊ ተልዕኮውን በብቃት ለመወጣት ቋሚ ኮሚቴዎችን በማደራጀትና ጽሕፈት ቤቱን በማቋቋም ባለፉት ሦስት የሥራ ዓመታት በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ለወከሉት ማኅበረሰብ ውሳኔዎችን አስተላልፏል፤ ሕጎችንም አጽድቋል።

የክልሉን ህዝቦች አብሮነትና አንደነትን ለማጠናከርና ብዝሀንናታችን በባህላዊ ኩነቱና እሴቱ ውበት፣ በመሰባሰባችን እድል ከፀጋዎቻችን አንፃር ተስፋና በጋራ ዓላማ ዙረያ እንድንቆም በሚያግዘን መንገድ ህብረ- ብሄራዊ አንድነታችን ለማፅናት በርካታ ተስፋ ይዞ የተደራጀ ክልል ነው፡፡

በቀጣይም የሕዝባችንን አብሮነት፣ ወንድማማችነትና የጋራ እሴቶቻችንን በማጠናከር፣ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ ከወትሮው በተለየ በትጋት
መሥራት ይጠበቅበናል። “የመፍጠንና የመፍጠር” ዕሳቤን በመሰነቅ፣ በክልላችን የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸውና የሕዝባችን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ በጋራ
እንድንቀሳቀስ ጥሪዬን አቀርባለሁ አመሠግናለሁ።

አፈ-ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ የመጪው ጊዜ ለሁላችን ስኬታማ እንዲሆንልኝ እመኛለሁ!!

‎የኮሬ ዞን ሽግግር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ‎አርባምንጭ ‎ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም የኮሬ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኬ...
18/08/2026

‎የኮሬ ዞን ሽግግር ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔውን ማካሄድ ጀመረ

አርባምንጭ ‎ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም የኮሬ ዞን ሽግግር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን በኬሌ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል።

ምክርቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታው ያለፈውን ጉባኤ አጀንዳ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፤ የምክርቤቱን የ2018 ዓ/ም ሪፖርትና የ2019 ዓ/ም እቅድ ማዳመጥና ማጽደቅ፤ የዞኑ አስተዳደር የ2018 ዓ/ም ሪፖርትና የ2019 ዓ/ም እቅድ ማዳመጥና ማጽደቅ፤ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድቤት የ2018 ዓ/ም ሪፖርትና የ2019 ዓ/ም እቅድ ማዳመጥና ማጽደቅ፤ የዞኑን አመታዊ በጀት መርምሮ ማጽደቅ እና የተለያዩ ሹመቶችን በማጽደቅ ጉባኤዉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

‎‎በጉባኤው የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር ረዳት ፕሮፌሰር ሚሊዮን ደሳለኝ፣ የዞኑ ም/ቤት ዋና አፌ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ አካላት በቀለ፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ወገኔ ጌታቸዉ፣ የዞን አስተባባሪዎችና ካቢኔ አባላት፣የዞን ምክርቤት አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘገባው የኮሬ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ነው

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በዲላ  ከተማ  ከ500 ሚሊዬን ብር በላይ የተገነቡ ፕሮጀክቶች በመመረቅ ላይ ይገኛሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዲላ  ከተማ  በህብረተሰቡ ን...
16/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በዲላ ከተማ ከ500 ሚሊዬን ብር በላይ የተገነቡ ፕሮጀክቶች በመመረቅ ላይ ይገኛሉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዲላ ከተማ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ከ500 ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጪ የገነቡ ፕሮጀክቶች በመመረቅ ላይ ይገኛሉ።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት የክቡር ጠቅላይ ሚንስተር የጉባ ብስራት የሆነው አንድ ሚሊየን ቤቶችን ለዜጎች ሰርቶ የማስረከብ ኢኒሼቲቭ አካል በመሆን በአጭር ግዜ ግንባታቸው የተጠናቀቁ 70 ቤቶችን በመገንባን ለህብረተሰቡ መተላለፍ ችላል።

በተጨማሪም በከተማዋ የኮሪደር ልማት አካል የተገነባ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክ፣ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የተገነባውን የመኖሪያ ቤት እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶችተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በኮሪደር ልማቱ አካል በከተማው በመከናወን ላይ የሚገኙ የተለያዩ የመሰረተ ልማት፤ ዘመናዊ የመንገድና የጎዳና መብራት ዝርጋታዎች፣ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች እና የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን የተመለከቱ ሲሆን፤ የኮሪደር ልማቱ አካል የተገነባ ማሞ ኮሞልቻ የሕዝብ መዝናኛ ፓርክ መርቀው በይፋ ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት፤ በከተማዋ በመከናወን ላይ የሚገኘው የልማት ስራዎቾ ሻላይቱ ዲላን ይበልጥ በማስዋብ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ተመራጪነቷን በእጅጉ በማሳደግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ደረጃ ፕሮጀክቶችን በአጭር ግዜ በማጠናቅቀ ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረግ መቻሉ ስራዎች በአግባቡ ከተመሩ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል እንዲሁም መትጋት እና መቀናጀት ሁኔታን እንደሚቀይር ዲላዎችን ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ለፕሮጀክቶቹ በስኬት መጠናቀቅ አስትዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል

ሰው ተኮር የሆነው የበጎ አድራጎት ስራ እና የኮሪደር ልማቱ፤ ዲላ ከተማን በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ጽዱና ለኑሮ ምቹ በማድረግ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ፤ በከተማዋ ፍትሃዊ መሰረተ ልማትን ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ላይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ዲላ ከተማ መንግስት እንደ ሀገር ለከተሞች ዕድገት በሰጠው ከፍተኛ ትኩረት፤ ፕሮጀክቶች በፍጥነት በማጠናቀቅ በመመዝገብ ላይ ያለው አስደናቂ ውጤትና መሠረታዊ ለውጥ ተጨባጭ ማሳያ በመሆን ላይ መሆኗንም መመልከት ተችሏል፡፡

የክልሉ መንግስት ከተሞችን በህብረተሰቡ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ለኑሮ ምቹ የሆኑ የኢኮኖሚያዊ ዕድገት እና የማህበራዊ ሽግግር ማዕከላት እንዲሆኑ በማስቻል ወደ ብልፅግና የሚደረግ ጉዞን ለማሳለጥ ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ የበጎ ተግባራት እንዲሁም ለኮሪደር ልማት እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

Address

Arba Mintch

Telephone

+251951450475

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት - South Ethiopia Regional Council posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share