Boloso sore ezema

Boloso sore ezema Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Boloso sore ezema, Political organisation, Berhan bank building, Areka.

ኢዜማ ሀገራችን እያንዳንዱ ዜጋዋ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች የተከበሩባት፣ ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት፣ በዜጎቿ ጽኑ አንድነት ማዕቀፍ የተለያዩ ባህሎች፣ቋንቋዎችና እምነቶች ሳይበላለጡ በነጻነት የሚስተናገዱባትና የውበቷ መገለጫ ብቻ የሆነባት፣ ሠላምና መረጋጋት የተረጋገጠባት ገናና ሀገር ሆና ማየት

በሰኔ 22  2016 ዓም በተደረገው የወላይታ ዞን ኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ በዞን ምክር ቤት በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ የቦሎሶ ሶሬ 03 ምርጫ ክልል ተወካይና የዞን ም/ቤት አባል የሆነው...
30/06/2024

በሰኔ 22 2016 ዓም በተደረገው የወላይታ ዞን ኢዜማ ጠቅላላ ጉባኤ በዞን ምክር ቤት በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ የቦሎሶ ሶሬ 03 ምርጫ ክልል ተወካይና የዞን ም/ቤት አባል የሆነው መምህር ተክሌ ተሰማ የወላይታ ዞን ኢዜማ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሆኖ ተመርጧል።

7ኛ/በዞናችን ውስጥ ካለፉት አምስትና ስድስት ዓመት ወዲህ በፕሮጀክቶች ስም ሕዝብን ማታለል የተለመደ የአመራር ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡ ለአብነት፡- በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ውስጥ ብቻ  1ኛ/የሔ...
16/06/2024

7ኛ/በዞናችን ውስጥ ካለፉት አምስትና ስድስት ዓመት ወዲህ በፕሮጀክቶች ስም ሕዝብን ማታለል የተለመደ የአመራር ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡ ለአብነት፡- በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ውስጥ ብቻ 1ኛ/የሔምቤች ወይቦ መስኖ /የፌዴራል ፕሮጀክት/ ፣ 2ኛ/ የአረካ ዱቦ ልህቀት ማዕከል/ በወላይታ ሶዶ ዩኒቨረሲቲ ስም የተጀመረ/፣3ኛ/በቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በአረካ ከተማ ውስጥ የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግንባታ ፕሮጀክት/ ፣እና አሁንም በህዝብ ዘንድ ሌላ ጥርጣሬ እየጫረ ያለው አዲስ ልገነባ የተያዘው የአየር ማረፊያ የንብረት ና ሀብት ካሣ ግመታ ጉዳይ ትክክለኛ መረጃ ለህዝብ እየተሰጠ አለመሆኑ ኢ-ዜማን እያሳሰበ ይገኛል፡፡ ምክንያቱም እንደ ሀገርም እንደ ዞንም በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብና ሀብት ወጥቶበት በጊዜ ወደ ሥራ ብገባ የአካባቢውን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጡም በላይ በየጊዜው ቁጥሩ እየጨመረ የሚመጣውን የስራ አጥ ቁጥር ለመቀነስ ሰፊ የሥር ዕድል ያለው የሔምቤች ወይቦ መስኖ ፕሮጀክት በውስን ግለሰቦች ተጭበርብሮ ሥራው መቆሙ እንደ ወላይታ ዞንም እንደ ሀገርም ከፍተኛ ኪሣራ መሆኑን እና ሌላው ደግሞ ዘንድሮ አምስተኛ ዓመት የያዘው በዞንና በወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የመሠረተ ድንጋይ ተጥሎ በወቅቱ ከፍተኛ የህዝብ ማደነጋገሪያ ተሠርቶ እስከ ዛሬ ሀውልት ሆኖ የቀረው ነገር ግን እስከ ዛሬ በየዓመቱ ሥራ ሳይሠራ በስሙ እስከ ሦስት ሚሊዮን ብር እየተመደበ ያለው ፕሮጀክት ጉዳይ ማጣራትን የሚፈልግ እንድሁም በፌዴራልና በዩኒቨርሲቲ አመራሮች ልዑካን ቡድን ተመርቶ የመሠረተ-ድንጋይ የተጣለበት የዱቦ ልህቀት ማዕከል ጉዳይና ሌሎችም በሁሉም አካባቢዎች በጅምር የቀሩ እንደ ድንጋይም ተቀብሮ የተዘነጉ መሠረተ ልማቶች የህዝብ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደሆኑ ኢ-ዜማ ይገነዘባል፡፡ስለሆነም የወላይታ ዞንና የክልል እንድሁም የፌዴራል መንግሥት እነዚህ ልማቶች በምን ምክንያት እንደቁሙ ፣ የህዝብ ሀብት በማን እንደተመዘበረ ትክክለኛ ማጣራት በማድረግ በህግ ተጠያቂ በማድረግና የተቋረጡ ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ አልቆ ለህዝብ አገልግሎት እንድውል የወላይታ ዞን አ-ዜማ በአጽንኦት ያሳስባል፡፡

ሰኔ 9/2016 ዓ.ም

ወላይታ ሶዶ

5ኛ/ በዞናችን በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች እንድሁም በመዋቅሮች ውስጥ ባሉ የመንግሥት ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን በየጊዜው ሕዝብ እያማረረ የሰሚ ያለ እያለ ይ...
16/06/2024

5ኛ/ በዞናችን በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች እንድሁም በመዋቅሮች ውስጥ ባሉ የመንግሥት ተቋማት ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መኖራቸውን በየጊዜው ሕዝብ እያማረረ የሰሚ ያለ እያለ ይገኛል፡፡ ለአብነት፡ የመንግሥት ሹማምንቶች በቢሮአቸው በር ላይ ̋ የባለ ጉዳይ ማስተናገጃ ቀን̋ ̋ ብሎ ፕሮግራም በመለጠፍ ከዞን እስከ ወረዳ ባለው በሁሉም መዋቅር ቢሮ ተዘግቶ የሚውልበት ሁኔታ 2/ በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በሚባል ደረጃ የቅጥር ፣ የደረጃ ዕድገት ፣የመደብ አሰጣጥ ኢ-ፍትሓዊ ከመሆኑም አልፎ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ሀይ ባይ አጥቷል 3/ በየደረጃ ባሉ መዋሮች ሕዝብን የሚመሩ መሪዎች በአቅምና በችሎታ ሳይሆን በዘመድና በገንዘብ ሆኗል 4/ሕዝብ በነጻ ማግኘት ያለባቸውን የመንግሥት አገልግሎቶች ወደ ገንዘብ ተቀይሯል ፡፡ ለምሳሌ የማዘጋጃ ቤቶች ፣የፖሊስ ተቋም ፣የፍትሕ ተቋም ፣በጤና ፣ በግብርና ወዘተ ተቋማት ላይ አገልግሎት ለማግኘት ወይ ገንዘብ ወይ ዘመድ ያለው ሰው ብቻ ሆኗል፡፡እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዚህ ሁኔታ ከቀጠሉ የህዝብን ማህበራዊ ሕይወት ከማናጋትም አልፎ ሕዝብ በመንግሥት ላይ ተስፋ እንድቆርጥ ያደርጋሉ ብሎ ኢ-ዜማ ያምናል፡፡ በመሆኑም የወላይታ ዞን መንግሥት እነዚህን ችግሮች ከሥር መሠረቱ በማጥናት በአፋጣኝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘላቂ መፍትሔ እንድሰጥ የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ ፓርቲ ያሳስባል፡፡

6ኛ/ በአጠቃላይ በወላይታ ዞን የመንግስት ገንዘብ ተቋማት ማለትም የፋይናንስ ተቋማት ለረጅም ጊዜ ኦዲት ካለመደረጋቸው የተነሳ ለበርካታ ኪራይ ሰብሳቢነት ምንጭ ሆኗል፡፡ በዚህ በነሻ በርካታ መዋቅሮችና የፋይናንስ ተቋማት የመንግሥትንና የህዝብን ገንዘብ ባልተገባ መንገድ በረጅም ብድር ስም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አባክኖ የመንግሥት መዋቅሮችን ሁሉ ባለዕዳ በማድረግ ህዝብ ልማት አቷል፡፡ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ለአብነት የጤና አገልግሎት ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት ፣የተቋማት ግንባታ ና ጥገና ፣ እንድሁም ይባስ ብሎ የሠራተኛ ደመወዝ ፣ከሠራተኛ የተቆረጠ የብድር ተቋማት ተመላሽ /ለአብነት የአረካና አካባቢ የግብርና ባለሙያዎች ገንዝብ ቁጠባና ብድር ኅ/ሥራ ማህበር ገንዘቡ በፋይናንስ በመበላቱ ምክንያት ማህበሩ ከነአካተው እንድጠፋ በማድረግ/ ፣ ከመንግሥት ሠራተኞች የተቆረጠ የጡረታ ድርሻ ገንዘብ ፣ በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ለመንግሥት ሠራተኞች ካሠራጨው ብድር ገንዘብ በፋይናን የተመለሰው ለተቋሙ ሳይመለስ መበላቱ ፣ ወዘተ ባልተገባ መንገድ የጠፋ የህዝብ ሀብት እንደሆነ የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ ይገነዘባል፡፡በመሆኑም ይህ ችግር ከመዋቅሮች ችግር አልፎ ወደ ማህበራዊ ቀውስም ጭምር እየተሸጋገረ በመሆኑ የክልልና የፌዴራል መንግሥት ትክክለኛ የኦዲት ቡድን በመላክ በዞናችን ውስጥ ያሉ የፋይናንስ ተቋማትን ኦዲት በማድረግ የእርምት እርምጃ እንድወስድ የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

1ኛ/  በወላይታ ዞን ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ እየጨመረ የመጣው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ አከፋፈል ችግር በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ በአካባቢያችን ከፍተኛ የሆኑ ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስ...
15/06/2024

1ኛ/ በወላይታ ዞን ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሩ እየጨመረ የመጣው የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ አከፋፈል ችግር በዚህ ሁኔታ የሚቀጥል ከሆነ በአካባቢያችን ከፍተኛ የሆኑ ማህበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ምንም ዋስትና እንደለሌ ኢ-ዜማ ያምናል፡፡ ምክንያቱም አሁን የሚታየው የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ ያለምንም መነሻ የአንድ ወር ደመወዝ ለሦስትና ለአራት ጊዜ ቆራርጦ መስጠትና የመንግሥት የፋይናንስ ህግ ከመጣስም በላይ የተላከው ደመወዝ ለሌላ ዓላማ ማዋል፣ያለሠራተኛ ፈቃድ ለፈለገው ዓላማ ቆርጦ መውሰድ፣ ከሦስት እስከ አራት ወር ድረስ ደመወዝ ማዘገየት፣እና መሰል ችግሮች እንደ ዞናችን በሁሉም መዋቅሮች ጎልተው ይታያሉ፡፡ እነዚህ ችግሮች በኑሮ ውድነትና ከሀገሪቱ የንግድ ሥርዓት ችግር እንድሁም ከገቢም አንጸር በዝቅተኛ ኑሮ እየማቀቀ ያለውን የመንግሥት ሠራተኛውን ማህበረሰብ ሕይወት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል፡፡የመንግሥት ሠራተኛ በኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሥራ በመሥራት ግዴታውን ለተወጣ ሠራተኛ ለሠራበት ዋጋ በወሩ መጨረሻ ወራዊ ደመወዝ መክፈል የመንግሥት ግዴታ እንደሆነ ኢ-ዜማ ያምናል፡፡ እንድሁም የመንግሥት ሠራተኛም የሠራበትን የወሩን ደመወዝ የማግኘት ከሰብዓዊ መብቶች ዋነኛ እንደሆነም ኢ-ዜማ ይገነዘባል፡፡ በመሁኑም ከላይ የተዘረዘሩ ችግሮች በአሁኑ ጊዜ እጅግ ገዝፎ የመንግሥት ሠራተኛ እና ቤተሰቦቹን ከተለያዩ ማህበራዊ እሴቶች እያገለለ ይገኛል፡፡ ለአብነት፡- በከተማ ቤት መከራየት፣ መበደር፣መዋዋስ፣እቁብና እድር፣በማህበራት መደራጀት፣ቆጥቦ የወደፊት ህይወት መምራት፣ልጆቹን በግልም ሆነ በመንግስት ትም/ቤት ማስተማር፣ አቅመ ደካማ ቤተሰቦችን መጦር እና ከሌሎችም ማህበራዊ ኩኔቶች እየተገለለ ይገኛል፡፡ ይህ ችግር ከዚህም በላይ ከሄደ መንግሥትንና ህዝብን በማጋጨት ወደ ከፋ ደረጃ ሳይደርስ የወላይታ ዞን መንግሥት ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት ሰጥቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ዘላቂ መፍትሔ እንድሰጥ የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ ፓርቲ ያሳስባል፡፡
2ኛ/ በዞናችን በሁሉም መዋቅሮች ለአርሶ አደር በሚቀርብ ምርጥ ዘርና አፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ችግሮች ይታያሉ፡፡ከችግሮቹም ቀዳሚዎቹ ፡- 1/ የማዳበሪያ የአቅርቦት ችግር -አርሶ አደሩ ባለው ማሳ ልክ ማዳበሪያ ማግኘት ያለመቻል 2/ በየመዋቅሩ በማዳበሪያ ዋጋ ላይ በአንድ ኩንታል ማዳበሪያ ከ800/ከስምንት መቶ ብር/ እስከ 1600/አንድ ሺህ ስድስት መቶ ብር/ እና ከዚያም በላይ ተጨማሪ ዋጋ ማስከፈል 3/ መንግሥት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ በከፍተኛ ድጎማ ያመጣውን ማዳበሪያ አንዳንድ የወረዳዎችና የቀበሌያት የመንግሥት አመራር የሀብት ምንጭ ለማድረግ ለነጋዴ አሳልፎ በመስጠት አርሶ አደሩ አንድ ኩንታል ማዳበሪ እስከ 15,000/አስራ አምስት ሺህ/ ብር እንድገዛ ተገድዷል፡፡ ምርጥ ዘርም ቢሆን ለነጋዴ እና ለባለሀብት ተላልፎ በመሰጠቱ 1/ በጣም ዝቅተኛ ጥራት ያለው/የወደቀውን/ እያቀረቡ ለዛውም አርሶ አደሩ ከአቅም በላይ የሆነ ክፊያ እያስከፈሉ ይገኛሉ፡፡ አንድ ማህበረሰብ ተረጋግቶ ለመኖር በአካባቢ ግብርናው ምርታማ መሆን የግድ ነው ፡፡ እንደ አገር የተቀመጠውን ግብ የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት ብቸኛው መፍትሔው ምርታማነትን መጨመር እንዳለበት መንግስትም ያምናል፡፡ አሁን ያለውን የህዝብ ቁጥር እና በየጊዜው በፍጥነት እያደገ የሚመጣው የከተሞች መስፋፋትን የሚመጥንና መመገብ የሚችል እንድሆን የወላይታ ዞንም ሆነ ለሎች አርሶ አደሮች ከቤት ፍጆታ አልፎ ለገበያ ትርፍ አምራች ካልሆኑ ቀጣይ የማህበረሰባችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጡ ጉዳይ አደጋ ላይ ይወድቃል ብሎ ኢ-ዜማ ያምናል፡፡ በመሆኑም የዞኑ መንግሥት ከምንም ተግባር በላይ ቅድሚያ ሰጥቶ 1/ በተለያዩ በመንግስት አደረጃጀት ውስጥ ሆኖ በምርት ዘርና በማዳበሪያ ስርጭት ውስጥ እጃቸውን በማስገባት ስህተት እየፈፀሙ ያሉትን አመራር ተጠያቂ እንድያደርግ 2/በየመዋቅሩ የማዳበሪያና ምርጥ ዘር ስርጭት ወቅት በአርሶ አደር ላይ የሚመጣውን አላስፈላጊ መዋጮዎችን እንድያስቆም 3/በየቀበሌ በማዳበሪያ ዋጋ ላይ የሚደረግ የተለያየ ተጨማሪ ክፊያ እንድያስቆምና ከዚህም በፊት አለ አግባብ የተከፈለውን አጣርቶ ገንዘቡን ለአርሶ አደሮች መልሰው ይህንን ድርጊት የፈፀሙትን ጥፋተኞች ተጠያቂ እንድያደርጋቸው 4/መንግሥት የማዳበሪያ አቅርቦት እጥረት እንዳያጋጥም በጊዜ መረባረብና አዝመራ ወቅት ከመድረሱ አስቀድሞ መዘጋጀትና ምርጥ ዘር ዋጋ ላይም ከፍተኛ ጥናት እንዲያደርግ የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ በጥብቅ ያሳስባል፡፡
3ኛ/ የዞናችን ማህበረሰብ ከሌሎች አካባቢዎች ጋር ሲነጻጸር የጤና መድህን መዋጮ በየዓመቱ በመክፈል እና አባል በመሆን ረገድ ግንባር ቀደም መሆናችንን መንግሥት በየጊዜው በሚያደርጋቸው የጤና ጉባኤዎች ላይ ሲያረጋግጥ ቆይቷል፡፡እኛም በቅርበት በየቀበሌ አደረጃጀቶች ማህበረሰባችን በጤና መድህን መዋጮ ከማንኛውም አርሶ አደር ከግብር ጋር ተከፍሎ እንዳለቀ ግልጽ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ ደረጃዎች በሚደረጉ የአሠራር ጥሰቶች ምክንያት ማህበረሰባችን በጤና መድህን አገልግሎት እርካታ እያገኙ አይደለም፡፡ለአብነት 1/በቀበሌ ደረጃ መዋጮ ለከፈሉ አርሶ አደሮች የጤና መድህን አባልነት መታወቂያ ያለመስጠት ችግር 2/ በየጤና ተቋማት መታወቂያ ያላቸውም የተሟላ አገልግሎት ያለማግኘት ችግር 3/በሀሁሉም ጤና ተቋማት በጤና መድህን ለሚታከም ሰው በከፍልም ሆነ በሙሉ መድሃኒት ያለማግኘት ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ ማህበረሰባችን ግን ከመንግሥት ጋር በገባው ውል መሠረት በየዓመቱ ውሉን የማደስ ግዴታውን እስከተወጣ ድረስ በያዘው መታወቂያ በየትኛውም ጤና ተቋም ሙሉ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አለበት ብሎ ኢ-ዜማ ያምናል፡፡ እንድሁም አንዳንዴ ሊፈጠር በሚችለው የመድሃኒት እጠረት አባሉ ከውጪ በትዕዛዝ የሚገዛ ከሆነ ከተቋሙ በህጋዊ ደረሰኝ ገንዘቡን የመቀበል መብት እንዳለውም ጭምር ይገነዘባል፡፡ ስለሆነም የወላይታ ዞን መንግሠት ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን ይህንን አሠራር በጥልቀት እንድፈትሽና ቀጣይ ማህበረሰባችንን ከእንግልት እንዲያወጣ ሲል የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ በአጽንኦት ያሳስባል፡፡
4/ላለፉት አራት እና አምስት ዓመታት የዞናችን ህዝብ በየማህበራዊ መሠረቶች የተለያዩ ሀገራዊ ፣ ክልላዊ ፣ዞናዊ ፣ ወረዳዊ እና ቀበሌያዊ የተባሉ መዋጮዎችን ለበርካታ ጊዜያት ስያዋጣ ቆይቷል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛም ቢሆን በግዴታ በፔሮል እየተቆረጠ በአንዳንድ መዋቅሮች ላልታወቀ ዓላማ የዋለበትም የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡/ ለአብነት ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ በ 2014 ዓ.ም ከአንድ ሠራተኛ 500/አምስት መቶ ብር/ በሥራ አስፈጻሚ ተወስኗል ተብሎ በወረዳ ሥራ አስፈጻሚዎች ብቻ ዞንም ሳያውቅ የጠፋበት ሁኔታ ነበር፡፡ በመሆኑም በህዝብ ላይ በየጊዜው በመንግሥት አካላት የሚጣለው መዋጮና ጫና በኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት የተደነገገውን የዜጎች ሰብዓዊ መብትን የሚጥስ መሆን እንደለሌበትና እንድሁም ምክንያታዊ ፣ሕዝብ ያመነውና የፈቀደው ፣የህዝቡን የኑሮ ሁኔታን ያገናዘበና ሕጋዊነቱን የጠበቀ መሆን እንዳለበት አ-ዜማ ያምናል፡፡ነገር ግን ከእነዚህ በተቃራኒ እየተደረገ ያለው መዋጮ ለአብነት 1/ያለ ግለሰቡ ፈቃድ በማሰር በመደብደብ ሀብትና ንብረትን በመዝረፍ 2/ ያለ ምንም ደረሰኝ ገንዘብ በህገ ወጥ መንግድ መሰብሰብ 3/በተደጋጋሚ በአንድ ዓመት ከሦስት እና ከአራት ጊዜ በላይ መዋጮ በመጠየቅ ለሕዝብ እፎይታ በመንሳት 4/የሕዝብን አቅምና የኑሮ ሁኔታን ያላገናዘበ ከአቅም በላይ የሆነ ለአብነት ̋አንድ መጽሐፍ ለአንድ ተማሪ ̋ በሚል የመጣው መዋጮ በአንድ ቀበሌ ላይ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ መዋጮ ግዴታ በመጣል ፣ በዚህ ሰበብ በገጠር ያለው የወል መሬት ለግለሰቦችና ለሀይማኖት ተቋማት መሸጥ እና ሌሎችም መሰል ችግሮች እየገዘፉ ሲሄዱ ሕዝብ በመንግሥት ላይ እምነት እንዲያጣ ያደርጋል፡፡ ማንኛውም የመንግሥት ገቢ በየትኛውም ደረጃ ያለደረሰኝ መሰብሰብ ለአንዳንድ ግለሰቦች ህገ ወጥ ሀብት ምንጭ መሆኑ ስለሚታወቅ ሆን ተብሎ የሚደረግ የህግ ጥሰት እንደሆነና ይህ የህግ ጥሰት ደግሞ የመንግሥት አመራር ኪራይ ሰብሳቢነት አዝማሚያ ከመሆኑ አልፎ ኪራይ ሰብሳቢነት ተግባር ነው ብሎ ኢ-ዜማ ያምናል፡፡ ስለሆነም የወላይታ ዞን በሁሉም መዋቅሮቸ እየገዘፈ የመጣውን የመዋጮ እና የመንግሥት ገቢ አሰባሰብ ችግር ከመሠረቱ በማጣራት የተፈጠሩ የህግ ጥሰቶችን በፍጥነት አርሞ የህግ ጥሰት የፈጸሙ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ እና በዚህ ሁኔታ የተመዘበረውን የሕዝብና የመንግሥት ሀብት የዞኑ መንግሥት እንድያስመልስ ሲል የወላይታ ዞን ኢ-ዜማ በጥብቅ ያሳስባል፡፡

የቦሎሶ ሶሬ ሕዝብ መልካም አስተዳደር ችግሮች Bolooso soore deriya lo"o ayisuwa metotaየቦሎሶ ሶሬ ምርጫ ክልል 03 ኢዜማ(የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ) ፓርቲ ሥ...
09/04/2024

የቦሎሶ ሶሬ ሕዝብ መልካም አስተዳደር ችግሮች
Bolooso soore deriya lo"o ayisuwa metota
የቦሎሶ ሶሬ ምርጫ ክልል 03 ኢዜማ(የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ) ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚዎች ባደረግነው ውይይት በወረዳችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይተን ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ አስተዳደር በደብዳቤ አዘጋጅተን በአካል ሄደን በቀን 23/07/2016 ዓም ያመለከትን ቢሆንም ለሕዝብ ችግር ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኝነት የሌለ በመሆኑ እነዚህንና ሌሎችንም ጉዳዮች መንግስት ትኩረት ሰጥቶ ሕዝብን እንዲያዳምጥ እናሳስባለን ።
Bolooso soore dooruwa zawaa 03 iizeemaa parttiya oosuwa polissiyageeti oottido zoretan hagaappe garssaara paatettida lo"o aysuwa metota ekkidi allana ayssiya gadaawakko gallassaa 23/07/2016 ML shiishshidaba gidikkone deriya metuwassi zaaruwa immanawu eenotay baynna gishawu kawotettay hageetussinne hara allaalletussi tishsha xeelaa immidi deriya ezgganaadan hassayisos.
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ዝርዝር እነንደሚከተለው ይቀርባል
Lo"o aysuwa metoti kaalliyagaadan shiiqoosona
1. መንግስት ሠራተኛ (kawo oosanchchatuba)
-ደሞዝ በጊዜ ባለመከፈል፣እየተቆራረጠ መከፈል እና ሰክቴርን ከሴክቴር ለይቶ መክፈል ለማህበራዊ ቀውስ እየተዳረገ መሆኑ
-damoozay wodiyan qanxxettennaagan, duuxerettidi qanxxettiyoganinne ooso keettata issuwa issuwappe dummayidi qanxxiyogan kawo oosanchchay deretetta gooshshaa giddo geliidi de"ees
2. ግብርና (goshsha oosuwaba)
-ለአርሶ አደር አፈር ማዳበሪያና ምርጥ ዘር በጊዜ ተደረሽ ካለመሆኑም በላይ ለነጋዴ ተላልፎ በመሰጠቱ ጥራት የሌለውን ምርጥ ዘር በመዝራት ለኪሳራ መዳረግ
-goshshanchchatussi imettiya biittaa araddissiya madaabarenne lo"o zerettay wodiyan gakkenaga bolli zal"anchchawu aatti immoogaappe denddaagan zerido kattay biittappe kiyennaga gaasuwan goshshanchchay gammaa meetettiidi beettes
-በወረዳችን ከየትኛውም አከባቢ በተለየ ሁኔታ በአንድ ኩንታል የ800 ብር የዋጋ ልዩነት መኖሩ በአርሶ አደሩ ኢኮኖሚ እና የማምረት አቅም ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ
- nu allaanan hara heeraappe dumma ogiyan issi kuntaale madaabariya hosppun xeetu biraa dummatettan shammiyoge goshshanchaa ikkonomiyanne murutissiyo wolqqa qohiiddi de"ees
3. በትምህርት (timirttiyaba)
-የመምህራን ደሞዝ ወቅቱን ጠብቆ ባለመከፈል፣ ለተማሪዎች መማሪያ መጽሐፍ ባለመኖሩና ቴክኖሎጂን በመጠቀም ለመማር ማለትም smartphone (ዘመናዊ ስልክ) መግዛት ከተማሪ ወላጅ አቅም በላይ ከመሆኑ የተነሳ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ያለመገኘታቸው
- tamaarissiyagetussi damoozay wodiya naagidi qanxxettennagan, tamaariyo maxaafay baynaaganinne zammaana silkiya shammanawu so asaassi wolqqi baynnaagaappe denddaagan tamaareti timirttiyappe haakkidi beettoosona
4. በጤና (payyatettaa)
- የጤና መድህን ዓመታዊ መዋጮ ሕዝባችን ከመሬት ግብር ጋር የከፈለ ቢሆንም በወረዳችን ባሉ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች የመድሀኒት አቅርቦት ባለመኖሩ ከውጪ መግዛት
-xeenaa mediiniya nu deree giiraara issippe qanxxaba gidikkonne nu allaanan de"iya ubba payyatetta eqotatunkka xalee baawa gin deree kareppe shamiiddi de"ees
- የትርፍ ጊዜ ክፍያ (duty) ባለመከፈሉ፣ አምቡላንስ በነዳጅ እጥረት በመቆሙ ወላድ እናቶች የጤና አገልግሎት አለማግኘት
-aakimetussi palaha wodiya miishsha (dutiya) qanxxennaagaappe denddaaganinne ambulanssee lambay baynnagan eqqido gaasuwan yeliya aayoti payyatettaa haggaazaa demmiiddi de"okkona
5. ሸማቾች (shammiyageetubaa)
- በወረዳ ደረጃ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች በመንግሥት ድጎማ በተመጣጣኝ ዋጋ ሲቀርብ የነበረው ዘይት፣ስኳር፣የዳቦ ዱቄት፣ሳሙናና መሰል ሸቀጣሸቀጦችን እንዲሰጡመንግስት ያደራጃቸው የሸማቾች ህብረት ሥራ ማህበራት የገቡበት አለመታወቅ
-allaanan guutta wolqqaara de"iya deriyaassi kawotetta maaduwan shiiqiiddi takkida zayitee, sukkaaree,daabbuwa xiillee,saamunaynne harabati gishiyageti awu gelako eretenna gaasuwan asaassi gakkiiddi dookkona

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ) ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት መጋቢት 13/2016 ዓ.ም. በተላከ መልዕክት እንደተገለፀው ከመጋቢት 22-24 ድረስ የጉብኝትና የው...
04/04/2024

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ( #ኢዜማ) ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት መጋቢት 13/2016 ዓ.ም. በተላከ መልዕክት እንደተገለፀው ከመጋቢት 22-24 ድረስ የጉብኝትና የውይይት መርኃግብር ላይ ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስድስት ሰዎች እንዲወክሉ በቀረበው ጥሪ መሠረት የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው ተወያይቶ ስድስት ተወካዮችን ማለትም ከመሪው ዘርፍ ሶስት ተወካዮች /ምክትል መሪው ፣ የትይዩ ካቢኔ አባል እንዲሁም የሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ/ ከድርጅት ዘርፍ ሶስት ተወካይ /ሊቀመንበር ፣ ዋና ፀሐፊ እና የሴቶች መምሪያ ሐላፊ/ አራት ወንድና ሁለት ሴት ተወካዮችን ልኮ በመድረኩ ላይ ተሳትፏል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረው ውይይትም በፅሁፍ የተዘጋጀውን ጥያቄ ለመጠየቅ እድሉን ባገኙት የፓርቲያችን ዋና ፀሐፊ እና የብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ አባል በሆኑት አቶ አበበ አካሉ በኩል በንባብ ማቅረቡን ለአባላት እና ደጋፊዎቻችን እያሳወቅን በዕለቱ የቀረበውን ጥያቄ ፅሁፍ ከዚህ በታች አያይዘናል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)የቦሎሶ ሶሬ ምርጫ ክልል 03 የኢዜማ ጽ/ቤት በይፋ የተከፈተ መሆኑን እያበሠርን ማንኛውም በዜግነት ፖለቲካ የሚያምን አባል መሆን የሚችልና ጽ/ቤታች...
26/03/2024

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)
የቦሎሶ ሶሬ ምርጫ ክልል 03 የኢዜማ ጽ/ቤት በይፋ የተከፈተ መሆኑን እያበሠርን ማንኛውም በዜግነት ፖለቲካ የሚያምን አባል መሆን የሚችልና ጽ/ቤታችን መጥቶ መመዝገብ የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።
አድራሻ: አረካ ዱቦ ማዞሪያጋ ብርሃን ባንክ ያለበት ህንጻ 1ኛ ፎቅ

12/03/2024
26/02/2024

አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ የመከላከያ ሰራዊት ወታደሮች በባህር ዳር ከተማ ፈጽመዋቸዋል ያላቸው “ግድያዎች” “የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ ይችላሉ” አለ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች ከአምስት ወራት በፊት በባህር ዳር ከተማ ፈጽሟቸዋል የተባሉ “ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ ግድያዎች”፤ በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት “የጦር ወንጀሎች ሊሆኑ ይችላሉ” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ “ተንሰራፍቷል” ያለው “የተጠያቂነት እጦት፤ “በዓለም አቀፍ ህግ ወንጀል የሆኑ ከባድ በደሎችን የሚፈጽሙ አካላትን የሚያደፋፍር ነው” ሲል ወንጅሏል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ይህን ያስታወቀው፤ ባለፉት ነሐሴ እና መስከረም ወራት በባህር ዳር ከተማ የተገደሉ 12 ሰዎችን በተመለከተ፤ ዛሬ ሰኞ የካቲት 18፤ 2016 ባወጣው አጭር ሪፖርት ነው። ዓለም አቀፉ ተቋም በዚሁ ሪፖርቱ በመጀመሪያ የዳሰሰው፤ በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 በተለምዶ አቡነ ሀራ እና ልደታ በሚባሉ አካባቢዎች የተፈጸመውን የስድስት ሰላማዊ ዜጎችን ግድያ ነው።

ስድስቱ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች የተገደሉት፤ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት “በቅርብ በተተኮሱ ጥይቶች” መሆኑን አምነስቲ የዓይን እማኞችን እና የቤተሰብ አባላትን ዋቢ በማድረግ በሪፖርቱ ይፋ አድርጓል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ “ከህግ አግባብ አውጪ” ተገድለዋል ካላቸው “ሰላማዊ ዜጎች” መካከል፤ “በመኖሪያ ግቢያቸው እንጀራ እየጋገሩ ባሉበት በተተኮሰባቸው ጥይት እንደተመቱ” የዓይን እማኞች የመስከሩላቸው ወ/ሮ ይታጠቁ አያሌው አንዷ ናቸው።

በዚህ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት ውስጥ፤ “በንግድ ስራ ይተዳደሩ ነበር” የተባሉት የ55 ዓመቱ አዛውንት አቶ አየነው ደፍረሽ እና ሁለት ልጆቻቸው ይገኙበታል። “እነዚህ ሶስት የቤተሰብ አባላት የተገደሉት፤ ከቤተክርስቲያን ወደቤታቸው በመመለስ ላይ እያሉ ጎዳና ላይ በጥይት ተመተው ነው” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል በሪፖርቱ ላይ አስፍሯል።

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2024/12622/

25/02/2024

ንቁ ዜጋ! ምቹ ሀገር

Address

Berhan Bank Building
Areka

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251925137932

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Boloso sore ezema posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share