Buzena Alkedir

Buzena Alkedir የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ
Speaker of the Addis Ababa City Council
(1)

"በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖ...
03/09/2026

"በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።
‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።

‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።" - የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር Abiy Ahmed Ali

እንኳን ደስ አለን!!ዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ ለከተማችን ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” በማት እውቅና ሰጥቷ...
02/09/2026

እንኳን ደስ አለን!!

ዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ ለከተማችን ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” በማት እውቅና ሰጥቷል፡፡
ከተማችን የሁሉንም ነዋሪዎቿን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ፣ ፈጣንና ፍትሐዊ ልማትና ዕድገት እያሳየች ትገኛለች፡፡ ልማቷ የዛሬ ነዋሪዎቿን ብቻ ሳይሆን መጪውን ትውልድም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን ሀገሩን የሚወድ፣ ለሀገሩ የሚቆረቆር፣ ያለፈውን ትውልድ የማይወቅስ፣ ለተከታዩ ትውልድም የሚያስብ እንዲሆን ዛሬ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ፣ ለዚህ ዕውቅና አብቅቷል፡፡ የተከበሩ ከንቲባ፣ ይህ የአመራርዎ ውጤት ነውና በድጋሚ እንኳን ደስ አለዎ!

02/09/2026

ኢትዮጵያ ተስፋ አላት፤ የሚጨበጥ ተስፋ!

01/09/2026
እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ!የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የ"ጓንዷ" በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ አክብረናል።የኢትዮጵያን ብዝኃ-ባሕልና የባሕል እሴቶች ለልማት፣ ለሰላምና ...
29/08/2026

እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ!

የጉሙዝ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የሆነውን የ"ጓንዷ" በዓል ዛሬ በአዲስ አበባ አክብረናል።

የኢትዮጵያን ብዝኃ-ባሕልና የባሕል እሴቶች ለልማት፣ ለሰላምና ለሕዝቦች አንድነት እንዲሁም ለትውውቅና እርስ በርስ ቅርርብ መጠናከር ዓይነተኛ ሚና ባለው መልኩ መጠቀም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።

የሁሉም ሕዝቦች መኖሪያዋ ከተማችን አዲስ አበባ፥ በዚህ ረገድ ያላት ሚናና የትውውቅ መድረክነት በእምቅ አቅም ልክ በስፋት እየተሠራባት ይገኛል። ቱሪዝም ለኢኮኖሚ ዕድገታችን ያለው ላቅ ያለ ሚናም ከጊዜ ወደ ጊዜ አድጎ እየታየ ይገኛል።

እንዲህ ዓይነቶቹን የኢትዮጵያውያን የጋራ ሐብቶች የሆኑ ክብረ በዓላትና የበዓላት እሴቶች ወደዓለም ሕዝቦች የጋራ ሀብትነት በማሸጋገር ልናስቀጥልም ይገባል።

ጓንዷ ለዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ እድገት!

29/08/2026

"አንድነታችን የኢትዮጵያ ታላቁ ጥንካሬዋ ነው።" 🇪🇹

27/08/2026

ቃል ሐሳብን ይቀርጻል፤ ሐሳብ ደግሞ ዓለምን ይለውጣል። ንግግሮች የጊዜን ወሰን ሰብረው፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩ የሕዝቦች የማንነት ማኅተምና የዘመን ምስክር ናቸው። በመሪዎች መነጽር ሲታይ ቃል ቀላል ድምፅ ሳይሆን፣ ታሪክን የሚወስን፣ ማኅበረሰብን የሚቀይር እና ሀገርን የሚገነባ የኃይል ምንጭ ነው። በመሪዎች ቃል ውስጥ ህዝብ የሀገርን ተስፋና የመሪዎቹን ርዕይ እንዲቃኝ ያስችላል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አዘጋጅነት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) ከ2017 እስከ 2018 ዓ.ም ያደረጓቸውን ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን መልዕክቶች ዳግም «ከመስከረም እስከ መስከረም» በተሰኘው መጽሐፍ 8ተኛ ቅጽ በይፋ ለአንባቢያን ቀርቧል።
እርስዎም በመጽሐፉ ዘልቀው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያየ አቅጣጫ ሀገር ለማቅናት የተጓዟቸውን የዓመት ጉዞ በተለያዩ ጊዜያት ባደረጓቸው ቁልፍ ንግግሮች እና ያስተላለፏቸውን አቅጣጫ ጠቋሚ መልዕክቶች ይቃኙ።

ሙሉ መጽሐፉን ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ:- https://share.google/uTjPqcMG1OFDWj7Xq

የ3ኛ ዙር ምክር ቤታችን የሥራ ዘመንና የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የምስጋናና የዕውቅና መድረክ ዛሬ አካሒደናል።የምክር ቤታችን የሥራ ዘመን ስኬታማነት መላው መዋቅራችንና ተጠሪ ተቋማት በ...
27/08/2026

የ3ኛ ዙር ምክር ቤታችን የሥራ ዘመንና የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የምስጋናና የዕውቅና መድረክ ዛሬ አካሒደናል።

የምክር ቤታችን የሥራ ዘመን ስኬታማነት መላው መዋቅራችንና ተጠሪ ተቋማት በቅንጅትና በተናበበ መንገድ የመሥራታቸው ውጤት ነው።

ባለድርሻና አጋር አካላት እንዲሁም የከተማችን ነዋሪዎች በማሣተፍ ለተልዕኳችን ስኬት ላደረጋችሁት ያልተቆጠበ ድጋፍ ላቅ ያለ ምሥጋና አቀርባለሁ።

በቆይታችን ያካበትነው ልምድ ለቀጣይ ስራችን ስንቅ ነው፤ የመረጠንን ሕዝብ በተሻለ ለማገልገል አቅም ይሆነናል።

የረዳን ፈጣሪ ይክበር።

መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ብሩህ ነው።

ፈጣሪ ውዷን ሀገራችንና ሕዝቧን ይባርክ፤ ይጠብቅምም።

Address

Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Buzena Alkedir posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Buzena Alkedir:

Shortcuts

Share