09/08/2026
ማስታወቂያ ለአሶሳ ከተማ ደረጃ ''ሀ'' ግብር ከፋዮች (ለተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢዎች በሙሉ:-
******
ነባሩ ደረሰኝ እንደ ክልላችን ከሰኔ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ መጠቀም እንደማይቻል በማስታወቂያ መግለፃችን ይታወቃል። ስለዚህም QR code የሌለው ደረሰኝ እና ካሽ እሪጅስተር ማሽን መጠቀም እንደለበችሁ በጥብቅ እያሳሰብን ለተከታታይ 3 ቀን ማለትም ከቀን 04/11/2018 ---06/11/2018 ዓ.ም ድረስ የካሽ እሪጅስተር ማሽን በመግዛት እንድትጠቀሙ ስንል እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ :-በተባለው ቀን መጥተው የሸያጭ ማሽን ግዢ የማይፈጽም ግብር ከፋይ ህጋዊ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳውቃለን ።
''የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ''