20/08/2026
በአጣዬ ከተማ የመንግስት ሰራተኛ አባላት "ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ማረጋገጥ "ላይ ውይይት ተካሄደ።
አጣዬ፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም. (አጣዬ ኮሙኒኬሽን) —
በአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከመንግስት ሰራተኞች የብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ተካሄደ።
የውይይቱን መድረክ በንግግር የከፈቱት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ፣ የዕለቱ የውይይት መድረክ በሰነዱ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲመካከሩና ሀሳብ እንዲለዋወጡ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።
በመቀጠልም የ“ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን” የውይይት ሰነድ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሮ ዘቡራ ከድር ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።
በሰነዱ ላይም ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት ሰጥተዋል።
ውይይቱ በተለይም የሰላምን መሠረት ማጠናከር፣ የውጫዊ ወረራ ስጋቶችንና የውስጣዊ ፅንፈኝነት አደጋዎችን በጋራ መመከት፣ ዘላቂ ሰላምን ማረጋገጥና የከተማዋን ልማት ማፋጠን በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ያተኮረ ነበር።
በመድረኩ ከቀረበው የውይይት ሰነድ መነሻነት ተሳታፊዎች የሰላምን ሁኔታ ለማስጠበቅ፣ የከተማዋን ልማት ለማስቀጠልና ህብረተሰቡን ለማጠናከር የሚያስፈልጉ የጋራ እርምጃዎችን በተመለከተ ሀሳቦችን አንስተዋል።
በመጨረሻም የተሳታፊዎችን ጥያቄዎችና አስተያየቶች በተመለከተ ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ተመስገን ተስፋ እና የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ከድር እንድሪስ ናቸው።
በማጠቃለያውም የመንግስት ሰራተኞች የሰላምና የልማት ሂደቱን በማጠናከር፣ ህግንና ሰላምን በመጠበቅ እና በተሰጣቸው ሙያዊ ኃላፊነት በብቃት በመወጣት የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
ህውሃት በአማራ ክልል ላይ የጦርነት እሳቤ መቀልበስ፣ የኢኮኖሚ ወድቀት እንዳይከሰት መቀልበስ ፣ ህውሃት በተለያዩ ተቋማት ውድመት እንዳይከሰት መመከት እና የህብረተሰብ መሰተጋብር እንዳይቋረጥ መስራት፣ ከውጪ ጠላት ጋር በመሆን በክልሉ ጥቃት እንዳይፈፁሙ መመከት በሚሉት ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም ዘላቂ ሰላም ለልማት ወሳኝ መሠረት መሆኑን በመገንዘብ፣ አመራሩ፣ መንግስት ሰራተኞችና ህብረተሰቡ በጋራ በመስራት ለከተማዋ ሰላም፣ ደህንነትና ልማት የሚጠበቅባቸውን ሚና ለመወጣት በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል።
"ፅንፈኝነት በማክሸፍ ወረራን በመመከት ሰላማችንና ልማታችንን እናረጋግጣለን!"