Kirkos cherkos w10communication

Kirkos cherkos w10communication Ensure Efficient And Effective Flow Of Information Between The Government And Public

28/10/2018

ቅን ልቦች! የቂርቆስ ወ10 ቀ25 ወጣቶች ማህበር በዛሬው ቀን ከ700 በላይ በጎዳና ላ ያሉ ወገኖችን ገላአ ጥበው ልብስ ቀይረው ምሳ በመጋበዝ ደስ የሚል የበጎ ፍቃድ ተግባርን ፈፅመዋል

14/10/2018

በቂ/ክ/ከ/ወረዳ10 አስ/ር በህገወጥ መንገድ የተያዙ እና ኮዶሚንየም ደርሷቸው ያልተለቀቁ የመንግስት ቤቶችን የማስለቀቅ እርምጃው የቀጠለ ሲሆን ከ50 በላይ በህገወጥ የተያዙ ቤቶች ይለቀቃሉ

11/10/2018

ሰንደቅ አላማችን ለዴሞክራሲያዊ አንድነታችን!! የቂርቆስ ወረዳ10 ሰራተኞች 11ኛው የሰንደቅ አላማ ቀንን አስመልክ ቶ በሰንደቅ አላማ ምንነትና ክብር ዙሪያ በመወያየት እለቱን አክብረዋል

27/07/2018
kirkos wereda10 yBego Fikad agelgilot Endih tejemirwal,Kirkos wereda10 youth voluntarisem
25/07/2018

kirkos wereda10 yBego Fikad agelgilot Endih tejemirwal,
Kirkos wereda10 youth voluntarisem

16/07/2018

Economist Charles Robertson discusses the economic challenges facing Ethiopia.

welcome Mr,presidant
13/07/2018

welcome Mr,presidant

27/06/2018

ኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት ትጀምራለች - ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ

ኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ድፍድፍ ነዳጅ ማውጣት እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቻይናው ፖሊ ሲ ጂ ኤል ኩባንያ በምስራቅ ኢትዮጵያ ሲያደርግ የቆየው የድፍድፍ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋ ውጤት ማስገኘቱን ተናግረዋል።

ሰኔ 20 ፣ 2010 (ኤፍ ቢ ሲ)

05/06/2018

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች ይፋ አድርጓል።

የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በዛሬው ስብሰባው ኢትዮጵያ ላለፉት 15 ዓመታት ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሏን፣ ይህም ዕድገት ከፍተኛ መነቃቃትንና ተነሳሽነትን በመቀስቀስ የሀገር ውስጥና የውጭ ኢንቨስትመንት እንዲጠናከር ዕድል መፍጠሩን፣ በአንፃሩ ደግሞ በቀጣይ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ያሉ መሆኑን በጥልቀት ገምግሟል።

እንዲሁም ባለፉት 2 ዓመት ተኩል የወጭ ንግድ አፈፃፀም ከታቀደው በታች በመሆኑ በዚህ ረገድ ያለውን ውስንነት ለመፍታት የግብርናና ኢንዱስትሪ አምራች ዘርፍን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በተለይ የወጭ ምርቶች ላይ መረባረብ እንደሚጠይቅ አጽንኦት ሰጥቶታል።

የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ማስፋት፣ የገቢ መሰብሰብ አቅም ማሳደግ፣ የኑሮ ውድነት ችግርን ማቃለልና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ኮሚቴው ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ገምግሞ ቀጣይ የአፈጻጸም አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

በዚህም መሰረት የስካሁኑን ፈጣን ዕድገት ይበልጥ ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም በተሻለ የኤክስፖርት አፈፃፀም ለመድገም ከአሁኑ የዕድገት ደረጃ ጋር የሚመጣጠኑ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚያስፈልግ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አምኖበታል።

በዚህም መሰረት ፈጣን ዕድገቱ ዜጎችን አካታች በሆነ መልኩ ግለቱን ጠብቆ እንዲቀጥል የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች በሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ የአክስዮን ድርሻ እንዲኖራቸው ወስኗል።

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለረጅም ጊዜያት በሀገራቸው ልማት ለመሰማራት ያላቸውን ምኞት በማረጋገጥና የዕድገቱን ፍጥነት ይበልጥ ለማስቀጠል እንዲሁም እውቀትና የውጭ ምንዛሪ ካፒታል ያላቸው የውጭ ባለሃብቶች በዕድገታችን ላይ ተገቢውን አዎንታዊ ሚና እንዲጫወቱ ለማስቻል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔዎችን አሳልፏል።

እነዚህም መሰረት፦

• በመንግስት ይዞታ ሥር ያሉ በማምረት ወይም አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትም ሆነ በግንባታ ላይ የሚገኙ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ እንዲተላለፉ፤

• እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች እና የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት ትልቁን የአክስዮን ድርሻ መንግስት ይዞ ቀሪው አክሲዮን ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ባለሃብቶች እንዲተላለፍ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አቅጣጫ አስቀምጧል።

አፈፃፀሙም የልማታዊ መንግስት ባህሪያት በሚያስጠበቅ፣ የኢትዮጵያን ፈጣንና ተከታታይ ዕድገት በሚያስቀጥልና የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም በሚያረጋግጥ ሁኔታ እንዲመራ፤ ዝርዝሩ በባለሙያዎች ተደግፎ በጥብቅ ዲሲፒሊን ተግባራዊ እንዲደረግ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ወስኗል።

የኢትዮ-ኤርትራ ግንኙነት

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር ጥሪ አቅርቧል።

በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተውን ጦርነት በአፍሪካ ከተከሰቱ የድንበር ጦርነቶች ሁሉ ደም አፋሳሹ ሲሆን፣ ከሁለቱም ወገን በርካታ ሺህ የሰው ህይወት ሊጠፋ ችሏል፤ ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ የመኖሪያ ቀዬ ማፈናቀሉ መግለጫው አስታውሷል።

በሁለቱ ሀገራት መሃከል የተደረገው ጦርነት በሁለቱም ሀገራት ያሉ ቤተሰቦችን አፍርሷል፣ በድንበር አቅራቢያ የሚኖሩ ዜጎች ሁሌም ያለመረጋጋትና የስጋት ስነ-ልቦና ሰለባ አድርጓቸዋል፤ በድንበር አካባቢ በንግድ የሚተዳደሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩንም በመግለጫው ተብራርቷል።

በድምሩ ላለፉት 20 ዓመታት በሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ፈጥሯል ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፤ በመሆኑም የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ግንኙነት ምን ሊሆን ይችላል? የሚለው ጥያቄ የአብዛኛው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን እንዲሁም የዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ጥያቄ ሆኖ መቆየቱን አንስቷል።

ከጦርነቱ በኋላ በአፍሪካ አንድነት ድርጅትና በተባበሩት መንግስታት አደራዳሪነት የአልጀርሱ ስምምነት ቢደረግም ላለፉት 20 ዓመታት በሁለቱ ወንድማማች ሀገሮች መካከል ጦርነትም ሆነ ሰላም የሌለበት ሁኔታ መፈጠሩን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በመግለጫው አንስቷል።

የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ወደነበረበት ለመመለስ ላለፉት 20 አመታት የተደረጉ ሙከራዎች በሙሉ ውጤት አላመጡም ያለው ማእከላዊ ኮሚቴው፥ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ ሀገራት መካከል የዕውነት ሰላም ለማስፈን ከቀድሞው የተለየ አቋምና አካሄድ ያስፈልጋል ብሏል የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው።

“እኔ እበልጥ፣ እኔ እበልጥ የሚል ፉክክር ለሁለቱም ህዝቦች የሚፈይደው ነገር አይኖርም” ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፥ ከዚህም በተጨማሪ ለአፍሪካ ቀንድ ሀገሮችና አካባቢ የፖለቲካ ቀውስ መብረድና መረጋጋት ዘላቂው መፍትሄ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጤናማ ግንኙነት መመሥረት ነው ብሏል።

ይህን ባለማድረጉም በርካታ ለሁለቱ እህትማማች ሀገሮችም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ትልቅ ፋይዳ ያላቸዉ እድሎች አምልጠዋል ብሏል መግለጫው።

“የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ቀድሞም ቢሆን ወዳጅ ነን” ያለው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው፥ “በደም፣ በባህል፣ በቋንቋና በረጅም ጊዜ የጋራ ታሪክ የተሳሰርን ሕዝቦች ነን” ብሏል በመግለጫው።

በመሆኑም በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል የኢትዮጵያ መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት እና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ ለሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የወሰነና ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት የሚሰራ መሆኑን በመግለጫው አረጋግጧል።

የኤርትራ መንግስትም ተመሳሳይ አቋም በመውሰድ ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ የቀረበለትን የሰላም ጥሪ ተቀብሎ በሁለቱም ወንድማማች ህዝቦች መካከል ከዚህ በፊት የነበረውን አብሮነትና ሰላም ወደነበረበት ለመመለስና በቀጣይም ዘላቂነቱን ለመጠበቅ ለተግባራዊነቱ ያለማመንታት በቁርጠኝነት እንዲሰራ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ጠይቋል።

03/06/2018

በአዲስ አበባ ነባር የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች በሙሉ በሚቀጥለው አመት ቤት ያገኛሉ
• እስከ ሰኔ 30 ድረስም 70 ሺህ ቤቶች ይወጣሉ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ዛሬ መልካም ልማታዊ አስተዳደርን ማስቀጠልን ዓላማው ባደረገ የምክክር መድረክ ላይ እንዳስታወቀው፤ ሁሉም የ1997 ነባር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤትተመዝጋቢዎች በሚቀጥለው አመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ቤት ያገኛሉ።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊው አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ዛሬ በዚሁ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፤ እስከተያዘው የበጀት አመት መጨረሻ )ሰኔ 2010) ድረስ 70 ሺህ የ20/80 እና የ40/60 ቤቶችን ለነዋሪዎች ይተላለፋሉ።

በ2011 በጀት አመት ደግሞ 60 ሺ የ20/80 እና የ40/60 ቤቶች ለነዋሪዎች እንደሚተላለፉና ለዚህም ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ነው ያስታወቁት።

ቁጥራቸው 18 ሺህ የሚጠጋ የ40/60 ተመዝጋቢዎች መቶ በመቶ የሚጠበቅባቸውን ቁጠባ በማጠናቀቃቸው በተያዘው አመት መጨረሻ ሁሉም ተመዝጋቢዎች ቤቶቻቸውን ያገኛሉ ብለዋል አቶ ይድነቃቸው።

ግንቦት 24/2010 /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

02/06/2018

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳትን አስመልክቶ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አህመድ የተሰጠ መግለጫ

የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሀገር እና ህዝብ ያሉበትን ነባራዊ እውነታ እና በቀጣይም እንደ ሀገር ሊገጥም ይችላል ተብሎ የሚገመት አደጋን ለመከላከል በመደበኛው ህግ እና አሰራር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ የሚመርጥ አስገዳጅ አማራጭ ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት አመታት ባጋጠማት የፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲታወጅ ተደርጎል፡፡ ይህንን ተከትሎም በመንግስት ዘንድ በተከናወነው ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እና በተከታታይ በተወሰዱ እርምጃዎች ህዝቡ መንግስት ባለው ችግሮችን የመፍታት ፍላጎት እና አቅም ላይ ተስፋን ሰንቋል፤ በዚህም ምክንያት እራሱ ህዝቡ የሰላሙ ዘብ በመሆን ላለፉት ሁለት ወራት በሀገራችን አንጻራዊ የሰላም ንፋስ መንፈስ ጀምሯል፡፡

የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች

ዛሬ ያሉበትን እና ነገም የሚደርሱበትን ተፈጥሯዊ የህይወት ኡደት- ሰላማዊ የመሆኑን እንዴትነት ባለማመን ውስጥ መኖር በሰርክ ህይወታችንና በእድገት ስኬታችን ላይ የሚያስከትለው አሉታዊ ተጽእኖ እጅግ ብዙ ነው፡፡
ሀገራችን ገብታበት በነበረው ውስብስብ ቀውስ ሳቢያ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በማወጅ ነገሮች መስመር እንዳይስቱ እና መልሶ ለማረቅም እንዳያዳግቱ ውጤታማ ስራ መስራት ችሏል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጊዜያዊ መፍትሄ እንጂ መደበኛና ዘላቂ ሰላምን የሚያመጣ ባለመሆኑ መንግስትም ይህንኑ በመረዳት የሀገራችን እና የህዝቦቿ ሰላም ከውጫዊ አዋጅ እና ክልከላ ሳይሆን ከዜጎች ፍላጎትና የሰላም ወታደርነት የሚፍለቅ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በተደረጉት እንቅስቃሴዎችም በመላው ሀገራችን አንጻራዊ ሰላምን ማሰፈን ተችሏል፡፡ የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለነበርንበት ችግር ወቅቱ የሚጠይቀው አማራጭ ውሳኔ ሆኖ ቢያሻግረንም ለማደግ መለወጥ እንደሚታትር ታላቅ ህዝብ ደግሞ ያስከተላቸውና የሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች መኖራቸው አይካድም፡፡ በመሆኑም የረጅም ዘመን ታሪክ- አኩሪ እና በዘመን የተፈተነ የአብሮነት ልክ- የማይደራደርበት የሞራል ጥግ- ራሱን እና ሌሎችንም ጭምር የሚጠብቅበት ባህላዊ የሰላም መቀነቻ ድግ እና ትላንቱን ዘክሮ፣ ዛሬውን መርምሮ እና ነገውንም ተንብዮ ሀገር አድባሩን በሰላም የሚሞላ ህዝብ ላላት ድንቅ ሀገር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ከቆየችው በላይ ትቆይ ዘንድ አይገባትም፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ላለች የዲፕሎማቲክ፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መናገሻ ለሆነች ሀገር የአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቆይታን ለማብቃት የሚደረግ ጥረት እና የጋራ ርብርብ አንድምታው ብዙ ነው፡፡ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስለማንሳት እና ህዝቡንም ወደ መደበኛው የአስተዳደር፣ የህግ እና የፍትህ መስመር ስለመመለስ ሲያስብ አዋጁን ለማወጅ ካስገደዱት ተግዳሮቶች አንጻር ያለውን ችግር በተመለከተ የመፍትሄውን ቁልፍ በማግኘት በኩል ሙሉ እምነቱ ያለው በህዝቡ እና በህዝቡ ላይ ብቻ ነው፡፡
መንግስት እና ህዝብ አዋጁን በማንሳት የሀገራችንን ሰላም እና የዜጎችን ደህና ወጥቶ ደህና የመግባት መብት፣ ምኞት እና ጸሎት እውን ለማድረግ በሚታትሩበት ወቅት ጉዳዩን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመግፋት እና ዞረን ተዟዙረን የቀውስ አዙሪት ውስጥ እንድንዳክር ለማድረግ የሚጥሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ሊኖሩ የመቻላቸውን ነገር ለአፍታም ቢሆን ቸል ልንል አይገባም፡፡ መንግስትም ስጋቱን እንደ ስጋት የሚጋራው ቢሆንም እንደ ታላቅ ሀገር እና እንደ ኩሩ ህዝብ ከአስጊው ስጋት ይልቅ ከኩሩው ህዝብ እምነት ጋር በመደመር ነገን ብሩህ ለማድረግ መስራት የመንግስት ምርጫ ሆኗል፡፡

ህዝባችን በገዛ ፈቃዱ መዳፉ ውስጥ ያኖረውን ሰላም ከሌላ መዳፍ ውስጥ አኑሮ ያለፈቃዱ የሚሰጋ- ያገሩን ሰላም የሚያናጋ ሳይሆን የሰላሙ ዘብ ራሱ መሆኑን በማመን ሀገር- ቀኤውን ከቀውስ የሚጠብቅ እንደሚሆን መንግስት በጽኑ ያምናል፡፡
መንግስት በተለያዩ ጊዜያት የህዝባችን ጥያቄ ሆነው የቆዩ የተለያዩ ጉዳዮች ሁነኛ ምላሽ ያገኙ ዘንድ ያለመታከት ይሰራል፡፡ ከችግሮቹ ስፋት እና ጥልቀት አንጻር ህዝብ በሚፈልገው ልክ እና መጠን ለሁሉም ጥያቄዎች አሁናዊ ምላሽ ማግኘት አዳጋች ቢሆንም መንግስት የመጨረሻውን የፍጥነት እና የትጋት ልክ ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ሰማይ ስር ነገሮች ሁሉ መልካም እንዲሆኑ ከህዝቡ ጋር ይረባረባል፡፡

ምንም እንኳን ዛሬ ለነገ መሰረት የመሆኗ ነገር ባያጠያይቅም ዛሬ ሰላም መሆን ማለት ግን ነገም ሰላም ትሆናለች የሚል ዋስትናን አይሰጠንም፡፡ ነገ ሰላም የምትሆነው በሁላችንም ጥረት እና ዛሬ ላይ ለነገ በምንጥለው የፍቅር መሰረት ብቻ ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት ህዝብን እና ህዝብን ብቻ አምኖ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የማንሳት ውሳኔ ላይ ሲደርስ ህዝባችንም በሀገሩ ምድር ሁሉ ላይየሁሌም የሚሆነውን እና ከየሰዉ አእምሮ የሚመነጨውን ተፈጥሯዊ የሰላም አዋጁን በህብረት እንደሚያውጅ እምነቴ የጸና ነው፡፡ ይህ ሲሆን ብቻ በእርግጠኝነት ነገ ከዛሬ የተሻለች ትሆናለች፡፡ ሀገራችን እና ህዝባችን ዘላቂ ሰላም እና የማያቋርጥ ለውጥ መገለጫቸው እንዲሆን ካስፈለገ መተኪያ የሌለው የሁሉም ነገር መሰረት እና ካስማ ሰላም እና ሰላም ብቻ ነው፡፡

በዚህ ሀሳብ መነሻነትም ባለፉት ወራት በሀገራችን ታውጆ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተነሳ መሆኑን እያሳወኩ በቀጣይም የሀገራችን ህዝቦች፣ የፌዴራል እና የክልል የጸጥታ ሀይሎች፣ በየደረጃው የምንገኝ የፌዴራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች፣ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና አባሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች እና የሚድያ ሰዎች፣ የሀገራችን የቅርብ ወዳጆች እና አጋሮች፣ የሀገራችን ምሁራን እና የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ የሀገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለት የዚህች ሀገር ደግ ቀን እንዲነጋ በተለያዩ መንገዶች የበኩላችሁን እያደረጋችሁ ያላችሁ በውጪ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወገኖች… ከምንም በላይ ለዚህች ሀገር ብልጽግና እና ለህዝቦቿም ሰላም ቅድሚያ ሰጥተን በጋራ እንድንረባረብ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
"ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራ፣ ተከብራና በልጽጋ ለዘላለም ትኑር!"
“ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ”

ye Ginbot 20, beal 27gna Amet kirkos werda10 lay bepanal wuyiyit tkebre
21/05/2018

ye Ginbot 20, beal 27gna Amet kirkos werda10 lay bepanal wuyiyit tkebre

Address

Awash
POSTCODE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kirkos cherkos w10communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share