አዋሽ አርባ መዘጋጃ / Hawaash Qarba Magaalah Kalayto ku/Buxa

  • Home
  • Ethiopia
  • Awash
  • አዋሽ አርባ መዘጋጃ / Hawaash Qarba Magaalah Kalayto ku/Buxa

አዋሽ አርባ መዘጋጃ / Hawaash Qarba Magaalah Kalayto ku/Buxa የአዋሽ አርባ መዘጋጃ ቤት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ። ስለ ከተማችን የልማት እንቅስቃሴዎች፣ ወቅታዊ መረጃዎችና የአገልግሎት አሰጣጥ መረጃ የሚያገኙበት መድረክ።
✨ ለተሻለች አዋሽ አርባ!

imagine one day xiqsitta tan meqem abtoh egla ke awashe qarbah kalaytoh kutbeh buxa ita luk cattiimak yamaatuwa qusba sa...
27/07/2026

imagine one day xiqsitta tan meqem abtoh egla ke awashe qarbah kalaytoh kutbeh buxa ita luk cattiimak yamaatuwa qusba santi baritto aba gaba dagoytiti urruh uwwati cato aben !!

የ አዋሽ አርባ መዘጋጃ ከ Imagine one day ጋር በመተባበር ለ 2019 የ ትምሕርት ዘመን ለ አቅመ ደካማው ማሐበረሰብ የተደረገ የትመርት ቁሳቁስ ድጋፍ

01/07/2026

ርዕስ፡ የአዋሽ አርባ ከተማ መዘጋጃ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የማስከፈትና የመልማት ስራ እየጀመረ ነው።
​ለአዋሽ አርባ ከተማ ነዋሪዎች በሙሉ፣

​የከተማችንን የትራፊክ ፍሰት ለማቀላጠፍ፣ ለነዋሪዎች ምቹ የሆነ የመንገድ መሠረተ ልማት ለመዘርጋት እንዲሁም የከተማችንን ውበት ለመጠበቅ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል።
​ይሁን እንጂ፣ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ከጸደቀው የከተማ ፕላን ውጭ የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ማጥበብ፣ የሁለተኛ ደረጃ መንገዶችን መዝጋትና የህዝብን መተላለፊያ መንገድ መገደብ እንደተስተዋለ በምርመራ ተረጋግጧል። ይህ ተግባር የከተማዋን እድገት ከማደናቀፉም በላይ፣ በአስቸኳይ ጊዜ ለሚኖሩ አገልግሎቶች (እንደ አምቡላንስ፣ የእሳት አደጋ መከላከያ እና መሰል የድንገተኛ አገልግሎቶች) ተደራሽነት ትልቅ እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል።
​በመሆኑም የአዋሽ አርባ መዘጋጃ ቤት በህግ የተሰጠውን ስልጣን መሰረት በማድረግ፦
1. ​በከተማ ፕላን መሰረት የተቀመጡ የውስጥ ለውስጥ እና የሁለተኛ ደረጃ መንገዶችን የማስከፈት ስራ እንደሚጀምር ያሳውቃል።
2. ​ያለምንም ህጋዊ ፈቃድ መንገዶችን የዘጉ ወይም ያጠበቡ ነዋሪዎች፣ ጉዳዩ በመዘጋጃ ቤቱ እና በህግ አስከባሪ አካላት ከመታየቱ በፊት በአስቸኳይ መንገዶችን እንዲለቁ እናሳስባለን።
3.​ ቀጣይነት ያለው የከተማዋን የልማት ስራዎች ለማሳካት የመላው ከተማ ነዋሪዎች ድጋፍ ወሳኝ በመሆኑ፣ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን በመከላከል በኩል ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

​"የከተማችን ልማት የሁላችንም ግዴታ ነው!"

የዴንጊ ትኩሳትን ለመከላከል በከተማችን የተቀናጀ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ​በወረዳችን የተከሰተውን የዴንጊ (Dengue) በሽታ አምጪ ትንኞች መራቢያ ቦታዎችን ለማጥፋት ያለመ ሰፊ የጽዳት ዘመቻ ...
03/05/2026

የዴንጊ ትኩሳትን ለመከላከል በከተማችን የተቀናጀ የጽዳት ዘመቻ ተካሄደ
​በወረዳችን የተከሰተውን የዴንጊ (Dengue) በሽታ አምጪ ትንኞች መራቢያ ቦታዎችን ለማጥፋት ያለመ ሰፊ የጽዳት ዘመቻ በዛሬው ዕለት በአዋሽ አርባ ከተማ ተካሂዷል።

​በዚህ የጽዳት ዘመቻ ላይ፦
​የሀገር መከላኪያ ሰራዊት አባላት፣
​የአዋሽ አርባ ወጣቶች ቡድን፣
​የከተማው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ነዋሪዎች በንቃት ተሳትፈዋል።
​የአዋሽ አርባ ከተማ መዘጋጃ ቤት ኃላፊ ወጣት ኡመር ሁሴን በዘመቻው ላይ ተገኝተው እንደገለጹት፤ በሽታውን ለመከላከል ዋነኛው መንገድ የትንኝ መራቢያ የሆኑ የቆሙ ውሃዎችን ማድረቅ እና አካባቢን በንጽህና መጠበቅ በመሆኑ፣ ይህ የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስበዋል።
​ለከተማችን ጤና እና ውበት በጋራ ስለቆማችሁ ለዘመቻው ተሳታፊዎች በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው።
​ጤናማ አካባቢ ለጤናማ ማህበረሰብ!
​ #አዋሽአርባ #የጽዳትዘመቻ #የዴንጊመከላከል #ኡመርሁሴን #ጤና

05/03/2026

ለከተማችን ነዋሪዎች በሙሉ የተላለፈ ጥሪ! 🏠✨
​የከተማችን መዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እና የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በዕቅድ ለመምራት እንዲያስችለው፤ የመኖሪያ ቤቶች የግብር ቆጠራ በልዩ ግብረ-ኃይል እያካሄደ ይገኛል።

​🔍 የቆጠራው ዋና ዓላማ፦
​የከተማችንን ነባራዊ የቤት ይዞታ መረጃ በትክክል ለማደራጀት፤
​ፍትሃዊ የግብር አሰባሰብ ሥርዓት ለመዘርጋት፤
​ለከተማችን ውበትና ዕድገት የሚውል ገቢን በጋራ ለማመንጨት ነው።

​🤝 የእርስዎ ትብብር ለስራችን ስኬት ወሳኝ ነው!
የግብረ-ኃይል አባላቱ ወደ መኖሪያ ቤትዎ በሚመጡበት ወቅት፦
1️⃣ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ይተባበሩ።
2️⃣ የይዞታ ማረጋገጫ (ካርታ/ደብተር) እና የግብር መክፈያ ሰነዶችን ዝግጁ ያድርጉ።
3️⃣ የግብረ-ኃይል አባላቱ የመዘጋጃ ቤቱን መለያ ማህተም ማድረጋቸውን ያረጋግጡ።

​💡 ማሳሰቢያ፦ ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን የከተማችንን ብርሃንና ልማት የመገንቢያ አቅም ነው።

​📲 ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ያጋሩ!
መረጃው ለሁሉም ነዋሪ እንዲደርስና ስራው በተቀላጠፈ ሁኔታ እንዲከናወን ይህንን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የዜግነት ድርሻዎን ይወጡ::

​"ከተማችንን በጋራ እናልማ!"

​🏢 የከተማው መዘጋጃ ቤት

የመከላከያ ሰራዊት ለህዝቡ ያለው ፍቅርና እንክብካቤ በተግባር!የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ደረጃ 2 ሆስፒታሉ ሰራተኞች እና ወጣት ኡመር ሁሴን (የመዘጋጃ ቤቱ ኃላፊ) ጋር በመሆ...
25/02/2026

የመከላከያ ሰራዊት ለህዝቡ ያለው ፍቅርና እንክብካቤ በተግባር!
የአዋሽ አርባ ውጊያ ቴክኒክ ትምህርት ቤት ደረጃ 2 ሆስፒታሉ ሰራተኞች እና ወጣት ኡመር ሁሴን (የመዘጋጃ ቤቱ ኃላፊ) ጋር በመሆን፣ በአቡነ ዮናስ አረጋውያን መርጃ ድርጅት በመገኘት መኖሪያ ቤቱን አጽድተዋል፤ ፀረ-ተባይ ርጭት አከናውነዋል፤ ከአረጋውያኑ ጋር ማዕድ በመጋራት የፍቅርና የአብሮነት ጊዜን አሳልፈዋል።

​እንደሚታወቀው መዘጋጃ ቤታችን ከዚህ ቀደም የኢፍጣር መርሃ ግብር በማዘጋጀት ማህበረሰቡን ሲያስተባብር መቆየቱ የሚታወስ ነው። ይህ ተግባርም ለወገን አጋርነት ያለንን ተከታታይ ቁርጠኝነት ያሳያል::

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ሌ/ኮ ጌታሰው እና የመዘጋጃ ቤት ኃላፊው ወጣቱ መሪ ኡመር ሁሴን በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው እንዳሉት፤ የመከላከያ ሰራዊታችን የህዝብ ልጅ እንደመሆኑ፣ በጦር ሜዳም ሆነ በሰላም ጊዜ ለህዝቡ በተለይም ለአረጋውያን ያለውን ክብርና እንክብካቤ በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

​ለህዝባችን ጥሪ፡
ይህንን አርአያነት ያለው የበጎ ፈቃድ ስራ በመደገፍና በመሳተፍ፣ አብሮነታችንን እናጠናክር። የአዋሽ አርባ ከተማ ነዋሪዎች እና ባለሃብቶች ለተቸገሩ ወገኖቻችን ከጎናቸው መሆናችንን እንግለጽ!
​ #የመከላከያሰራዊት #አዋሽአርባ #አብሮነት #አረጋውያን #በጎፈቃድ

የአዋሽ አርባ ከተማ መዘጋጃ ቤት የአፍጥር ፕሮግራም በአረጋውያን መርጃ ማዕከል! ​ዛሬ በአዋሽ አርባ ከተማ መዘጋጃ ቤት አዘጋጅነት፣ በአዋሽ አርባ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ከሚገኙ የሙስሊም...
21/02/2026

የአዋሽ አርባ ከተማ መዘጋጃ ቤት የአፍጥር ፕሮግራም በአረጋውያን መርጃ ማዕከል!

​ዛሬ በአዋሽ አርባ ከተማ መዘጋጃ ቤት አዘጋጅነት፣ በአዋሽ አርባ የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ከሚገኙ የሙስሊም አረጋውያን አባቶቻችን እና እናቶቻችን ጋር እጅግ ደስ የሚል የጋራ የአፍጥር (Iftar) ፕሮግራም አካሂደናል።

​ይህ የበረከት ፕሮግራም የተካሄደው በአዋሽ አርባ መዘጋጃ ኃላፊ በክቡር ወጣት ዑመር ሁሴን መሪነት ሲሆን፤ የከተማችን ቀና እና ታታሪ ወጣቶችም በቦታው ተገኝተው ከአረጋውያኑ ጋር ፍቅራቸውን እና ማዕዱን ተጋርተዋል።

​በዚህ የተከበረ ወር ከአረጋውያኑ ጋር ማዕድ መጋራት፣ የደስታቸው ተካፋይ መሆን እና ምርቃታቸውን መቀበል በራሱ ትልቅ ፀጋ ነው! የአዋሽ አርባ መዘጋጃ ቤት አረጋውያንን ማክበርና መንከባከብ የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን በማመን በቀጣይም መሰል በጎ ተግባራትን አጠናክሮ ይቀጥላል።
​አላህ ፆማችንን፣ ዱዓችንን እና በጎ ስራችንን ይቀበለን! 🕌🤲✨
​ #አዋሽአርባ #አፍጥር

Address

Awash Arba City
Awash

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አዋሽ አርባ መዘጋጃ / Hawaash Qarba Magaalah Kalayto ku/Buxa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share