13/10/2026
#ማስታወቂያ
ለU-12፣ U-15 እና U-17 ዓመት በታች የታዳጊዎች እግር ኳስ የ2019 ዓ.ም ውድድር ዓመት ለማካሄድ ዝግጅት ያጠናቀቅን ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ፕሮጀክቶች እና በግል ቡድን ያላችሁ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 14/02/2019 ዓ.ም ድረስ በሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።
የመመዝገቢያ መስፈርቶች፡-
ተጫዋቾች ከመስከረም 1 ቀን 2003 ዓ.ም በኋላ የተወለዱ መሆን አለባቸው
እድስ ያልተደረገ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ማቅረብ የሚችሉ
ከ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዱበት ካርድ ከሁለቱ አንዱን ማቅረብ የሚችሉ
በተጨማሪ ትክክለኛ የለደይት ካርድ፣ የክትባት ወረቀት፣ የ1ኛ ክፍል የሪፖርት ካርድ ይዞ መቅረብ ይቻላል።
ይህንን መስፈርት የሚያሟሉ ቡድን ያላችሁ አሰልጣኞች መረጃውን በሚገባ በማደራጀት የያንዳንዱ ተጫዋች ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለብቻ በማደራጀት እንዲያቀርቡ እናሳውቃለን።
መሳሰቢያ፡- ትምህርት የማይማር ልጅ በውድድሩ ላይ መሳተፍ አይችልም!!!
ለበለጠ መረጃ፡- 0935879990
0916064580