Mamush Zerfu

Mamush Zerfu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Mamush Zerfu, Public & Government Service, Addis Ababa, Awassa.

የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ***//***ሐምሌ 18/2018 ዓ/ም የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የሚሰጠውን መደበኛ የድህ...
25/07/2026

የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT Exam) የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ
***//***
ሐምሌ 18/2018 ዓ/ም

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 ዓ.ም የሚሰጠውን መደበኛ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና /National Graduate Admission Test/ ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ፈተናውን ለመውሰድ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ የድህረ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች በሙሉ ምዝገባ የሚካሄደው ከሀምሌ 15 – 25/2018 ዓ.ም ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከታች በተቀመጠው የመመዝገቢያ ሊንክ ገብታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ለፈተናውም አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን። የፈተና መስጫ ጊዜው ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል፡፡

የመመዝገቢያ ሊንክ፡- https://ngat.ethernet.edu.et

ማሳሰቢያ:-
ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ።

የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር (ሰባት መቶ ሀምሳ ብር) መሆኑን አውቃችሁ በቴሌ ብር በኩል በምዝገባው ወቅት የሚፈጸም ይሆናል።
ምዝገባው የሚከናወነው በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆን የፈተና ጣቢያውን በሚመለከት ግን ከምዝገባ በኋላ የተመዝጋቢ ቁጥሩ ታይቶ በስታንዳርዱ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ŗēşpęçţ culture!!
18/07/2026

ŗēşpęçţ culture!!

ዚዙ ተመልሷል  | ዚነዲን ዚዳን የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ።በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኝነት ቦታ በመጨረሻ ምላሽ አግኝቷል። ፈረንሳያዊ...
18/07/2026

ዚዙ ተመልሷል

| ዚነዲን ዚዳን የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኝነት ቦታ በመጨረሻ ምላሽ አግኝቷል።

ፈረንሳያዊው የቀድሞ ኮኮብ ቸጫዋችና ውጤታማው አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተሹሟል።

ቡድኑን ለመረከብ የሚያስችለውን ሙሉ ስምምነት ማድረጉም ተረጋግጧል።

ካለፉት ሁለት አመታት ጀምሮ ከተለያዩ ክለቦች የቅጥር ጥያቄዎች የቀረቡለት የነበረ ሲሆን ዚዙ ሳይቀበላቸው ቀርቷል።

በእነዚህ ሁለት አመታት ሙሉ ትኩረቱን የፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድንን የመምራት ፕሮጀክት ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ ነበር ተብሏል።

ዚዳን የቡድኑን የአሰልጣኞች ቡድን አባላትን ጨምሮ አስፈላጊ ዝግጅቶችን ያጠናቀቀ ሲሆን አሁን የቀረው የአሰልጣኝ ዲዲየ ዴሾን ስንብት ይፋ መደረግ ብቻ ነው ሲል ፋብሪዚዮ ያስነበበው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

15/07/2026

ታሪክ ተሰርቷል! አርጀንቲና እንግሊዝን በድንቅ ሁኔታ በመርታት የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ደርሳለች!

እንዴት ያለ እብድ ጨዋታ ነው! በዓለም ዋንጫው የግማሽ ፍፃሜ መድረክ ድንቅ ፉክክር ያስተናገደውና በታላቅ ቁጭት የታጀበው ጨዋታ በአርጀንቲና የ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው

55' — አንቶኒ ጎርደን እንግሊዝን መሪ ያደረገች ድንቅ ጎል አስቆጠረ! (1-0)

85' — ጨዋታው ሊጠናቀቅ 5 ደቂቃ ብቻ ሲቀረው ኤንዞ ፈርናንዴዝ አርጀንቲናን ወደ ጨዋታው የመለሰች ድንቅ ጎል አስቆጠረ! (1-1)

90+2' — በጭማሪ ሰዓት ላውታሮ ማርቲኔዝ የአርጀንቲና ደጋፊዎችን ያስፈነደቀችውን እና ወደ ፍፃሜው ያሳለፈችውን ወሳኝ የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አሳረፈ! (2-1)

ይህንን ተከትሎ የአሁኗ የዓለም ሻምፒዮን አርጀንቲና ዋንጫዋን ለማስጠበቅ በሚቀጥለው እሁድ ከጠንካራዋ ስፔን ጋር በፍፃሜው ጨዋታ ትፋለማለች።

ጭዋታውን እንዴት አያችሁት ?

⚽️⚽️⚽️

ጉርሻ Page

🌴🌴🌴

15/07/2026
ትምህርት ለትውልድ!!
13/07/2026

ትምህርት ለትውልድ!!

13/07/2026

«መንግሥት የሕዝቡን የኑሮ እውነታ በቁጥር ጨዋታ ከመሸፈን ይውጣ»

‎ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ

‎ | ​ባለፉት አምስት ዓመታት የሕዝቡን የኑሮ ስቃይና የመንግሥትን መዋቅራዊ ድክመቶች በቅርበት ሲታዘቡ መቆየታቸውን የገለጹት የፓርላማ አባል ዶክተር ደሣለኝ ጫኔ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መንግሥት ላይ ጠንከር ያሉ የትችትና የጥያቄ ጠይቀዋል።

‎ስድስተኛው የፓርላማ ዘመን አምስተኛ ዓመት ማጠቃለያ የመንግሥት ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ንግግር ያደረጉት የሕዝብ ተወካዩ፣ መንግሥት በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠሉትን የሰላም እጦቶችና የፖለቲካ ምኅዳሩን መጥበብ ችላ በማለት፣ በኢኮኖሚ ስኬት ስም የቁጥር ጨዋታዎችን እያቀረበ ሕዝብን እያደናገረ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

‎በተለይም የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመጣው ሰማይ የነካ የዋጋ ግሽበት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን የመግዛት አቅም ያሳጣና መካከለኛውን የኅብረተሰብ መደብ ያጠፋ ስውር ረሃብ መውለዱን ገልጸዋል።

‎​በትምህርት ዘርፍ በኩል የታየውን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ92 በመቶ መውደቅ ሲሉ የገለጹት ዶክተር ደሣለኝ፣ ይህ አሳሳቢ ውጤት የመንግሥትን የትምህርት ሥርዓት መዋቅራዊ ኪሳራ የሚያሳይ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስትሩ ሊጠየቁበት ይገባል ብለዋል።

‎አያይዘውም በሀገሪቱ ሰብአዊ ቀውስ እያለ የመረጃ ማጥራት በሚል ሰበብ የእርዳታ ፈላጊዎች ቁጥር ወደ 2.3 ሚሊዮን ዝቅ ተደርጎ መቅረቡ እውነታውን የማይወክል የፖለቲካ ቁጥር ማሳመሪያ ነው ሲሉ ነቅፈዋል።

‎ተወካዩ እንደ መፍትሔ ያቀረቡት መንግሥት ትኩረቱን ከኮሪደር ልማትና ከሪዞርቶች ግንባታ በመቀነስ፣ ወደ መሠረታዊ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ወደ ማኅበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሞችና ሁሉንም የታጠቁ ኃይሎች ያካተተ እውነተኛ ብሔራዊ የፖለቲካ ድርድር ላይ እንዲያደርግ ነው።

‎በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ችግሮችን በኃይል ከመፍታት ወጥተው፣ ሕዝቡ በአዲሱ የ2019 ዓመተ ምህረት በተግባር ሊያየው የሚችለውን ግልጽ የሰላም የጊዜ ሰሌዳና ቁርጠኝነት እንዲያብራሩ በይፋ ጠይቀዋል።

‎Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን )

‎ #ጌጡ

13/07/2026

Address

Addis Ababa
Awassa

Telephone

+251926318683

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mamush Zerfu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share