Gofa zone pp youth league office

Gofa zone pp youth league office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gofa zone pp youth league office, Political organisation, Awassa.

የመሎ ኮዛ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወጣቶች ክንፍ የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አካሄደሐምሌ 24/2018 ዓ.ምበጎፋ ዞን በመሎ ኮዛ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈ...
01/08/2026

የመሎ ኮዛ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወጣቶች ክንፍ የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አካሄደ

ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም

በጎፋ ዞን በመሎ ኮዛ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወጣቶች ክንፍ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አካሂዷል ።

የግምገማ መድረኩን የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙኔ በትሶ ያስጀመሩት ስሆን የወጣቶችን አደረጃጀት በማጠናከር ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ አቶ አየለ አማሬ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ሪፖርት እና የ2019 ዓ.ም ጠቋሚ ዕቅድ አቅርበው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል ።

በውይይቱም በቀጣይ በትኩረት ሊሰሩ ሚገቡ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ተደረሶ መድረኩ ተጠናቋል ።

‎የዛላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ‎‎ሐምሌ፦ 24/2018 ዓ.ም (የዛላ ወረዳ ብልጽግና ፓር...
01/08/2026

‎የዛላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ ውይይት አካሄደ

‎ሐምሌ፦ 24/2018 ዓ.ም (የዛላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ)

‎የዛላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸምን በመገምገም ለ2019 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ዕቅዶችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አካሂዷል።

‎የዛላ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወንድም ጎጃሜ ጎላ እንደገለጹት ወጣቶች በፓርቲ፣ በልማት፣ በሰላምና በአገር ግንባታ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተጠናከረ መልኩ መወጣት እንደሚገባ በማሳሰብ፣ በ2019 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትጋትና በአንድነት እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

‎የዛላ ወረዳ ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወንድም መምህሩ ማልዳዬ በበኩላቸው ወጣቶች በተለያዩ የልማትና የበጎ ፈቃድ ተግባራት በንቃት በመሳተፍ ለማህበረሰቡ አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።

‎በመጨረሻም ተሳታፊዎች የ2019 ዓ.ም ዕቅድን በተጠያቂነትና በትብብር በመተግበር የተሻለ ውጤት ለማምጣት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል።

የደምባ ጎፋ  ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የ2018 ዓ/ም ግምገማ እና የ2019 ዓ/ም ፈፃሚ መድረክ አካሄደ ‎ሣውላ፣ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም ‎የደምባ ጎፋ ወረዳ ብልጽግና ...
30/07/2026

የደምባ ጎፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የ2018 ዓ/ም ግምገማ እና የ2019 ዓ/ም ፈፃሚ መድረክ አካሄደ

ሣውላ፣ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም

‎የደምባ ጎፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የ2018 ዓ/ም አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 ዓ/ም ፈፃሚ መድረክ ያካሄዱ ሲሆን የደምባ ጎፋ ወረዳ ረዳት መንግስት ተጠሪ እና ፖለትካና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚልክያስ ቡኬ መድረኩ ላይ ተገኝቶ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

‎አቶ ሚልክያስ ቡኬ ወጣቱ በማህበራዊ፥በፖለትካ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሆኖ በመንቀሳቀስ ሀገርን የመገንባት እና የማስቀጠል ኃላፊነት እንዳለበት ገልጿል።

‎ወጣቶች በማህበራዊ፣በፖለትካ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ሀገርን ማስቀጠል የወጣቶች ድርሻ ከፍ ያለ መሆኑን ጠቁመው ወጣቶች በዬትኛውም ጊዜ የተገኙ ዕድሎችን ተጠቅመው ሀገርን ማሻገር አለባቸው ሲሉ አስረድተዋል።
‎​

‎የደምባ ጎፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብንያም ካሌብ ወጣቶች የሀገር ባለቤት ስለሆኑ ሀገሪቱ ላይ እየተመዘገቡ ያሉ በሁሉም ለውጦች፣ በልማት ሥራዎችና፣ በሀገር ግንባታ ላይ የላቀ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል።

‎አቶ ብንያም ካሌብ አክለው ለውጥ በወጣቶች ንቁ ተሳትፎ የሚመጣ ውጤት መሆኑን ጠቅሰው ለለውጡ መምጣት ዋና ተዋናዮች ወጣቶች ስለሆኑ ጊዜ አይበቃኝም በሚል ስሜት በንቃትና በመነሳሳት ከጠባቂነት ወጥተው በራስ መተማመን ውስጥ ሆነው በሁሉም አቅጣጫ የሚጠበቅባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት እንድወጡ አሳስበዋል።

‎​ለሀገር ግንባታ የሚደረገው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን የወጣቱን አቅም በአግባቡ መጠቀም እና ማደራጀት ወሳኝ መሆኑም በመድረኩ ተመላክቷል።

‎እንዲሁም ከልማት ማህበር ተሳቶፎ አንስቶ አስከ ዓለም አቀፍ ድጅታል ስራዎችን በተገቢው መጠቀም መጪውን ዘመንን ወስነው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎ወጣቶች ክንፍ በ2018 ዓ/ም የተከናወኑ ተቋማዊ ተግባራትን መነሻ በማድረግ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በዝህም በውጤት የታጀቡ ጉዳዮችን በማጠናከር እና በቀጣይነት ትኩረት የሚሹ የወጣቱ የኢኮኖማ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ስራዎችን በማጎልበት መሥራት እንደሚገባ ተገልጾ መድረኩ ተጠናቋል።

‎የደምባ ጎፋ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት



በላሃ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም በጎፋ ዞን ላሃ ...
29/07/2026

በላሃ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ

ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም

በጎፋ ዞን ላሃ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወጣቶች ክንፍ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ አካሂዷል ።

መድረኩን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የላሃ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪና ፖለቲካና የህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ወንድም ታረቀኝ ጎፋ እንዳሉት ወጣቱ በኢኮኖሚ ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ ተሳትፎ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የማይተካ ሚና የተጫወቱ መሆኑን በማንሳት አድናቆታቸውን ገልጸው በ2019 ዓመትም በታቀደው ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ተሳትፎ በማድረግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትና በለሎች ዕቅዶች አፈጻጸም ላይ በመድገም የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ በመድገም የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።

የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ወንድም ሙሉቀን ማስረሻ የ2018 ዓ.ም አፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ።

በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ ተግባራት ፣ ጠንካራ ጎኖች ፣ የታዩ ክፍተቶችና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች በስፋት ተዳሰዋል ።

በዚህም የወጣቶች ክንፍ ለብልጽግና ስኬት የማይተካ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ በቀጣይም ለውጡን በባለቤትነት እንዲመሩ ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠር ጽህፈት ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል ።

በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አካሄደወጣቱ በሁሉም ዘርፍ ተሳታፊ በመሆን ሀገርን የመገንባት ሚናውን ማጠናከር እንዳለበት ተገለጸበጎፋ ዞን ...
27/07/2026

በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አካሄደ

ወጣቱ በሁሉም ዘርፍ ተሳታፊ በመሆን ሀገርን የመገንባት ሚናውን ማጠናከር እንዳለበት ተገለጸ

በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ የ2019 ፈጻሚ ማዘጋጃ መድረክ አካሄደ

​በሁሉም ዘርፍ የወጣቱ አመራር ተሳታፊ በመሆን ሀገር ገንቢና ጠንካራ ወጣት በመገንባት ረገድ የሚጠበቅበትን ሚና በይበልጥ ሊጫወት እንደሚገባ ተጠቆመ።
​ይህን የተናገሩት በውይይቱ ተገኝተው መድረኩን የመሩት የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ይሁን ደምሴ ናቸው።

አቶ ይሁን አክለውም ወጣቱ የሀገሪቱ የነገ ተረካቢ ብቻ ሳይሆን የዛሬ ባለቤትም በመሆኑ፣ በልማት፣ በሰላም እና በህገ-መንግስታዊ ስርአቱ ግንባታ ላይ ያለው ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

​ለሀገር ግንባታ የሚደረገው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን የወጣቱን አቅም በአግባቡ መጠቀም እና ማደራጀት ወሳኝ መሆኑም በመድረኩ ተመላክቷል።

በውይይቱ ተገኝተው መድረኩን የመሩት የዞኑ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ይሁን ደምሴ በሁሉም ዘርፍ የወጣቱ አመራር ተሳታፊ በመሆን ሀገር ገንቢ ጠንካራ ወጣት በመገንባት ሚናውን በይበልጥ መጠቀም አለበት

እንዲሁም ከዞኑ ልማት ማህበር ተሳቶፎ አንስቶ አስከ ዓለም አቀፍ ድጅታል ስራዎችን በተገቢው መጠቀም መጪውን ዘመንን ወስነው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የዞኑ ወጣቶች ክንፍ በ2018 ዓ/ም የተከናወኑ ተቋማዊ ተግባራትን መነሻ በማድረግ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በዝህም በውጤት የታጀቡ ጉዳዮችን በማጠናከር እና በቀጣይነት ትኩረት የሚሹ የወጣቱ የኢኮኖማ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ስራዎችን በማጎልበት መሥራት ይገባል ሲሉ የዞኑ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ በሪፖረታቸው ገልጸው ውይይቱ ተጠናቋል።

የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

የበቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከሻምባራ ቀጠና ወጣቶች ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሄደ ሰኔ 27/ 2018 ዓ.ም (የበቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግ...
04/07/2026

የበቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ከሻምባራ ቀጠና ወጣቶች ጋር የንቅናቄ መድረክ አካሄደ

ሰኔ 27/ 2018 ዓ.ም (የበቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት)

በጎፋ ዞን የበቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት በከተማዋ በሚገኘው የሻምባራ ቀጠና ወጣቶች ጋር ወቅታዊና ስልታዊ በሆኑ አገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሰፊ የውይይትና የንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

ይህ መድረክ የተዘጋጀው የወጣቱን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የአመለካከት አንድነትን ለመፍጠር እና ወጣቱ በአካባቢው የልማትና የሰላም ሥራዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚና እንዲጫወት ለማስቻል ነው።

መድረኩን የመሩት የበቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ፍሬው ጎሳዬ ገለጻ እንደሰጡት፣ ከውይይቱ የተወሰዱ ዋና ዋና የትኩረት ነጥቦች አንጻር ወጣቶች የአሁኗ ኢትዮጵያና የነገዋ የበለጸገች አገር ተረካቢ ትውልድ በመሆናቸው፣ ለአካባቢያቸው አስተማማኝ ሰላምና ደህንነት በንቃት ዘብ መቆም እንዳለባቸው መመሪያ ሰጥተዋል።

አያይዘውም ወጣት ፍሬው በማንኛውም አጋጣሚ በወጣቶች መካከል የሚፈጠሩ ልዩነቶችንና አለመግባባቶችን በባህላዊ እሴቶችና በሰለጠነ የውይይት መድረክ ብቻ የመፍታት ልምድ ሊጎለብት እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል።

መንግሥት ለወጣቱ ዘርፈ-ብዙ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የአቅም ግንባታና ልዩ ልዩ የልማት ፓኬጆችን እያወረደ ይገኛል። ወጣቶች እነዚህን ዕድሎች በመጠቀም ሁለንተናዊ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባ ተብራርቷል።

ከዚህ በኋላ ወጣቱ የአስተሳሰብ ሳንካ (ችግር) ባለባቸው፣ የሰላም ስጋት በሚፈጥሩና አገርን ወደኋላ በሚጎትቱ ማናቸውም አጀንዳዎች ላይ መሰለፍ እንደሌለበት በጥብቅ ተመልክቷል።

“ይህ ድል የጋራ ጥረታችን ውጤት ነው።” ክቡር አቶ ጋሻያለው ገላ​የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ጋሻያለው ገላ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት​ለተከበራችሁ የዞናችን ...
22/06/2026

“ይህ ድል የጋራ ጥረታችን ውጤት ነው።” ክቡር አቶ ጋሻያለው ገላ

​የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ጋሻያለው ገላ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት
​ለተከበራችሁ የዞናችን ነዋሪዎች፣ የፓርቲያችን አመራርና አባላት፣ እንዲሁም ለመላው ሕዝብ፤ አስተላልፈዋል።

​በመጀመሪያ፣ በሀገራችን ብሎም በዞናችን የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ በሰላም፣ በዲሞክራሲያዊ መንገድ እና በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎ በማጠናቀቃችን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ።

በምርጫው የብልጽግና ፓርቲን መርጣችሁ ድል ላጎናጸፋችሁ የዞናችን ሕዝቦች፣ ላሳያችሁት የላቀ የፖለቲካ ብስለት እና ለሰጣችሁት ታላቅ አደራ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

​ለአመራራችንና ለአባላቶቻችን እንኳን ደስ አለን
​ይህ ድል የጋራ ጥረታችን ውጤት ነው። በየደረጃው የምትገኙ አመራሮችና አባላት፣ የህዝቡን ስሜት ተረድታችሁ ላደረጋችሁት ያልተቋረጠ ጥረት እና በምርጫ ሂደቱ ወቅት ላሳያችሁት ዲሲፕሊን ምስጋና ይገባችኋል።

በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ አሸንፈን የምንመሰርተው መንግስትና የምንቀበለው ኃላፊነት "ለማረፊያ" ሳይሆን "ለስራ መነሻ" ነው። በቃል የገባነውን የልማትና የመልካም አስተዳደር አጀንዳዎች ለመፈጸም ዝግጁ እንሁን።

​በምርጫው የተሳተፋችሁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ለዲሞክራሲያዊ ስርአታችን ግንባታ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ እና ለሰላማዊ ተሳትፏችሁ ክብር ይገባችኋል። ምርጫው ተጠናቋል፤ አሁን የጎፋ ዞን የጋራ ግንባታ ዘመን ነው።

የዞናችንን ብልጽግና ለማረጋገጥ፣ ገንቢ በሆኑ ሀሳቦች ላይ ከእናንተ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር አብረን ለመስራት የምንገኝበትን በር ክፍት አድርገን እንጠብቃለን።

​ለመረጡን እና ላልመረጡን የዞናችን ነዋሪዎች
​የጎፋ ዞን የሁላችንም ነች። የመረጣችሁን ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፣ ላልመረጣችሁኝ ወገኖቼ ደግሞ ይህ የዲሞክራሲ ውበት መሆኑን ላስታውስ እወዳለሁ።

እኛ የምንመሰርተው መንግስት የመራጭና ያልመረጠ ሳይል፣ ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት የሚቆም፣ የሁሉንም ጥያቄ የሚመልስ እና የሁሉንም ክብር የሚያስጠብቅ መንግስት ይሆናል። የብልጽግና ጉዟችን ስኬታማ የሚሆነው በእናንተ ተሳትፎና ሂሳዊ አስተያየት ነው።

​ባለፈው የሁለት ቀናት የምክክር መድረካችን እንዳየነው፣ የዞናችን የልማት ፍላጎት ከፍተኛ ነው። እንደ መንግስት የህዝብን አቤቱታ በቅጽበት የሚመልስ፣ ግልጽና ተጠያቂነት ያለው ተቋማዊ አሰራር እንዘረጋለን።

​ሴቶችና ወጣቶች የለውጡ ባለቤቶች ናችሁና የውሳኔ ሰጪነት ሚና በማሳደግ እና የወጣቶችን የቴክኖሎጂ አቅም በመጠቀም፣ ዘመናዊና የበለጸገ ዞን እንገነባለን።

የተሰጠን አደራ ከባድ፣ ጉዞአችን ግን ብሩህ ነው። በህዝብ የተወደደ፣ በህግ የበላይነት የሚመራ እና የጋራ ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ስርዓት ለመገንባት ዛሬ ቃል እንገባለን። እባካችሁ፣ እንደወትሯችሁ ሁሉ በሰላም፣ በአንድነትና በታታሪነት ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

​ለጎፋና ለኢትዮጵያ ብልጽግና በጋራ እንተጋለን!
አመሰግናለሁ።

ክቡር ​አቶ ጋሻያለው ገላ
የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ

ምንጭ የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ሚዲያና ህዝብ ግንኝነት ዘርፍ!

ትላንት በሀገራዊ ምርጫ የሴቶችና የወጣቱ ሚና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታችን ፈር ቀዳጅ እንደሆነው ሁሉ ነገም በስርዓተ መንግስት ምስረታውም ሂደት አይተኬ ሚናቸውን ይወጣሉአቶ ቦረና ቦላዶበጎፋ...
22/06/2026

ትላንት በሀገራዊ ምርጫ የሴቶችና የወጣቱ ሚና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታችን ፈር ቀዳጅ እንደሆነው ሁሉ ነገም በስርዓተ መንግስት ምስረታውም ሂደት አይተኬ ሚናቸውን ይወጣሉ
አቶ ቦረና ቦላዶ
በጎፋ ዞን ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

የምርጫው ውጤት ማግስት ለአዲሱ የአገልጋይነት ዘመን መጀመሪያ ምዕራፍ ላይ እንገኛለን። የምንመሰርተው መንግስት፣ የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች በፈጣን ምላሽ ለመመለስ የተዋቀረ፣ ለውጤት የሚተጋ እና ተጠያቂነትን የተላበሰ እንዲሆን እንሰራለን።

ለ​ብቃትና ለስነ-ምግባር ከፍ ያለ ትኩረት በሚሰጥበት በዚህ ወቅት በየደረጃው ያሉ ለመንግስትና ለፓርቲ ስራዎች ቀልጣፋና የዘመነ አገልግሎት መስጠት የሚችል የለውጥ መሪዎችን እንደሆነ እንረዳለን።

​ለሕዝብ ቅርብ የሆነ አስተዳደር አለን፤ መንግስታችን ከቢሮ ወጥቶ ወደ መሬት የወረደ ነው። በየአካባቢው ያሉ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታዎች እና የጤና አገልግሎቶች በአጭር ጊዜ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲውሉ ቅድሚያ ሰጥተን እንሰራለን።

የተፎካካሪ ፓርቲዎች ገንቢ ሃሳቦች እና የምሁራን ጥናቶች በመንግስት ፖሊሲ ቀረጻ ውስጥ ቦታ ይኖራቸዋል። የብልጽግና ጉዟችን ስኬታማ የሚሆነው የሁላችንንም ድምጽና ፍላጎት ባካተተ መልኩ ሲመራ ብቻ ነው ብለን እናምናለን።

​በዚህ አዲስ የመንግስት ምስራታ ምዕራፍ፣ የጋራ ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመቀየር፣ የሕዝብን እምነት በስራ ለማረጋገጥ እና የዞናችንና የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን ለማድረግ ዝግጁ ነን።

​እውነታን በግልጽ በማቅረብ ከተግባቦት እየደረስን፣ የሕዝብን አንድነት በመጠበቅ እና የመረጃ ጥራትን በማረጋገጥ የዲጂታል ዘመቻችንን እናጠናክራለን ሚዲያዎቻችን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያንጸባርቁ እንዲሆኑ እንሰራለን።

​የፓርቲያችን ብልጽግና ራዕይ ኢትዮጵያን በዲሞክራሲ፣ በኢኮኖሚ ልማት እና በመልካም አስተዳደር ለአፍሪካ ተምሳሌት ማድረግ ነውና እጅለእጅ መያያዝ ግድ ይለናል።

በዞናች​ የማይናወጥ የህግ የበላይነት በማስከበር ሙስናንና ብክነትን በመዋጋት፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል ፍትሐዊነትን በማረጋገጥ ለሕዝብ የገባነውን ቃል እንጠብቃለን።

ወጣቶች እና ሴቶች በፓርቲ መዋቅር ውስጥ ብቻ ሳይሆን፣ በማህበረሰብ ልማት እና በአስተዳደር እርከኖች ውስጥ የውሳኔ ሰጪነት ሚና እንዲኖራቸው ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አይነተኛ ድርሻ አለው።

የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በአንድ ወቅት ወይም በአንድ ምርጫ የሚጠናቀቅ ሳይሆን፣ የትውልድ ቅብብሎሽ እና የባህል ግንባታ ሂደት ነው። ወጣቶች እና ሴቶች በዚህ ሂደት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎ የዴሞክራሲን መሰረት የሚያጸና ዋስትና ይሰጠናል

በመጨረሻም፣ የተሰጠንን አደራ በታማኝነት በመወጣት፣ ወደፊት የምንሄድበት የብልጽግና ጉዞ የሁላችንም ተሳትፎ የሚታይበት እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ። ኢትዮጵያ በጋራ ጥረታችን ታፍራና ተከብራ ትኖራለች።

ብልጽግና አሸንፏል !!
​ጎፋም ጥረት እድገቷን ታረጋግጣለች!
አመሰግናለሁ።

አቶ ቦረና ቦላዶ
በጎፋ ዞን ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

ምኖጭ የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ሚዲያና ህዝብ ግንኝነት ዘርፍ!

በጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት የታገዘ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የስርዓተ መንግስት ምስረታን በጽኑ መሰረት መትከል ያስችላል። አቶ ይሁን በላይ በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃ...
22/06/2026

በጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት የታገዘ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የስርዓተ መንግስት ምስረታን በጽኑ መሰረት መትከል ያስችላል። አቶ ይሁን በላይ በጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

በምርጫ እና በድህረ ምርጫ ወቅት የታየው የዴሞክራሲ ስርዓት ነገም ለጠንካራ ስርዓተ መንግስት ምስረታ የውስጠ- ፓርቲ አደረጃጀቶቻችን አይነተኛ ሚናቸውን ይወጣሉ።

አገራችን በታሪካዊ የለውጥ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። የፓርቲያችን አደረጃጀት ለጠንካራ ስርዓተ መንግስት ምስረታ ያለው ሚና ወሳኝ ነው።

የፓርቲው አቅም የሚለካው በስትራቴጂያዊ እቅዱ ብቻ ሳይሆን፣ በመሬት ላይ ባለው የአደረጃጀት ጥንካሬ መሆኑን አባላቱ በምርጫም ወቅት ሆነ በድህረ ምርጫ ወቅት አስመስክሯል።

አደረጃጀታችን በአባል ላይ የተመሰረተ ነውና እያንዳንዱ አባል በስርዓተ መንግስት ምስረታ ሂደቱ ውስጥ ያለውን ፋይዳ እንዲገነዘብ በማድረግ፣ ንቁ ተሳትፎ እንዲኖረው መስራት ይጠበቅብናል።

​ለፓርቲያችን አመራሮች እና አባላት በስርዓተ መንግስት ምስረታ ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችሉ ስልጠናዎችን እና ውይይቶችን በየደረጃው እንቀጥላለን።

ጠንካራ ስርዓተ መንግስት የሚመሰረተው በጠንካራ የውስጥ ዲሲፕሊን የታነፀ ፓርቲ ነው። የአሰራር ስርዓታችንን በአግባቡ በመከተል፣ ለሌሎች አርአያ መሆን ይኖርብናል።

የፓርቲያችን አላማ የህዝብን ጥቅም ማስጠበቅ እና ሀገራዊ ስርዓትን ማፅናት ነው። ይህን ታላቅ አላማ ለማሳካት የግል ፍላጎትን ለጋራ ግብ ማስገዛት ተገቢ ነው።

አደረጃጀታችን የፓርቲያችን የጀርባ አጥንት ነው። አደረጃጀቱ ሲጠናከር የፓርቲያችን አቅም ይጎለብታል፤ የሀገራችንም የስርዓተ መንግስት ምስረታ በጠንካራ መሰረት ላይ ይገነባል። ሁላችሁም በየምትገኙበት እርከን ለዚህ አላማ እንዲሰሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ።

ብልጽግና አሸንፏል !!
​አብረን እንገንባ፣ አብረን ኃላፊነታችንን እንወጣ!

አቶ ይሁን ደምሴ
የጎፋ ዞን ​የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ

ምንጭ የጎፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ህዝብ ግንኝነት ዘርፍ!

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ  ሚካኤል ዋዳ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ለክልሉ ወጣቶች የምስጋና መልዕክት አስ...
03/06/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሚካኤል ዋዳ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሠላም መጠናቀቅ አስመልክቶ ለክልሉ ወጣቶች የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

ክቡራንና ክቡራት የክልላችን ወጣቶች፤
ሀገር ወዳድ የክልላችን ሕዝቦች እና መላው የፓርቲያችን አመራሮችና አባላት በሙሉ!

ሀገራችን ኢትዮጵያ የጀመረችውን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ለማሳካትና የህዝባዊ ሉዓላዊነት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ የሆነው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ፣ ነፃ፣ ፍትሃዊ እና በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ባገኘበት መልኩ ተጠናቋል። ይህ ታሪካዊ ሀገራዊና ክልላዊ ድል እውን እንዲሆን ግንባር ቀደም ሚና ለተጫወታችሁት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች በክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ስም ከልብ የመነጨ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ውድ የክልላችን ወጣቶች፤ እናንተ ሀገራችን ወደ ተሻለ የዴሞክራሲ ምዕራፍ ለመሸጋገር በምታደርገው ጥረት ውስጥ ያላችሁን ጉልህ ድርሻ በተግባር አሳይታችኋል። ከምርጫው አስቀድሞ በነበረው ሂደት በመራጮች ምዝገባ ላይ በንቃት በመሳተፍ፣ የምርጫ ስነ-ምግባር ደንቦችን በማክበር፣ እንዲሁም የምርጫውን ሂደት ለማወክ በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች አማራጮች የሚሰራጩ የሀሰት መረጃዎችን በማምከን ያበረከታችሁት አስተዋፅኦ የላቀ ነው።

ምርጫው በድምፅ መስጫ ጣቢያዎች በሰላም፣ በዲሞክራሲያዊ መንገድ እና የዜጎችን ሰብአዊ መብቶች ባከበረ መልኩ እንዲካሄድ ቀንና ሌሊት ሳትሰለቹ ላደረጋችሁት ክትትል፣ ለታየው የወጣትነት ጨዋነትና ሀገራዊ ኃላፊነት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ወጣቶች ክንፍ ታላቅ ክብር አለው።

የክልላችን ወጣቶች ለሀገራችሁ ሰላም፣ ልማት እና ዴሞክራሲያዊ ሂደት ያላችሁን ሚና በመገንዘብ ላሳያችሁት ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ ቁርጠኝነትና የጋራ ትብብር ያደረጋችሁት መስዋዕትነት በታሪክ የሚዘከር ነው። ይህንን የነቃ ተሳትፏችሁን እና ሀገራዊ ኃላፊነታችሁን በቀጣይም በክልላችን ሁለንተናዊ ብልፅግና እና የሰላም ማስከበር ስራዎች ላይ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የምርጫው የመጨረሻ ውጤት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በይፋ እስከሚገለጽ ድረስ ወጣቱ ትውልድ እንደተለመደው ሁሉንም አሰራር በማክበርና በመታገስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲወጣ እናሳስባለን።

ኢትዮጵያውያን መርጠዋል ! ኢትዮጵያም አሸንፋለች!

የክልላችን ወጣቶች ተሳትፎ ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን ዋስትና ነው!

ሚካኤል ዋዳ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ የወጣቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

Address

Awassa

Telephone

+251930619796

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gofa zone pp youth league office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share