03/09/2026
የመሀል ክፍለ ከተማ የሥራ፣ አሠሪና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማዋ ባለፉት 2 ወራት የተከናወነውን የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም ገምግሟል
ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም | ሀዋሳ
የመሀል ክፍለ ከተማ የሥራ፣ አሠሪና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማዋ ባለፉት 2 ወራት የተከናወነውን የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም የገመገመ መድረክ አካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ የሀዋሳ ከተማ ሥራ፣ አሠሪና ሠራተኛ መምሪያ ኃላፊ ክቡር አቶ ሽታ ኤብሶ፣ የሀዋሳ ከተማ ሥራ፣ አሠሪና ሠራተኛ መምሪያ ም/ኃላፊና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ታምሬ ተፈራ፣ የመሀል ክፍለ ከተማ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሐንስ ኤርምያስ፣ የክፍለ ከተማዋ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራ ቴክኒክና ስትሪንግ ኮሚቴ አባላት ተሳትፈዋል።
በግምገማው ወቅት የ2 ወራቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈጻጸም በዝርዝር በመገምገም የተመዘገቡ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና በቀጣይ የሚወሰዱ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ተለይተው ተቀምጠዋል። በተጨማሪም የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተሰጥተዋል።
የሥራ ዕድል ፈጠራን በማስፋት፣ ወጣቶችን በማብቃትና የክፍለ ከተማዋን ኢኮኖሚያዊ አቅም በማጠናከር የተጨባጭ ውጤት ለማምጣት ሥራው በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለወጣቶቻችን!
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሥራ፣ አሠሪና ሠራተኛ መምሪያ
🌐 ለተጨማሪ መረጃዎችና ወቅታዊ ዜናዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ገጻችንን ይከተሉ፦
🔵 ፌስቡክ (Facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=61578511693825