04/11/2025
«መርቆሬዎስ» ማለት "የአብ ወዳጅ ማለት ነው፣ እንደገናም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ" ማለት ነው።
ቅዱስ መርቆሬዎስ ከአረማዊነት ወደ ክርስትና ከመጡ ቤተሰቦች ተወለደ።
ለጣኦታት አልሰግድም አምላኬን አልክድም ብሎ ዓለማዊ ሥልጣኑን የናቀ ቅዱስ ነው።
ለእግዚአብሔርና ለሰማያዊው መንግሥት የቀናው ቅዱስ መርቆሬዎስ የንጉሡን ትዕዛዝ አልተቀበልክም ተብሎ ተይዞ በብዙ ተሰቃየ።
በንጉሥ ዳኬዎስ ትዕዛዝም ህዳር ፳፭(25) ቀን አንገቱን በሰይፍ ተቀልቶ መስዋዕትነትን ተቀበለ።
በኋላም የቅዱስ መርቆሪዎስን አንገቱን ቆርጠው
ከገደሉት በኋላ ፈረሱ ለ7 አመት ወንጌልን አስተምሯል።
ጌታችን ቅዱስ መርቆርዮስን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ ሁለተኛው ሊቀ ሰማዕት ተደርጎ ተመርጧል።
የቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት በረከቱ፣ አማላጅነቱና ቃል ኪዳኑ ከሁላችንም ጋር ይሁን🙏