10/09/2026
የክረምቱ ወራት አልፎ፣ አበቦች እንቡጥ እያሳዩ ፣ ፏፏቴዎች ባዘቶ መስለው፣ ከተራራ ምድረበዳማ ስፍራ መፍሰስ ጀምረዋል። ሰማይ ከጥቁር ደመና አልፎ በነጭ ደመና ይሸፈን ጀምሯል ፡፡ እኛም በአዲስ ተስፋ እና መንፈስ የጠራ ውሃና የጠራ ዘመን እየጠበቅን መስከረም 1/2019 አዲስ አመት እንላለን።
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
ዘመን የሚለወጠው ቀን በተቀየረ ብቻ አይደለም፤ ሰው በሚያስበው፣ በሚፈጥረውና ለትውልድ በሚተወው አሻራ ነው።
አዲስ ዓመትም የዘመን መቁጠሪያ አዲስ ገጽ ብቻ ሳይሆን፤ ትናንትን በትውስታ፣ ዛሬን በጥበብ፣ ነገን በተስፋ የምንጽፍበት አዲስ ምዕራፍ ነው።
2019 ዓ.ም ባህላችን ከትናንት የተረከብነውን አደራ ወደ ነገ የምናስተላልፍበት፣ ኪነ-ጥበባችን ማንነታችንን ከመግለጽ ባሻገር ትውልድን የሚያገናኝበት፣ ቅርሳችን ትናንትን ብቻ ሳይመሰክር ለነገ የሚያበራበት ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ ።
ያለፈውን በክብር እንዘክር፤ የተሰጠንን በአደራ እንጠብቅ፤ የሚመጣውን ደግሞ በጥበብ፣ በፈጠራና በጋራ እንጻፍ።
ለመላው ኢትዮጵያውያን ፣ ለባህልና ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ለባህልና ጥበብ ጠባቂዎች ፣ ለስራ ባልደረቦቻችን ፤ 2019 ዓ.ም የሰላም፣ የፍቅር፣ የፈጠራ፣ የባህል ህዳሴና የተስፋ ዓመት ይሁንልን እላለሁ ።
ገብረማርያም ይርጋ
የአብክመ ባህል ፣ኪነጥበብና ዝ/ታሪክ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ
መልካም አዲስ ዓመት!