Amhara National Regional State Head of Government Office

Amhara National Regional State Head of Government Office Amhara National Regional State president office is one of the Amhara region Governmental office that is established for public service delivery.
(6)

ህግዳ- 21/04/2012 ዓ.ም የአመራር አካላት የልማት ጥያቄ ለማቅረብ ግምባር ቀደም የመሆናቸውን ያህል ልማቱን ለሚያስተጓጉሉ ክስተቶች ፈጥነው ምላሽ መስጠትም እንደሚጠበቅባቸው ተገለጠ፡፡ ...
31/12/2019

ህግዳ- 21/04/2012 ዓ.ም የአመራር አካላት የልማት ጥያቄ ለማቅረብ ግምባር ቀደም የመሆናቸውን ያህል ልማቱን ለሚያስተጓጉሉ ክስተቶች ፈጥነው ምላሽ መስጠትም እንደሚጠበቅባቸው ተገለጠ፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የዐማራ ክልል የኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ አለበል ትላንት በተካሄደው የክልሉ የመሰረተ-ልማት አስተባባሪ ኮሚቴ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም መድረክ ላይ እንደገለጡት ባለፉት ዓመታት ክልሉ ፍትሃዊ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ አልነበረም፡፡

ህዝቡና በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላትም ይህን ጥያቄ በግምባር ቀደምትነት ሲያተጋቡ እንደቆዩ አቶ መላኩ አስታውሰዋል ፡፡

ከለውጡ ጋር ተያይዞ ግን የፌድራል መንግስት ውስን የመሰረተ-ልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ አበረታች ጅማሮ እያሳየ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

መብራት፣መንገድ፣መስኖ ልማት፣ንጹህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ምላሽ ለመስጠት የተሞከረባቸው ዘርፎች መሆናቸውን አቶ መላኩ ጠቁመዋል፡፡

ልማቱ ወደ አካባቢው ቢመጣም የአመራር አካላትና ህዝቡ ግን ለልማት የሚፈለገውን ቦታ ፈጥኖ አለማስረከብ፣ ከካሳ ክፍያ ጋር እና ተጓዳኝ ተግባራትን በማጓተት የተባባሪነት ጉድለት እየተስተዋለባቸው ነው ሲሉ አቶ መላኩ ገልጠዋል፡፡

ሁሉም አካላት ልማቱ እንዲመጣ በጠየቁት ልክ የድርሻቸውን በመወጣት ልማቱን ለማፋጠን በሚደረግ ጥረት ተባባሪ አለመሆን ግን ትልቅ ችግር መሆኑን አቶ መላኩ አመልክተዋል ፡፡

የለውጡ መንፈስ ህዝብ ባለው ላይ እንዲጨመርለት እንጂ ያለውን እያጣ አዳዲስ ልማቶች እንዲደናቀፉ አለመሆኑን በውል በመረዳት በኩል በየደረጃው የግንዛቤ ጉድለት ስለሚስተዋል ከዚህ ስህተት ፈጥኖ በመውጣት የድርሻን መወጣት እንደሚገባም አቶ መላኩ በአጽንዎት አሳሰበዋል ፡፡

በፌድራል ብቻ ሳይሆን በክልሉ አቅም ለሚገነቢ ፕሮጀክቶችም ጅምርን ማጠናቀቅ፣ ተግባርን በዕቅድ መምራት፣ ወደ ታች ወረዶ መደገፍ፣ለህብረተሰቡ ግንዛቤ መፍጠርን ጨምሮ ለውይይቱ ተሳታፊዎች ከ10 በላይ ዋና ዋና የቀጣይ ስድስት ወራት የትኩረት አቅጣጫዎችን አቶ መላኩ አስገንዝበዋል ፡፡

ህግዳ፡-17/04/2012 ዓ.ም ‹አሊባባ› እና ‹ቻይና ኤሌክትሪክ ፓዎር› የተባሉ ድርጅቶች የተለያዩ የህክምና እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችን አበረከቱ፡፡አሊባባ እና የቻይና ኤሌክትሪክ ፓዎ...
27/12/2019

ህግዳ፡-17/04/2012 ዓ.ም ‹አሊባባ› እና ‹ቻይና ኤሌክትሪክ ፓዎር› የተባሉ ድርጅቶች የተለያዩ የህክምና እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎችን አበረከቱ፡፡

አሊባባ እና የቻይና ኤሌክትሪክ ፓዎር የተባሉ ድርጅቶች ከ700 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና መሳሪያዎችን ለፈለገ ሕይወት አጠቅላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ከ15 በላይ የሚሆኑ የቻይና የሕክምና ቡድን አባላት በፈለገ ሕይወት አጠቅላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከትናንት ታህሳስ 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀን የሚቆይ የህክምና ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡

የህክምና ቡድኑ ከምርመራ እስከ ቀዶ ጥገና ድረስ እየሰራ እንደሆነም የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዐብይ ፍስሐ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም ተጨማሪ የህክምና መሳሪያዎችን ለመደገፍ እና ሐኪሞችን ወደ ቻይና በመላክ የአጭርና የረጅም ጊዜ ስልጠና ለመስጠት ቃል መገባቱን ነው ስራ አስኪያጁ የገለጹት፡፡

ድርጅቶቹ ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ለመሸንቲ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችም የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በትምህርት ቤቶች የአይ ሲ ቲ ዘርፍን ለማሳደግ እና ለተማሪዎች ቁሳቀስ ሶስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ ማድረጋቸውመም ተገልጿል፡፡

ድርጅቶቹ ድጋፍ ያደረጉት ከዐማራ ልማት ማህበር (አልማ) በቀረበ የድጋፍ ጥያቄ የመነሻ ሐሳብ አማካኝነት መሆኑም ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር አማካሪ ሊዩ ዩ እንዳሉት ለአንድ አካባቢ ዕድገት ቁልፉ ጉዳይ ኢንቨስትመንት ወይም መዋዕለ ንዋይ ሳይሆን ትምህርት ነው፡፡ በመሆኑም መንግስት ትኩረት መስጠት አለበት፤ ተማሪዎችም በርትተው መማር እና መመራመር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በቀጣይም ሙያዊ ድጋፍን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ከክልሉ ጋር አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸውም የአምባሳደሩ አማካሪ ገልጸዋል፡፡

የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ በድጋፍ ርክክቡ ላይ እንደገለጡት ‹‹ለአንድ አገር ዕድገት መሰረቱ ትምህርት በመሆኑ ወላጆች ልጆቻቸውን የማስተማር ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል›› ብለዋል፡፡
በትምህርት ቤቶች ግንባታ ላይም ህብረተሰቡ እንዲሳተፍ ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ሐኪሞችም ሙያዊ ስነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉ መክረዋል፡፡ የክልሉ መንግስትም የሚችለውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የገለጹት፡፡

ምንጭ፡- የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት

ህግዳ፡-13.04/2012  የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ከማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ለዐማራ ህዝብ ፖለቲካዊ ፋይዳው የጐላ እንደሆነ ተገለጠ፡፡የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክ...
23/12/2019

ህግዳ፡-13.04/2012 የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ከማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር ለዐማራ ህዝብ ፖለቲካዊ ፋይዳው የጐላ እንደሆነ ተገለጠ፡፡

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ባንቻምላክ ገ/ማሪያም በ12/2012 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ለሚዲያ ፎረም አባላት ተሳታፊዎች በመክፈቻ ንግግራቸው እንዳሳወቁት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ትኩረት ሰጥተን ከሰራንበት ለክልላችን ብሎም ለአገራችን ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ወሳኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በማገልገል ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በተለይ የዐማራ ህዝብ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች በትክክለኛ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ለመሞገትና ምላሽ ለመስጠት ፋይዳው የጐላ መሆኑን ለተሳታፊዎች ገልጠዋል፡፡

ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ከሌሎች ስነ-ህዝብ ምዝገባ መረጃዎች በባህሪው የተለየ ነው ያሉት የኤጀንሲው ባለሙያ አቶ በተግባር እንየው በገለፃቸው ምዝገባው ወጥና ተነፃፃሪ፣የተሟላ፣ ትክክለኛ እና በህግ ፊት ራሱን ችሎ ማስረጃ ያለው እና ሁሉን አሳታፊም ነው ብለዋል፡፡

የአብክመ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ስለ ኩነቶች ምዝገባ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ህብረተሰቡን በማስገንዘብ ረገድ በክልላችን በተለይ ዐማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ፣ መንግስት ኮሚዩኒኬሽንና የህዝቡ እና የተቋማት ልሳን ከሆኑ የህዝብ ግንኙነት አካለት ጋር ተጣምሮ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ በመሆኑ ሰኔ11/2011 ዓ.ም የሚዲያ ፎረም በመመስረት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ መግባቱን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር ወ/ሮ ማስተዋል አለባቸው ገልጠዋል፡፡

የተቋማትን ተልዕኮ ለማሳካት የጋራ መግባባት ለመፍጠር የአስተሳሰብና የአሰራር ለውጥ ማምጣትን እንደሚጠይቅ የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬቷ ወ/ሮ ማስተዋል አለባቸው ገለጠው የአስተሳሰብና የአሰራር ለውጥ ከማምጣት አንፃር በሚዲያዎች የህዝብ ግንኙነት ተግባራትን በመከወን የማይተካ ሚና እንዳላቸውም ለተሳታፊው አስገንዝበዋል ፡፡

ዳይሬክቶሬቷ አክለውም የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ካለው ክልላዊና አገራዊ ጠቀሜታ አኳያ ህብረተሰቡን ግንዛቤ ማስጨበጥና ማስተማር ስራ ለተቋሙ ብቻ የሚተው ባለመሆኑና የሁሉም አካላት ርብርብ የሚጠይቅ ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም የሚዲያ ፎረሙ መቋቋም ዋና ዓላማም ኤጀንሲው ፊት ለፊት ከሚያደርገው የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በተጨማሪ ተባባሪ አካላት የተለያዩ የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎችን በመጠቀም ፣ህዝቡን በማስተማርና በመቀስቀስ ተግባር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡ ለማስቻል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሞላ ትዛዙ በበኩላቸው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባለፈ ፖለቲካዊ ፋይዳው የጐላ ነው ብለው በተለያዩ ጊዜያት የዐማራ ህዝብ ቁጥርን በመሸራረፍ የልማትና የፋይናንስ ተጠቃሚነቱን ሲነሱት የነበሩ ቡድኖችን በመረጃ ተመስርቶ ለመሞገት እና የህዝባችንን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት ለማረጋጥ ልንስራ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ተቋሙ የተሰጠው ተልዕኮ ትልቅ በመሆኑ በአደገ መንገድ ተመልክተን ሁላችንም በመረባረብ መረጃውን በአግባቡ በመመዝገብ ለቀጣይ ትውልድ ልናስተላልፍ ይገባል በማለት አቶ ሞላ ትዛዙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም የክልሉ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጉዳዬች ኃላፊ አቶ ጌትነት ይርሳው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የክልሉ መንግስት ለሚያቅዳቸው እቅዶች፣ፖሊሲዎች እና ስትራቴጅዎች ወሳኝ ሚና እንዳለው አሳይተው ከምንም በላይ ደግሞ የዐማራ ህዝብን የሚጠቅም በመሆኑ ሁላችንም በሌሎች ደራሽ ስራዎች ሳንወሰድ የተቆጠረ ዕቅድ በማቀድና በዕቅዱ በመመራት የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በመቀባበል ስራውን ትኩረት ሰጠን መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ህግዳ :- 10/04/2012 ዓ.ምየማህበራዊ ተጠያቂነትን በማስፍት ህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ የዐማራ ክልል የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ ገለጡ ። ኃላፊዋ ወ/ሮ ከዲጃ ሀ...
20/12/2019

ህግዳ :- 10/04/2012 ዓ.ምየማህበራዊ ተጠያቂነትን በማስፍት ህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ የዐማራ ክልል የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ኃላፊ ገለጡ ።

ኃላፊዋ ወ/ሮ ከዲጃ ሀሴን ይህን የገለጡት ለተቋሙ ሰራተኞች በእንጅባራና ደብረታቦር ከተሞች ሰሞኑን በተሰጠው የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ላይ ነው ።

የለውጥ ሂደቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ለሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጉድለቶችና ቅሬታዎች በየደረጃው የሚገኙ አንዳንድ የስራ ኃላፊዎች ተገቢ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ የመገፋፋት ክስተትን ስለሚያስተናግዱ ችግሩን ለመከላከል የማህበራዊ ተጠያቂነት አሰራርን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ኃላፊዋ ገልጠዋል ።

ለዚህም የለውጥ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እና ለሰራተኛች ተከታታይነት ያለው የአቅም ግምባታ ስልጠናዎች መሰጠት እንዳለበት ኃላፊዋ አስታውቀዋል ።

ለሰራተኞቹ ስለቅሬታ ማጣራትና ምርመራ' ስለ አገልግሎት ፍተሻ እንዲሁም ስለማህበራዊ ተጠያቂነት አሰራርና ተዛማጅ ጉዳዮች ስልጠና ተሰጥቷል ።

በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ እየታገዘ እንደ አገር በ223 ወረዳዎች እየተተገበረ ያለው የህበራዊ ተጠያቂነት አሰራርን በክልሉ ዘንድሮ ከ31 ወረዳዎች ወደ 51 በማሳደግ ወደ ተግባር መገባቱ ተመልክቷል ።

ሰራተኞቹ በስልጠናው ላይ እንደገለጡት የሰው ሀይል እና የበጀት እጥረት እንዲሁም በእኩል የተመዘነ ስራ እኩል ክፋያ የሚለው መርህ የእነርሱን ደረጃ አሳንሶ የፈረጀ በመሆኑ ሊጤን እንደሚገባ ጠይቀዋል ።

ወ/ሮ ከዲጃም ጥያቄአቸው አሳማኝ መሆኑን ጠቅሰው ለመፍተሄ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል ።

ህግዳ፡-10/04/2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ህሊና ኤራክሲነን ክልሉ ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰጡትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አ...
20/12/2019

ህግዳ፡-10/04/2012 ዓ.ም በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ህሊና ኤራክሲነን ክልሉ ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚሰጡትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ ፡፡

አባሳደሯ በክልሉ ርዕሰ መዲና ባህርዳር ተገኝተው በፊንላንድ መንግስት ድጋፍ እየተከናወኑ በሚገኙ የግብርና፣ የትምህርትና ንጹሕ መጠጥ ውኃ ግንባታ ስራዎች እና በቀጣይ መከናወን ያለባቸው ተግባራት ላይ ከዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የፊንላንድ አምባሳደር ህሊና ኤራክሲነን እንደተናገሩት ኢትዮጵያና ፊንላንድ ከባለፉት 25 ዓመታት ጀምሮ በጋራ እየሠሩ መሆኑን ገልጠው ግብርና፣ የመሬት አስተዳደርና የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ዋና ዋናዎቹ የልማት መስኮች እንደሆኑም አምባሳደሯ አስረድተዋል፡፡

አገሪቱ የያዘቻቸውን የልማት እንቅስቃሴዎች ለመደገፍም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የ22 ሚሊዮን ዩሮ መፈራራማቸውንም አምባሳደሯ ጠቁመው በፊንላንድ መንግስት ድጋፍ የማህበረሰቡን ህይወት መለወጥ የሚያስችሉ የግብርናና ሌሎች ተግባራት እየተከናወኑ ከሚገኙ ክልሎች አንዱ የዐማራ ክልል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

ክልሉ ለኢንቨስትመንት ያለውን ምቹ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አምባሳደሯ አስረድተዋል፡፡

የዐማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው ፊንላንድ ‹‹አግሮ ቢግ›› እና ‹‹ኮ ዋሽ›› በተባሉ መርሀ ግብሮች እየሰራች ላለችው ስራ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ‹‹አግሮ ቢግ›› በተሰኘው የግብርና ፕሮግራም አርሶ አደሮች በሽንኩርት፣ በድንችና በሩዝ ዘመናዊ የአመራረት ሂደት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቅሰው በፕሮግራሙ በክልሉ ያሉ ስምንት ወረዳዎች ተጠቃሚ እንደሆኑ እና ደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ኘሮግራሙ ከሚተገበርባቸው ዞኖች መካከል መሆናቸው አስረድተዋል፡፡

ንጹህ የመጠጥ ውኃ ተደራሽነትን መሰረት አድርጎ በሚሰራው ‹‹ኮ ዋሽ›› በተባለው መርሀ ግብር በክልሉ 40 ወረዳዎች እየተሰራ መሆኑ ተገልጧል፡፡ በተለይ ዘመናዊ የመሬት አያያዝ ስርዓት እንዲፈጠር የፊላንድ እየሰራችው ያለው አርአያነት ሊሰፋ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል፡፡

ፊንላንድ የምትሰጠውን ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል እና ማልማት የሚፈልጉ የአገሪቱ ባለሀብቶችን እንድትልክ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ ወር ከአገሪቱ ፓርላማ፣ ከንግዱ ማህበረሰብና ከባህል ተቋማት የተውጣጣ ልዑክ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ አባሳደር ህሊና ኤራክሲነን ጠቁመዋል፡፡ በሚኖራቸው ቆይታም የዐማራ ክልል ኢንቨስትመንት አማራጮችን እንደሚጎበኙም አባሰደሯ ተናግረዋል፡፡

Address

Bahir Dar, Ethiopia
Bahir Dar

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251-582200924

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara National Regional State Head of Government Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Amhara National Regional State Head of Government Office:

Videos