10/07/2026
"የዲግሪ ማስረጃ ማረጋገጫና የመውጫ ፈተና አዲስ መመሪያ (ከ2010 - 2015 ዓ.ም)"
ይህ መመሪያ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ በማንኛውም የመንግስት እና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ከመስከረም 2010 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም የተመረቁ ተመራቂዎችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፥ ዝርዝር አፈጻጸሙ እንደሚከተለው ነው፦
1. የመውጫ ፈተና ሳይወስዱ ለተመረቁ (የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ)
ማንነታቸው፦ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA/BSc)፣ የሁለተኛ ዲግሪ (MA/MSc) እንዲሁም የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) የያዙ ተመራቂዎች።
የማረጋገጫ መስፈርት፦ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት፥ ባሉበት የትምህርት ደረጃ (ለBA፣ MA እና PhD) የተዘጋጀውን ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ ብቻ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡
2. ከዲፕሎማ/ቲቪቲ (TVET) ተነስተው የመጀመሪያ ዲግሪ ለሰሩ ተመራቂዎች
ይህ ክፍል በቀድሞው ዲፕሎማ (12+2)፣ በ10+3 ወይም በቴክኒክና ሙያ ደረጃ 4 (Level 4) ስልጠና አጠናቀው፥ ትክክለኛነቱ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ (ETA) ወይም በፌደራል/ክልል ቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ የተረጋገጠ ኦሪጅናል ማስረጃ እና ትራንስክሪፕት ያላቸውን ያጠቃልላል።
እነዚህ ተመራቂዎች የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ሳይኖራቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው ከተመረቁ ማስረጃቸው የሚረጋገጠው በሚከተለው ሁኔታ ነው፦
የመግቢያ መስፈርት ማሟያ ሁኔታዎች፦
ለዲግሪ መግቢያ መስፈርት የተቀመጠውን የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና ሳይወስዱ ዲግሪ ተምረው የተመረቁትን፣ ወይም
ለዲግሪ ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የደረጃ 4 የብቃት ማረጋገጫ (COC) ፈተና የወሰዱ ተመራቂዎችን ያጠቃልላል፡፡
የማረጋገጫ መስፈርት፦ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከተሻሻለበት ጊዜ ድረስ የተመረቁ እና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፉ ከሆነ ብቻ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል።